የክርስቲያን አገልግሎት
ከመጀመሪያ አንስቶ በሥራ ላይ የሚገኘው መንፈስ ቅዱስ
እግዚአብሔር ለወደቀው ዘር ያለውን ዓላማ ለማሳካት ከመጀመሪያ አንስቶ ሰብዓዊ ወኪሎቹን ተጠቅሞ በመንፈስ ቅዱስ ይሠራ ነበር፡፡ ይህ ሁናቴ በኃይማኖት አባቶች vይወት ተገልጾአል፡፡ በሙሴ ዘመን “ያስተምራቸው ዘንድ ቸር መንፈስህን ሰጠሃቸው” ተብሎ የተነገረ ሲሆን በሐዋርያት ዘመን ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ለቤተ ክርስቲያን እጹብ ድንቅ ነገሮች ተሠርተው ነበር፡፡ ለካሌብና ለኢያሱ እምነትና ወኔ የሰጠ፣ የኃይማኖት አባቶችን ደግፎ ያቆየና የሐዋርያትን ቤተ hርስቲያን ውጤታማ ያደረገ ያው ኃይል—በእያንዳንዱ ቀጣይ ትውልድ የእግዚአብሔርን ታማኝ ልጆች ደግፎ ይይዛል፡፡ በጨለማው ዘመን ይኖሩ ለነበሩት ዋልዴንስ ክርስቲያኖች የተሐድሶ ጎዳና የተቀየሰላቸው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ነበር፡፡ ዘመናዊውን የወንጌል ተልዕኮ ለማቋቋም ፋና ወጊ የነበሩትን ታዋቂ ወንዶችና ሴቶች ጥረትም ሆነ የመጽሐፍ ቅዱስን በልዩ ልዩ ቋንቋዎችና ዘዬዎች ትርጓሜ ውጤታማ ያደረገ—ያው መንፈስ ቅዱስ ነው: ፡— The Acts of the Apostles, p. 53. ChSAmh 355.1