የክርስቲያን አገልግሎት

145/246

ስደት…መሰረታዊ ነገር

የተልዕኮአቸውን ብርቱ ኃላፊነት የተገነዘቡ በመሆናቸው ስደት በየአቅጣቸው ሲበታትናቸው በወንጌላዊ ቅንአት ተሞልተው ወደ ፊት ገሰገሱ፡፡ በአምላካዊው ቃል ረሐብ ለተመታው ዓለም የሚበጅ የሕይውት እንጀራ በእጃቸው እንዳለ የሚያውቁት እነዚህ ሕዘቦች ይህን እንጀራ ለሚያሻቸው ሁሉ ይቆርሱ ዘንድ የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይላቸው ነበር፡፡ The Acts of the Apostles, p. 106. ChSAmh 219.1

ፈታኝ እውነቶች በንቀት ቢስተዋሉ እንኳ ከፊት ለፊት ተሰላፊ የምርመራና የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮች እንዲሆኑ እግዚአብሔር ይጠቀምባቸዋል፡፡ የሕዝቡ አእምሮ የተነሳሳ ሊሆን የግድ ነው፡፡ እያንዳንዱ ውዝግብ፣ ነቀፌታ፣ ዘለፋና ሐሜት ሰዎችን በማነሳሳት፣ አንቀላፍቶ ይቀር የነበረው አእምሮ የሚቀሰቀስበት አምላካዊ መንገድ ነው፡፡Testimonies, vol. 5, p. 453. ChSAmh 219.2