የክርስቲያን አገልግሎት

225/246

ዕረፍትና ተመስጥኦ

የየሱስ ደቀ መዛሙርት እንዴት መሥራትና ማረፍ እንዳለባቸው መማር ነበረባቸው፡፡ በእግዚአብሔር የተመረጡ ሠራተኞች የክርስቶስን ትእዛዛት በመስማት አገልግሎት እየሰጡ ለጥቂት ጊዜ ገለል ብለው ዕረፍት እንዲያደርጉ ይፈለጋል፡፡ ያሌ የከበረ ዋጋ ያላቸው ነፍሳት ይህን ትዕዛዝ ባለማስተዋላቸው የተነሳ አላስፈላጊ መሥዋዕትነት ለመክፈል ተገደዋል... ምንም እንኳ መከሩ ታላቅ ሠራተኞች ግን ጥቂት ቢሆኑም ጤንትንና ህይወትን መሥዋዕት በማድረግ የሚገኝ ነገር አይኖርም... ገና ያልተነካውን የሥራ መጠን እነርሱ ሊያከናውኑ ከሚችሉት ኢምንት ድርሻ ጋር ሲያስተያዩ እጅግ ተስፋ የሚቆርጡ፣ የሚደክሙና የሚዝሉ አያሌ ሠራተኞች አሉ፡፡ ለበለጠው ክንውን የላቀውን አካላዊ ብቃት ለሚመኙ የሱስ “እስቲ ብቻችሁን ከእኔ ጋር ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራ እንሂድና ጥቂት ዕረፉ” ይላቸዋል፡፡Review and Herald, Nov. 7, 1893. ChSAmh 345.1

የክርስትና ህይወት ፋታ በሌለው እንቅስቃሴ ወይም በማያቋርጥ አምልኮ የተሞላ አይደለም፡፡ ምንም እንኳ ክርስቲያኖች ለጠፉ ወገኖች በጽናት መሥራት ቢጠበቅባቸውምለተመስጦ፣ ለጸሎትና ቃሉን ለማጥናት ጊዜ መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡ አገልግሎት ሁል ጊዜ በሥራ ጫናና ኃላፊነት መወጠር አይደለም፡፡ ይህ አካሄድ የግል ቅድስና ችላ እንዲባል ከማድረጉ ባሻገር የአእምሮም ሆነ የአካል ኃይል ጉዳት ላይ እንዲወድቅ መንስዔ ይሆናል፡፡- Review and Herald, Nov. 7, 1893. ChSAmh 345.2

በአምላካዊው ሥልጠና ስር የሚገኙ ሁሉ ከገዛ ልባቸው፣ ከተፈጥሮና ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት የሚፈጥሩባቸው በጸጥታ የተሞሉ ሰዓታት ያስፈልጓቸዋል፡፡ ከዓለምም ሆነ ከወግና ልማዷ ጋር ስምሙ ያልሆነ ህይወት በእነርሱ ሊገለጥ ይገባል፡፡ የአምላካዊውን ፈቃድ ዕውቀት በማግኘቱ ረገድ የግል ተሞክሮ ወሳኝ እንደመሆኑ እግዚአብሔር በግል ለልባችን ሲናገረን ልናደምጠው የግድ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሌላ ድምፅ ጭጭ ሲልና _ እርሱን ብቻ በጸጥታ ስንጠባበቅ የነፍሳችን ውስጥ ዝምታ አምላካዊውን ድምፅ በግልጽ ለይተን እንድናደምጥ ያስችለናል፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ይለናል “ዕረፉ እኔ አምላh እንደሆንኩም ዕወቁ፡፡” ይv ለእግዚአብሔር ለምንሠራ ሁሉ ተፈላጊውን ውጤት የሚያስገኝልን ዝግጅት ነው:፡ በጥድፊያ የተጨናነቀውና በውጥረት የዛለው የህይወት እንቅስቃሴ መታደስ ሲያገኝ በብርሃንና ሰላማዊ ስሜት ውስጥ የተከበበ ይሆናል፡፡ ከአካላዊም ሆነ ከአእምሮአዊ ብርታት አዲስ ገጸ በረከት ይቀበላል፡፡ መለኮታዊውን ኃይል በመግለጽ ወደ ሰዎች ልብ መድረስ የሚችል፣ በመልካም መዓዛው የሚያውድ የሕይወት ትንፋሽ ጠረን ይኖረዋል፡፡— The Ministry of Healing p. 58. ChSAmh 346.1