የክርስቲያን አገልግሎት
አእምሮን ማበልጸግ
አእምሮን የማበልጸግ ሥራ እንደ ሕዝብ የሚያሻንና ጊዜው የሚጠይቀውን ለሟሟላት ሊኖረን የሚገባ ነው::-- Testimonies, vol. 4, p. 414. ChSAmh 309.2
ወደ ጌታ ሥራ በድንገትና ያለ ዕቅድ ገብተን ስኬት መጠበቅ የለብንም፡፡ ጌታ አእምሮአቸውን ተጠቅመው በማስተዋል የሚሠሩ ሠራተኞችን ይፈልጋል፡፡ የሱስ ብልህነት የጎደለውን ስህተት ለሚሠሩ ሳይሆን አብረውት ለሚሠሩ ጥሪ ያቀርባል፡፡ እግዚአብሔር ለነፍሳት ደኅንነት አስፈላጊ የሆነውን ታላቅ ሥራ የሚሠሩ ቀና አስተሳሰብ ያላቸውንና ብልvዎችን ይፈልጋል፡፡--Testimonies, vol. 4, p. 67. ChSAmh 309.3
አንዳንዶች አእምሮአቸውን በማለማድ ለመልካም ሥነ ምግባር ለማስገዛት ይሻሉ፡፡ አእምሮ በተደጋጋሚ ቀናውን እንዲያስብ ተደርጎ ሊገራ ይገባል፡፡ ሰዎች--ሌሎች ለእነርሱ እንዲያስቡና ችግሮቻቸውን እንዲያቃልሉ በመፍቀድ አእምሮአቸው ጽንሰ ሐሳቦችን እንዲያብላላ ሳይፈቅዱ ሲቀሩ ያለፈውን የማስታወስ ኃይላቸውም ሆነ የወደፊቱን የመመልከት ችሎታቸው ደካማነት የሚቀጥል ይሆናል፡፡ እያንዳንዱ ሰው አእምሮውን የማስተማርና የማሰልጠን ጥረት ከማድረግ ወደ ኋላ ሊል አይገባም፡፡Testimonies, vol. 2, p. 188. ChSAmh 309.4
እግዚአብሔር በስንፍናችን፣ ባልተገራ አስተሳሰባችን፣ በደካማ ስሜታችንና በደብዛዛ የማስታወስ ችሎታችን ደስተኞች ሆነን እንድንቀጥል አይፈልግም፡፡- Counsels to Teachers, p. 506. ChSAmh 310.1
የእግዚአብሔር ሕዝቦች ተጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች፣ ዕውቀትን ለመሸመት ጽኑ ፍላጎት ያላቸውና ጊዜያቸውን በዋዛ ፈዛዛ የማያሳልፉ ሊሆኑ የግድ ነው፡፡ በኃይል የተሞሉና ተጽእኖ አሳዳሪ ክርስቲያኖች እንደመሆናቸው ተግተው በመሥራት በማንኛውም ከፍታና ልቀት ላይ ይደርሳሉ፡፡-Testimonies, vol. 4, p. 411. ChSAmh 310.2
ጊዜ የከበረ ዋጋ እንዳለው ልብ እንበል፡፡ በጉዞ ላይ የምናጠፋው ጊዜ፣ ምግብ እስኪቀርብ የሚባhነው... የጊዜን ዋጋ የማያስተውሉ ወገኖች ቀጥረውን ጭልጥ ሲሉ በከንቱ የሚጠፋው ጊዜ የትዬለሌ እንደመሆኑ መጽሐፍ ከእጃችን ባይለይና እነዚህ ሽርፍራፊ ሰዓቶች ለጥናት፣ ለንባብ ወይም ለተመስጦ ጊዜ ቢውሉ ምን ያህል ክንውን ማግኘት በቻልን! Christ’s Object Lessons, pp. 343, 344. ChSAmh 310.3
