የክርስቲያን አገልግሎት
ስኬት የምናገኝበት ወሳኝ አካሄድ
የመንፈስ ቅዱስ በወንጌል ሠራተኞች መሃል መኖር ለእውነት እወጃ የሚሰጠው ኃይል—ዓለም ሊሰጥ የማይችለውን ማንኛውም ክብርና ዝና ያጎናጽፋል፡፡The Acts of the Apostles, p. 51. ChSAmh 352.1
እግዚአብሔር ከፊታችን ያለውን ሥራ በራሳችን ብርታት እንድንሠራ እይጠይቀንም፡፡ይልቁንም ለማንኛውም ከተፈጥሮአችን ጋር ለማይመጣጠን ድንገተኛ ሁኔታ መለኮታዊ እገዛ አቅርቦልናል፡፡ እርሱ አእምሮአችንን ለማብራት፣ ልባችንን ለማጥራት፣ የሰጠንን ተስፋ ለማጠንከርና ለማረጋገጥ ሲል በማንኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ የሚረዳንን መንፈስ ቅዱስ ሰጥቶናል፡፡ Southern Watchman, Aug. 1, 1905. ChSAmh 352.2
መንፈስ ቅዱስ ከወረደ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ በክርስቶስና እርሱ በሞተላቸው ፍቅር ስለተሞሉ በሚናገሯቸው ቃላትና በጸሎታቸው ልቦች ይቀልጡ ነበር፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መናገራቸውን ተከትሎ በዚያ ኃይል ተጽእኖ ስር የወደቁ ሁሉ ተለውጠው ነበር፡The Acts of the Apostles, p. 22. ChSAmh 352.3
ራስ ወዳዱን ማንነት ወደ ጎን ትቶ መንፈስ ቅዱስ በልቡ ውስጥ እንዲሠራ ማንነቱን ክፍት በማድረግ ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር በተቀደሰ ህይወት የሚመላለሰው ነፍስ የሚኖረው ጠቀሜታ ገደብ የለውም፡፡— Southern Watchman, Aug. 1, 1905. ChSAmh 352.4
በጴንጤቆስጤ ዕለት የወረደው መንፈስ ቅዱስ ያስከተለው ውጤት ምን ነበር? ከመቃብር ስለተነሳው አዳኝ ይነገር የነበረው አስደሳች ዜና ይታወቁ ወዳልነበሩ የዓለም ክፍሎች ተዛምቶ ነበር. የደቀ መዛሙርቱን በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ አገልግሎትን ተከትሎ የሕይወትን ቃል ይቀበሉ የነበሩ ሰዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን ይጨመሩ ነበር፡፡ እነዚህ አዳዲስ ነፍሳት ራሳቸውን ለአገልግሎት እየቀደሱ ልባቸውን በደስታ የሞላውን የሰላምና ደስታ ተስፋ ለሌሎች ያካፍሉ ነበር፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች” እያሉ ይሰብኩ ነበር፡፡ መልእክቱን ለመስጠት ወደ ኋላ አላሉም ወይም ዛቻም ሆነ ማስፈራሪያ አልበገራቸውም፡፡ ጌታ በእነርሱ ውስጥ ይናገር ስለነበር በሄዱበት ሁሉ በሽተኞች ይፈወሱ፣ ወንጌልም ለድኾች ይሰበክ ነበር፡፡ ሰዎች ራሳቸውን በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሰር ሲያውሉ እግዚአብሔር በእነርሱ አማካይነት እጅግ ታላላቅ ድንቅ ነገሮች ማድረግ ይችላል፡፡Southern Watchman, Aug 1, 1905. ChSAmh 352.5
መንፈስ ቅዱስ የመንፈሳዊ vይወት እስትንፋስ ነው፡፡ መንፈስን መቀበል የክርስቶስን ህይወት መቀበል ማለት ነው፡፡ መንፈስ በተቀባዩ ግለሰብ ውስጥ የክርስቶስ መንፈስ እንዲሰርጽ ያደርጋል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ተወካይ በመሆን በስሟ ለማገልገል ብቃት የሚኖራቸው ከእግዚአብሔር የተማሩ፣ መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው የሚሠራና በሕይወታቸው የhርስቶስ ዓይነት ሕይወት የሚታይባቸው ሰዎች ብቻ ናቸው፡: The De sire of Ages, p. 805. ChSAmh 353.1
በቅርቡ _ እጅግ ያልተለመዱ ፈጣን ለውጦች እውን ይሆናሉ፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝቦች በሰማያዊው ጥበብ ተሞልተው ጊዜ የማይሰጥ ቀውስ ውስጥ የወደቀውን ይህን ትውልድ እንዲታደጉና በሞራል የዘቀጠ እንቅስቃሴ ውስጥ ለሚገኘው ዓለም አጸፋዊ ምላሽ እንዲሰጡየመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ይቀበላሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ካላንቀላፋች፣ የክርስቶስ ተከታዮች የሚተጉና የሚጸልዩ ከሆነ፤ የጠላትን እንቅስቃሴ ለማስተዋልና ለመረዳት የሚያስችል ብርሃን ሊኖራቸው ይችላል፡፡— Testimonies, vol. 6, p. 436. ChSAmh 353.2