የክርስቲያን አገልግሎት
የተረጋጋ ስብዕና
እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጅ ለጌታ ምርጥ አገልግሎት መስጠት ይችል ዘንድ ለሚበላውምግብ፣ ለአለባበሱና ለሚሠራው ሥራ ልዩ ትኩረት መስጠቱ የግድና አስፈላጊ ነው፡፡ ሠራተኛው ብርቱ የሥራና ኃላፊነት ጫና ደርሶበት አእምሮውም ሆነ አካሉ ሲዝል ለጊዜው ከሥራ ገበታው ዘወር - ብሎ ዕረፍት ያድርግ፡፡ ዕረፍቱ ቀጣይ ተግባራትን ለማከናወን በቂ ዝግጅት እንዲያገኝ ያስችለዋል፡፡ ሁሌም በመንገዳችን እየተመላለሰ ፈተና በመደንቀር በእያንዳንዱ ድhመታችን ጥቅም የሚያገኝ በንቃት የሚሠራ ጠላት አለን፡፡ አእምሮ በሥራ ጫና ሲጨናነቅና አካል ሲዝል ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ የእግዚአብሔርን ልጅ ለመዘረር ይችል ዘንድ በጽንፈኛ ፈተናው ነፍስን ቁልቁል ይጫናታል፡፡ ለእግዚአብሔር የሚሠራው አገልጋይ ጉልበቱን በሥራ ላይ ሲያፈስ መድከሙና መዛሉ አይቀሬ እንደመሆኑ አረፍ ብሎ ከየሱስ ጋር ግንኙነት ያድርግ፡፡Review and Herald, Nov. 14, 1893. ChSAmh 343.3
አካላዊ ጉልበታችንን በአግባቡ ሳንጠቀም ስንቀር ለእግዚአብሔር ክብር ይውል የነበረውን የሕይወት ዘመናችንን እናሳጥራለን፡፡ እግዚአብሔር የሰጠንን ሥራ ለማከናወን ብቃት የጎደለን እንሆናለን፡፡ አፈንጋጭ ባህሪዎች እንዲፈጠሩ በመፍቀድ፣ ከሥራ በኋላ ዕረፍት ባለማድረግና ለጤና ጎጂ የአመጋገብ ባህሎችን በማዳበር የደካማነትን መሰረት እንጥላለን፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ችላ በማለት፣ አካልን ወይም አእምሮን ከመጠን በላይ በማሠራት ነርቨስ ሲስተም ሚዛኑን እንዲስት እናደርጋለን፡፡ የተፈጥሮን ሕግጋት በመናቅ አካላዊም ሆነ አእምሮአዊ የአገልግሎት ብቃት እንዲጎድላቸው በማድረግ ህይወታቸውን የሚያሳጥሩ እነዚv ሰዎች እግዚአብሔርንም ሆነ ባልንጀራቸውን በመስረቃቸው ጥፋተኞች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር እነርሱን ወደዚህ ዓለም ለአገልግሎት በመላክ ለሌሎች በረከት እንዲያመጡ የሰጣቸው ዕድል በገዛ ራሳቸው ልማድ በአጭሩ እንዲቀጭ በማድረጋቸው በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ሊያከናውኑ ይችሉ ለነበረው ሥራ እንኳ ራሳቸውን ብቁ ከማድረግ ገትተዋል፡፡ ጉዳት ሊያስከትሉ በሚችሉ ልማዶች ተተብትበን የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ጎን ስንል ጌታ እንደ ጥፋተኛ ይመለከተናል፡፡ Christ’s Object Lessons, pp. 346, 347. ChSAmh 344.1
ሁል ጊዜም በምህረትና በርኅራኄ የተሞላው አምላካችን ለሚጠይቀን ነገር ምከንያታዊ ነው፡፡ በጤንነታችን ላይ መቃወስ ወይም በማሰብ ኃይላችን ላይ ድካም የሚያስከትል አካሄድ እንድንከተል አይጠይቀንም፡፡ ብርቱ ተጽእኖም ሆነ ጫና ሊያስከትል በሚችል ሁናቴ ውስጥ እየሠራን ለነርቭ መዛል እንድንጋለጥ ምኞቱ አይደለም፡፡ የምናመዛዝንበት አእምሮ የሰጠን ጌታ አመከንዮአዊውን አስተሳሰብ እየተለማመድንና በውስጣችን ለተተከሉት የህይወት ሕግጋት እየተገዛን ሚዛኑን ከጠበቀ ስብዕና ጋር ውህደት ስንፈጥር ለመመልከት ይጠባበቃል፡፡ አንዱ ቀን አልፎ ሌላው ሲተካ የራሱን ኃላፊነትና ግዴታ ይዞ የሚመጣ እንደመሆኑ የነገው ሥራ ዛሬን ማጨናነቅ የለበትም፡፡ የእግዚአብሔር ሠራተኞች አገልግሎቱ ምን ያህል የተቀደሰ ባህሪ እንደተላበሰ በማስተዋል ለነገው አገልግሎትዛሬ በማመዛዘንና በብልሃት ጉልበታቸውን ሊያዘጋጁ ይገባል፡፡Review and Herald, Nov. 7, 1893. ChSAmh 344.2