የክርስቲያን አገልግሎት
ተስፋ መቁረጥን የምንከላከልበት አካሄድ
የጌታ አገልጋዮች ተስፋ አስቆራጭ ሁናቴዎች ሊሰከቱ እንደሚችሉ በማስተዋል ከወዲሁ ተጋጅተው ሊጠብቁ ይገባል፡፡ እነዚህን ሕዝቦች ጠላት በቁጣ፣ በንቀትና በጨካኝነት ብቻ አይፈትናቸውም ነገር ግን በስንፍና፣ በልዩነቶች፣ በበራድነት፣ በወዳጆችና ረዳቶች ክስ ጭምር ይሆናል፡፡ አምላካዊውን ሥራ ወደ ፊት የማራመድ ምኞት ያላቸው የሚመስሉ አንዳንዶች ለተራ ወሬና አሉባልታ ጆሮአቸውን እየሰጡ በግማሽ ልባቸው የስም አጥፊውን፣ የትዕቢተኛውንና የጠንቀኛውን ሰብቅ እየሰሙ ለአገልግሎት የተዘረጋውን ወንጌላዊ እጅ ያዳክማሉ፡፡ …እጅግ ተስፋ አስቆራጭ በነበረው ሰዓት ነህምያ በእግዚአብሔር እንደታመነ ሁሉ የእኛም መከላከያ መሣሪያ ይኸው ሊሆን ይገባል፡፡ ጌታ ለእኛ ያደረገውን ማስታወስ ሊገጥመን ለሚችል ማንኛውም አደጋ ድጋፋችን ይሆነናል፡፡ “ለገዛ ልጁ ያልሳሳለት ነገር ግን ለሁላችንም አሳልፎ የሰጠው እርሱ ሁሉንስ ነገር ከእርሱ ጋር እንደ ምን በልግስና አይሰጠን?” “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ሊቃወመን ይችላል?” የሰይጣንና የወኪሎቹ ሴራ የቱንም ያህል የረቀቀ ቢሆን እግዚአብሔር ግን ምክራቸውን ሁሉ ያፈራርሳል፣ መናም ስኬታማ የክርስቲያን አልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ብቃት ማጎልበቻዎች ያስቀረዋል፡፡Southern Watchman, April 19, 1904. ChSAmh 332.1
የውዝግቡ ግንባር ቀደም ተሰላፊዎች ግፊቱ ከተወገደ በኋላ ውጤቱ ያለማቋረጥ ሊሰማ የሚችል የተለየ ሥራ እንዲሠሩ በመንፈስ ቅዱስ ይገፋፋሉ፡፡ መከፋትና ተስፈ መቁረጥ ጀግና የተባለውን እምነት ሊያንቀጠቅጥጽኑና የማያወላውለውን ሊያዳክም ቢችልም፤ ነገር ግን ይህን የሚያስተውለው አምላክ ፍቅርና ርኅራኄውን ከማሳየት አሁንም ወደ ኋላ አይልም፡፡ እርሱ የልብን ዓላማና ዕቅድ ያነባል፡፡ ሁሉም ነገር በድንግዝግዝ ጨለማ የተዳፈነ ሲመስል ጌታን በትዕግሥት መጠባበቅና እርሱን ታምኖ መመላለስ የሥራው መሪዎች ሊማሩት የሚገባ ትምህርት ይሆናል፡፡ በመከራቸው ቀን ሰማይ አይደፋባቸውም፡፡ ከንቱነት ተሰምቷት ሙሉ ለሙሉ በእግዚአብሔር ላይ ተስፋ _ ከምታደርገው ነፍስ የላቀ ደካማነት ደግሞም አይበገሬነት ሊኖር አይችልም፡፡Prophets and Kings, pp. 174, 175. ChSAmh 333.1
ጌታ ለውድቀትም ሆነ ተስፋ መቁረጥ አይበገሬ ወታደሮች ጥሪ ቢያቀርብም—ይvን ውጣ ውረድ የበዛበትንና እምብዛም የማያስደስት ገጽታ የተላበሰ ሥራ የሚቀበል ማን ነው? ሁላችን ክርስቶስን ምሳሌያችን አድርገን እንድንወስድ ጥሪ ቀርቦልናል፡፡--Review and Herald, July 17, 1894. ChSAmh 333.2
ዛሬ በብዙዎች ዘንድ ታዋቂ ያልሆነውን እውነት እየሰበኩ፤ ጳውሎስና ጓደኞቹ በዚያን ዘመን ከመሰከሩላቸው ሕዝቦች ይልቅ ክርስቲያን ነን በሚሉ መሃል እኛገኘዋለን ብለው ያሰቡትን ተቀባይነት ሳያገኙ ቢቀሩ ተስፋ አይቁረጡ፡፡ የመስቀሉ መልእክተኞች የትጋትና የጸሎት የጦር ልብስ ለብሰው ሁል ጊዜ በየሱስ ስም እየሠሩ በእምነትና በወኔ ወደ ፊት ይገስግሱ፡፡— The Acts of the Apostles, p. 230. ChSAmh 333.3