የክርስቲያን አገልግሎት
የትወናው የመጨረሻ ገቢር
የሰውን ሥልጣን በማግዘፍ የእግዚአብሔር ሕግ የሆነውን መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ቅዳሜ በእሁድ ሰብዓዊ ሕግ ለመተካት የሚደረገው እንቅስቃሴ የትወናው የመጨረሻ አካል ነው፡፡ ሰባተኛውን ቀን በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ለመተካት የሚደረገው እቅድ ዓለማቀፋዊ በሕሪ ሲላበስ እግዚአብሔር ምድርን ክፉኛ ሊያናውጥ ራሱን በንጉሣዊ ክብር በመግለጥ ይነሳል፡፡ የምድርን ነዋሪዎች ስለ እርክስናቸው ሊቀጣ ይገለጣል፡፡ ምድርም ያፈሰሰችውን ደም ገልጣ ታሳያለች እንጂ ከዚህ በኋላ የገደለቻቸውን አትሸሽግም፡፡--Testimonies, vol. 7, p. 14. ChSAmh 220.2
አሜሪካ እንደ አገር የተቋቋመችበት መርኅ ፈርሶ የእሁድ ሕግ በመንግሥት አማካይነት ሲወጣ የፕሮቴስታንቱ ዓለም ከጳጳሳዊው ሥርዓት ጋር እጅ ለእጅ ይያያዛል፡፡ ይህ ሕብረት አጋጣሚውን በጉጉት ሲጠባበቅ ለነበረው _ ማናለብኝ ጨካኝ ሥርዓት ሕይወት በመስጠት ዳግመኛ እንዲያንሰራራ ከማድረግ ውጪ የሚፈይደው አይኖርም፡፡-Testimonies, vol 5, p. 712. ChSAmh 220.3
የእግዚአብሔርን ሕግ በመጣስ በጳጳሳዊው ተቋም የሚወጣው አስገዳጅ ሕግ አሜሪካ ሙሉ ለሙሉ ራሷን ከአምላካዊው ጽድቅ ውጪ እንድታደርግ መንስኤ ይሆናል፡፡ ፕሮቴስታንቶች በእነርሱና በጳጳሳዊው ሥርዓት መካከል ያለውን ገደል አልፈው እጃቸውን ዘርግተው ከሮም ኃይል ጋር ሲያያዙናሰዎች ከሙታን መንፈስ ጋር ግንኙነት መፍጠር ይችላሉ ከሚል በጥልቅ ገደል ካለ አስተምህሮ (ስፕሪቹዋሊዝም) አራማጆች ጋር ሲጨባበጡ--አሜሪካ በሦስትዮሹ ሕብረት ተጽእኖ ስር ትወድቃለች፡፡ የፕሮቴስታንትና ሪፑብሊካን አገርነቷ አክትሞ በእያንዳንዱ ሐı መንግሥቷ ላይ የሰፈረውን መርኅ የምቃወም ትሆናለች፡፡ ለጳጳሳዊው _ ሥርዓት የሐሰትና ከእውነት የራቀ አስተምህሮና መንሰራፋት ያላትን ሁሉ ትሰጣለች፡፡ ይv ሲሆን ሰይጣን ድንቃድንቆችና ተአምራት የሚሠራበት መጨረሻው ሰዓት ላይ መድረሳችንን እናውቃለን፡፡-Testimonies, vol. 5, p. 451. ChSAmh 221.1
እንደ ቀደሙት ደቀ መዛሙርት ሰዎች በማይኖሩባቸው ብቸኛ ስፍራዎች ለመሰደድ የምንገደድበት ጊዜ እሩቅ አይደለም፡፡ የየሩሳሌም በሮም ሠራዊት መከበብ የይሁዳ ክርስቲያኖች ስፍራውን ለቅቀው እንዲወጡ ምልክት እንደ ነበርጳጳሳዊው ሥርዓት አስገዳጁን የእሁድ ቀን አዋጅ ለማውጣት በማሰብ ከአሜሪካ ጋር በተቀናጀ ኃይል የሚያደርገው እንቅስቃሴ ለእኛም የማስጠንቀቂያ ደወል ይሆነናል፡፡ በዚህን ወቅት ትላልቅ ከተሞችን ለቅቀን በመውጣት፣ ከትናንሾቹም እየራቅን ኑሮአችንን በተራራማ ስፍራዎች እናደርጋለን፡፡— Testimonies, vol. 5, pp. 464, 465. ChSAmh 221.2