ቆራጥና የማያወላውል ዓላማ ያነገበ፣ ጽኑ አቋም ኖሮት ጊዜውን በአግባቡ ጥቅም ላይ የሚያውል ግለሰብ፤ ሰዎችበየትኛውም ኃላፊነት ተጽእኖ አሳዳሪዎች፣ ጠቀሜታ ያላቸው፣ የዕውቀት ባለቤቶችና በዲሲፕሊን የታነጸ አእምሮ ባለቤት እንዲሆኑ ያስችላቸዋል፡ Christs Object Lessons, p. 334. ChSAmh 310.4
በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ የተቀመጡ ሰዎች የማያቋርጥ እድገትና ግስጋሴ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ _ አሮጌውን ተሞhሮ ብቻ አጥብቀው ይዘው የአዳዲሶቹን ሳይንሳዊ አሠራር ስልቶች ጠቀሜታ ችላ ማለት የለባቸውም፡፡ ምንም እንኳ ሰው ወደዚህች ምድር ከመጣ በኋላ ከእግዚአብሔር ፍጥረታት ሁሉ ደካማና ቅንነት የጎደለው ተፈጥሮ የተላበሰ ቢሆንም ነገር ግን በማያቋርጥ ዕድገትና ግስጋሴ ክህሎት የተሞላ ነው፡፡ ከመላእhት አነስ ተደርጎ የተፈጠረው ሰብዓዊ ፍጡር የዕውቀት ፍጽምናና የጸባይ ንጽሕና ላይ እስኪደርስ አእምሮው ያለማቋረጥ ያድጋል፡፡-Testimonies, vol. 4, p. 93. ChSAmh 310.5
ከእግዚአብሔር ጋር ሠራተኞች የሚሆኑ ሁሉ ለእያንዳንዱ የሰውነታቸው አካል ፍጽምናና የአእምሮ ልቀት ብርቱ ተግል ሊያደርጉ ይገባል፡፡ እውነተኛ ትምህርት አካላዊው፣ አእምሮአዊውና ሞራላዊው ኃይል እያንዳንዱን ተግባር ለመፈጸም እንዲያስችለን አድርጎ ማዘጋጀት ነው፡፡ አካልን፣ አእምሮንና ነፍስን ለመለኮታዊው አገልግሎት ማሠልጠን ነው፡፡ ይህ እስከ ዘላለማዊው ህይወት የሚዘልቅ ትምህርት ነው፡፡-Christ’s Object Lessons, p. 330. ChSAmh 311.1
የዕደ ጥበብ ሰዎች፣ የሕግ ባለሙያዎች፣ ነጋዴዎችና የልዩ ልዩ ሙያ ባለቤቶች ራሳቸውን እያስተማሩ ብቁ ባለሙያ የሚያደርጋቸውን ትምህርት ይቀስማሉ፡፡ ታዲያ የወንጌል ሥራ ባለሙያዎች ሆነው በአምላካዊው አገልግሎት ተሳታፊ የሆኑ የክርስቶስ ተከታዮች ስለ ተቀጠሩበት ሥራ ዕውቀትና ብልሃት የሌላቸውከእነርሱ ያነሰ አስተሳሰብ ባለቤት ሊሆኑ ይገባል? የዘላለማዊ ሕይወት ባለቤት የሚያደርገው፣ ከሁሉ በላይ የሆነው ታላቁ አገልግሎት ከማንኛውም ምድራዊ ሥራና ሙያ ጎን አጽንኦት ሊሰጠው አይችልም፡፡ ነፍሳትን ወደ የሱስ ለመምራት በቅድሚያ በሰብዓዊው ተፈጥሮና አእምሮ ዙሪያ ስነ ልቡናዊ ጥናትና ዕውቀት ሊኖር ይገባል፡፡ በታላቁ የእውነት ርዕሰ ጉዳይ Fሪያ ወንዶችንና ሴቶችን እንዴት ማግባባት እንደሚኖርብን ለማወቅ ጥንቃቄ የተሞላው ሰፊ አስተሳሰብና ከልብ የመነጨ ጽኑ ጸሎት መደረግ ይኖርበታል፡፡ Testimonies, vol. 4, p. 67. ChSAmh 311.2