የክርስቲያን አገልግሎት

236/246

ስለ ውድቀት እንዳናስብ

የክርስቶስ ሠራተኞች ስለ አገልግሎት ውድቀት ሊያስቡም ሆነ ሊያወሩ አይገባም፡፡ ጌታ የሱስ በማንኛውም ነገር ኃይላችንና ብርታታችን ነው፡፡ መንፈሱ በውስጣችን መነቃትና መነሳሳት የሚፈጥርልን ሊሆን ይገባል፡፡ የብርሃን አስተላላፊዎች እንድንሆን ራሳችንን በእጆቹ ስናኖር መልካም ማድረግ የሚያስችሉን መንገዶች ድካም ላይ አይወድቁም፡፡ በሙላት ወደ እርሱ እየተቃረብን ወሰን የሌለው ጸጋ ተቀባዮች እንሆናለን፡፡ --Gospel Workers, p. 19. ChSAmh 362.3

ራሳችንን ለእግዚአብሔር ቀድሰን ስንሰጥና በሥራችን ሁሉ አምላካዊውን ትእዛዝ ስንከተል ለአገልግሎቱ መሳካት ራሱ ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡ አዳኛችን የታማኙን ጥረታችንን ስኬት በግምት እንደማይመራ ሁሉ ስለ ውድቀት እንዴ እንኳ ማሰብ የለብንም፡፡ የወደፊቱን ከሚያውቀው ከእርሱ ጋር መተባበር ከእኛ ይጠበቃል፡፡Christ’s Object Lessons, p. 363. ChSAmh 363.1

ጌታ ሕዝቦቹ ለራሳቸው አነስተኛ ግምት ሰጥተው ሲመለከት ቅር ይለዋል፡፡ ምርጦቹ ሕዝቦቹ ለእነርሱ ከተከፈለው ዋጋ አንጻር ራሳቸውን እንዲመለከቱ ይሻል፡፡ እግዚአብሔር የhበረ ዋጋ ለጠየቀው ተልዕኮ ልጁን የላከበት ምክንያት መዳናቸውን በመሻቱ ነው፡፡ ለክብሩ የሚጠቀምባቸው እነዚህ ሕዝቦቹ ለአምላካዊው ስም ውዳሴ ሲያቀርቡ ሲመለከት እጅግ ደስ ይሰኛል፡፡ በሰጣቸው ተስፋ ካመኑ ታላቅ ነገር እንደሚያገኙ እርግጠኞች መሆን ይችላሉ፡፡The Desire of Ages, p. 668. ChSAmh 363.2