የክርስቲያን አገልግሎት

212/246

ቅድመ ዝግጅትና ጥንቃቄ

ነህምያ የየሩሳሌምን ቅጥር ዳግም ለመገንባት በነበረው ዕቅድ አምላካዊውን እርዳታ ይማጸን በነበረበት ወቅት አንዳችም ጥንቃቄም ሆነ ኃላፊነት እንደማይሰማው ሰው እጆቹን አጣጥፎ አልተቀመጠም ነበር፡፡ ይልቁንም የሥራውን ስኬት ሊያረጋግጥ የሚችል አስገራሚ ቅድመ ዝግጅትና ጥንቃቄ በማድረግ አስፈላጊውን ሁሉ ከወዲሁ አሟላ፡፡ የነህምያ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ጥንቃቄ የታከለበት ነበር፡፡--Southern Watchman, March 15, 1904. ChSAmh 331.1

ራሱን ለእግዚአብሔር ቀድሶ የሰጠው የነህምያ ምሳሌነት በእምነት መጸለይ ብቻ ሳይሆን በትጋትና በታማኝነት መሥራት እንደሚገባ ለመላው የእግዚአብሔር ሕዝብ ትምህርት ሊሆን ይገባል፡፡ እግዚአብሔር በቸርነቱ ጣልቃ እየገባ ከሰጠን ሥራ ምን ያህሉን አስተጓጎልን? መልሱ ቀላል ነው ቅድመ ዝግጅትና ጥንቃቄ ለኃይማኖት ሊኖረው ስለሚገባ አንደምታ አነስተኛ ግምት እየሰጠን ችላ ብለነዋል! ይህ ለብርቱ ውድቀት የሚዳርግ ስትvት ነው፡፡ ለእግዚአብሔር የላቀ ውጤታማ አገልግሎት እንድንሰጥ የሚያlችለንን እያንዳንዱን አቅም ማበልጸግና ለሥራው ብቁ አድርጎ የተልዕኮው አካል ማድረግ የውዴታ ግዴታችን ነው፡፡ ነገሮችን በጥንቃቄ በማጤን በሳልና ጥሩ ሆነው የጎለበቱ ዕቅዶችን ማውጣት በነህምያ ዘመን እንደነበረው ለዛሬውም የተቀደሰ ተልዕኮ ስኬት ወሳኝ ነው:: Southern Watchman, March 15, 1904. ChSAmh 331.2