የክርስቲያን አገልግሎት

196/246

የhርስትና ማዕረግና ትህትና

በcንበት ጠባቂዎች የኃላፊነት ተዋረድ የሚስተዋለው እውነተኛ የhርስትና ክብርና የባሕሪ ልዕልና እጦት እንደ ሕዝብ ወደ ኋላ በመጎተት ተስፋ የምናደርገውን እውነት vይወት የማይሰጥ ያደርገዋል፡፡ አእምሮንና ባህሪን የማስተማርና የማሠልጠን ሥራ እስከ ፍጽምና ሊያመራ የሚችል ሂደት ነው፡፡ እውነት አለን የሚሉ አሁን እያገኙ ያሉትን ልዩ መብት፣ ጥቅምና መልካም አጋጣሚ በየሱስ ክርስቶስ ለማደግ ሥራ ላይ የማያውሉ ከሆነ ውሎ አድሮ ለእውነት ግስጋሴም ሆነ ለክርስቶስ ክብር መስጠት ያቆማሉ፡፡-- Testimonies, vol. 4, pp. 358, 359. ChSAmh 311.3

በሥርዓት በሚመራ ሕይወትና በተቀደሰ አነጋገር የሥራውን ክብርና ማዕረግ ጠብቀው መጓዝዎን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡ አምላካዊውን ትእዛዛት ከፍ አድርጎ ለማውለብለብ ፈጽሞ ፍርሐት _ አይሰማዎ... ማንኛውም ሻካራም ሆነ ግርድፍ ከእኛ ሊወገድ የግድ ነው፡፡ መልካም ምግባር፣ የባህሪ ልዕልና _ እንዲሁም ክርስቲያናዊ ትህትና ከፍተኛ ዋጋ ተሰጥቶአቸው በእንክብካቤ ሊያዙ ይገባል፡፡ ራስዎን ከጥድፊያና ከድንዛዜ ይጠብቁ እንጂ ሊይዙት እንደሚገባ መልካም ባህሪ አይመልከቱ፡፡ ማንንም ላለማሳዘን ወይም ቅር ላለማሰኘት ጥረት ያድርጉ፡፡--Review and Herald, Nov. 25, 1890. ChSAmh 312.1

የአምላካዊው ፈቃድ ዕውቀት ያላቸው ወንዶችና ሴቶች ስኬታማ ሠራተኞች የሚያደርጋቸውን ትምህርት ተምረው ወደ ሥራው መግባታቸው በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡ እነዚህ ወገኖች ውጪያዊ ማንነታቸው ብቻ እያንጸባረቀና የታይታ ፈገግታ እያሳዩ ዓለምን የሚወዱ ሳይሆን፤ የመለኮታዊው ተፈጥሮ ወራሽ የሆነ ማንኛውም ክርስቲያን ሊኖረው የሚችል ሰማያዊ ባህሪ የተላበሰ እውነተኛ አንጸባራቂና የነጠረ ማስተዋል ባለቤቶች ናቸው፡፡Testimonies, vol. 4, p. 358. ChSAmh 312.2

ከዚህ ቀደም ለዓለም ተሰጥቶ የማያውቅ የነጠረ እውነት፣ ተስፋና እምነት ባለቤቶች እንደመሆናችን ይህን መልእክት እጅግ በከበረ ግርማ ለዓለም ለማቅረብ ፍላጎታችን ነው፡፡ የከበረውን መልእክት በማመናችንና ከተቀደሰው መልእክት ጋር አግባብ በመፍጠራችን ለዓለም ምኅረት እየለመንን የምናልፍ አድርገን ራሳችንን አንመለከትም፡፡ ይልቁንም—ደካማ ሠራተኞቹ ብንሆንም በእጅጉ አስፈላጊ፣ አስደሳችና ከማንኛውም ጊዜያዊና ዓለማዊ መልእክት በላቀ የከበረ የሆነውን ርዕሰ ጉዳይ እንደያዝን በማመን ከእግዚአብሔር ጋር በትህትና ለመራመድ እንፈልጋለን፡፡Review and Herald, July 26, 1887. ChSAmh 312.3

ለነፍሳት የሚሠራው ሥራ ራስን ቀድሶ መስጠት፣ ሐቀኝነት፣ ብልህነት፣ ጠንካራ ሠራተኝነት፣ አቅምና መላ ይፈልጋል፡ እነዚህን የብቃት መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ሰው ለመልካሙ ሥራ የአዛዥነት ተጽእኖ ይኖረዋል እንጂ የበታች ተደርጎ ሊታይ ×ይችልም፡፡ ፡፡::-Gospel Workers, p. III. ChSAmh 313.1

ግለሰቦችንና ቤተሰቦችን ምርጥ በሆነ አካሄድ እንዴት መድረስ እንዳለባቸው ለመማር ፈቃደኞች የሆኑ በሥራው ሊሰማሩ ይገባል፡፡ አለባበሳቸው የተሽቀረቀረ ሳይሆን ነገር ግን ንጽሕናው የተጠበቀ፤ ከሰው ጋር ያላቸው አግባብ—የሚያርቅ ሳይሆን የሚስብና መልካም ምግባር የተላበሰ መሆን ይኖርበታል፡፡ እንደ ሕዝብ እውነተኛ ትህትና በእጅጉ ይፈለግብናል፡፡ በወንጌል ሥራ የሚሠማሩ እንዲህ _ ያለውን ስብዕና እንዲያበለጽጉና እንዲሊላበሱ ተጠርተዋል፡ ፡- Testimonies, vol. 4, pp. 391 392. ChSAmh 313.2