የክርስቲያን አገልግሎት
ምዕራፍ 26—ስለ ስኬት የተሰጠን መለኮታዊ ማረጋገጫ
መለኮታዊው ዋስትና
እግዚአብሔር እንዲጠቀምብን ፈቃደኞች እስከሆንን ድረስ በእኛ ውስጥ ሊሠራ ይወዳል፡፡Testimonies, vol. 9, p. 107. እግዚአብሔር በሙሉ ልባችን የምንሰጠውን አገልግሎት በመቀበል ጉድለቶችን ራሱ ይሞላቸዋል፡፡The Ministry of Healing p. 150. ChSAmh 356.1
ምንም እንኳ መልካም የሚያደርገው ሰው አንዳች ዋጋ ያለው ነገር እንዳልሠራ ቢሰማውም ነገር ግን እያንዳንዱ የጽድቅ ሥራ ሕያውና ዘላለማዊ ነው፡፡Testimonies, vol. 2, p. 683. ChSAmh 356.2
ራስዎን በእውነት ለእግዚአብሔር ቀድሰው የሰጡ ከሆነ እርስዎን የብርሃን አስተላላፊ አድርጎ በመጠቀም በጨለማ ያሉትን ወደ እውነት ማምጣት ይችላል፡፡-Testimonies, vol. 7, p. 63. ChSAmh 356.3
በዚህ ወቅት ከእግዚአብሔር ጋር ሠራተኞች ለመሆን የሚመርጡ ሁሉ በቅርቡ በክብር የተሞላ ድል ከሚቀዳጀው እውነት ጋር አሸናፊዎች ይሆናሉ፡፡Testimonies, vol. 9, p. 135. ChSAmh 356.4
ራሱን ለጌታ አገልግሎት አሳልፎ በመስጠት አምላካዊውን እውነት ከመግለጽ ለማይቆጠበው ሊለካ የማይችል ውጤት የሚያስገኝ ኃይል ተሰጥቶታል፡፡Testimonies, vol. 7, p. 30. ChSAmh 356.5
ለባልንጀራችን ደኅንነት በትጋት ስንሠራ እግዚአብሔር እያንዳንዱን ጥረት ያበለጽጋል፡: Testimonies, vol. 9, p. 86. ChSAmh 356.6
ጌታ በታላቁ ዕቅዱ ውስጥ ለእያንዳንዱ ቦታ አለው፡፡ አስፈላጊነት የሌላቸው መክሊቶች አስቀድሞውኑ አይሰጡም፡፡ አነስተኛ መክሊት እንዳለው የሚሰማውእግዚአብሔር ይህን ስጦታ ጥቅም ላይ የሚያውልበት ቦታ አለው፡፡ እንዲv ያለው አንድ መhሊት በታማኝነት አገልግሎት ላይ ከዋለ እግዚአብሔር እንዲውልበት ያቀደውን ታላቅ ሥራ ይሠራል፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 37. ታማኝ አገልጋዮች ከክርስቶስ ጋር ባላቸው አንድነት የሚነኳቸው የድምፅ አውታሮች እስከ ምድር ጫፍ የሚሰሙለዘላለም ተደምጠው የማይጠገቡ ዜማዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡The Ministry of Healing, p. 159. ChSAmh 357.1
በማንኛውም የአገልግሎት ዘርፍ የሚገኝ እውነተኛ ስኬት መንስዔ— ዕድል፣ አጋጣሚ ወይም የጉዳዩ የወደፊት ዕጣ ፈንታ አስቀድሞ ስለተወሰነ አይደለም፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቸርነትና ጣለቃ ገብነት፣ በነጻነት ውሳኔ የመስጠት ይል፣ መልካም ምግባርና ዓላማን ለማሳካት ተግቶ የመሥራት ውጤት ነው፡፡ በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ የአእምሮ ሁኔታና ከፍ ያለ የሥነ ምግባር ባህሪ በአጋጣሚ አይገኝም፡፡ ስኬት እግዚአብሔር የሚያመቻችልንን መልካም አጋጣሚዎች ጥቅም ላይ ማዋል ቻል ነው፡፡-Prophets and Kings, p. 486. ChSAmh 357.2
በሚኖሩበት አካባቢ ወይም ርቀው በመሄድ አገልግሎት በመስጠት ወደ ሥራው ለመግባት ጉጉት የሚያድርባቸው በጌታ ስም ወደ ፊት ይራመዱ፡፡ ጸጋና ብርታት እንዲያገኙ በእግዚአብሔር ላይ እስከ ተማመኑ ድረስ የስኬት ባለቤቶች ይሆናሉ፡፡ ምንም እንኳ መጀመሪያ ላይ የሚሠሩት ሥራ አነስተኛ ቢመስልም ነገር ግን የጌታን ዕቅድ ተከትለው ሲጓዙ አገልግሎቱ እየሰፋና እያደገ ይሄዳል፡፡ ራስ ወዳድ ያልሆነውና ራሱን ለአልግሎት መሥዋዕት የሚያደርገው አገልጋይ ማንም ይሁን ወይም የትምይገኝ—ሕያው አምላh አብሮት ይሠራል፡፡Southern Watchman, April 9, 1903. ChSAmh 357.3