የክርስቲያን አገልግሎት

144/246

ምዕራፍ 14—የኃይማኖት ነጻነት

ለዘመኑ ገጣሚ የሆነው ጸሎት

ዳዊት “እግዚአብሔር ሆይ ሕግህ እየተጣሰ ነውና፤ ጊዜው አንተ የምትሠራበት ነው” በማለት ጸልዮአል፡፡ ይህ ጸሎት ከመቼውም ይልቅ ለዚህ ዘመን ገጣሚ ነው፡፡ ዓለም ከትክክለኛው አምላካዊ መንገድ አፈንግጦ መውጣቱን ተከትሎ የሚገኝበት ሐገ ዐልባ ሁናቴ በሰብዓዊው ልብ ውስጥ የሚለቀው የሽብር ስሜት ለታላቁ ንጉሥ ታማኝ የሆኑት ሁሉ ተሐድሶ የማምጣት ሥራ እንዲሠሩ የሚመራ ነው፡፡ የጳጳሳዊው ሥርዓት ኃይል የእግዚአብሔርን ሰንበት በሌላ ቀን አጭበርብሮ በመተካት አምላካዊውን ሕግ ለመለወጥ ያስባል፡፡ መላው የክርስትና _ ዓለም እውነተኛውን ሰንበት ረግጦ ሐሰተኛውን ቀን በቅድስና እየጠበቀ ይገኛል... በክርስቶስና በመላእክቱ እንዲሁም በሰይጣንና በመላእክቱ መካከል የሚደረገው የመጨረሻው ታላቁ ተጋድሎ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ማዕከል ያደረገ በመሆኑ ለመላው ዓለም ወሳኝ ነው... በተቀደሰው የአገልግሎት ወንበር ላይ በኃላፊነት ተቀመጡ ሰዎች ራሳቸው ሰንበትን ችላ በማለትና በመናቅ ብቻ ሳይወሰኑ ለሰብዓዊው ወግና ልማድ አፈ ቀላጤ ሆነው በመቆም ሕዝቡ በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን እንዲያርፍ ይወተውታሉ፡፡ እሑድ በቅድስና ባለመከበሩ እግዚአብሔር _ ስላልተደሰተ ምድርን— በማዕበል፣ በአውሎ ንፋስ፣ በጎርፍ፣ በመሬት መንቀጥቀጥና በሰደድ እሳት ቁጣ እየመታት እንደሆነ ለመናገር ይሞክራሉ፡፡ አንዱ ውድመት ሌላውን እየተከተለ አሰቃቂዎቹ ተፈጥሮአዊ ክስተቶች ይበልጥ እየጨመሩና እየተስፋፉ ይሄዳሉ፡፡ የእግዚአብሔርን ሕግ ያፈረሱ ሰዎች ለአምላካዊው ቁጣ አራተኛውን ትእዛዝ የሚጠብቁትን ጥቂት ሕዝቦች ተጠያቂ በማድረግ ጣቶቻቸውን በእነርሱ ላይ ይቀስራሉ፡፡ ይህ የሐሰት ክስ ሰይጣን ያልተጠራጠሩትን ነፍሳት የሚያጠምድበት ዓይነተኛ መንገድ ነው፡፡-Southern Watchman, June 28, 1904 ChSAmh 213.1

ሕዝቦቻችን ይህን ማሳሰቢያ እርባና እንደሌለው አነስተኛ ነገር ሲቆጥሩት ቢቆዩም ለውጥ ግን ይመጣል፡፡ የእግዚአብሔርን ሕግ የሚጠብቁ ሕዝቦችን ስመ ጥር የሚያደርጉ አንዳንድ እንቅስቃሴዎች በክርስትናው ዓለም እየተተገበሩ ይገኛሉ፡፡ የእግዚአብሔርን እውነት ከሰብዓዊው በመነጩ ንድፈ ሐሳቦችና የሐሰት ይማኖታዊ አስተምህሮዎች የመተካት እንቅስቃሴ ባለማቋረጥ እየተተገበረ ይገኛል፡፡ ለእግዚአብሔር ታማኝ የሚሆነውን ሕሊና በባርነት ስር የማስገዛት እንቅስቃሴዎች በመተግበር ላይ ናቸው፡፡ ሕግ አውጪ ኃይላት ከእግዚአብሔር ሕዝቦች በተቃራኒ ይሰለፋሉ፡፡ እያንዳንዱም ነፍስ ይፈተናል፡፡- Testimonies, vol. 5, p. 546. ChSAmh 214.1

cዎች ከእግዚአብሔር ሕግ ጋር ቀጥተኛ ተጻራሪነት ያላቸው ሕጎች እንዲገኑና በጥብቅ እንዲተገበሩ ያደርጋሉ፡፡ “እግዚአብሔር እንዲv ይላል” በግልጽ ከተቀመጠው አምላካዊ ትእዛዝ አፈንግጠው የገዛ ትእዛዞቻቸውን ተግባራዊ የማድረግ ቅንአት ያድርባቸዋል፡፡ ለተጭበረበረው የሐሰት እረፍት ቀን ብርቱ _ አጽንኦት በመስጠትና ዕለቱን በማግነን ሰዎች የእግዚአብሔር ጸባይ ቅጂ ለሆነው አምላካዊው ሕግ ታማኝ እንዳይሆኑ የማስገደድ ምኞት ያድርባቸዋል፡፡ ምንም እንኳ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ንጹሐን ቢሆኑም ነገር ግን በሰይጣን በሚመሩ hፉ ምኞት ባደረባቸው አክራሪ ኃይማኖተኞች እጅ ሥቃይና ውርደት ይደርስባቸዋል፡፡ Testimonies, vol. 9, p. 229. ChSAmh 214.2

ግብራቸው ከሰማይ ጋር ሕብረት ያለውጸባያቸው የበጉ እንደሆነ አፋቸውን ሞልተው የሚናገሩ የኃይማኖት ኃይላት ልባቸው የዘንዶ፣ በሰይጣን የተነሳሱና በእርሱ ቁጥጥር ስር የዋሉ መሆናቸውን ሥራቸው ይመሰክራል፡፡ _ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰንበትን ቅዱስ አድርገው በመጠበቃቸው ብቻ አሳዳጅ እጆች የሚከታተሏቸው ጊዜ እየመጣ ነው... ሆኖም የእግዚአብሔር ሕዝቦች ለአምላካቸው ጸንተው ሊቆሙ ይገባል፡፡ ጌታየአማልክቶች አምላክ መሆኑን በግልጽ በማሳየት ስለ እነርሱ ይሠራል፡፡ --Testimonies, vol. 9, pp. 229, 230. ChSAmh 215.1

ሰይጣን ሰብዓዊውን ልብ በመሣሪያነት ተጠቅሞ እያንዳንዱን ክብረ ነክ ድርጊት፣ ዘለፋና የጭካኔ ተግባር በየሱስ ተከታዮች ላይ እንዲፈጽሙ ሲያነሳሳቸው ኖሮአል፡፡ ከእግዚአብሔር ሕግ ጋር በጠላትነት የሚኖረው የሥጋ ልብ ለተእዛዛቱ ተገዢ መሆን ስለማይችል ይህ ድርጊት ዳግም ገቢራዊ የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል፡፡ በሐዋርያት ዘመን ከነበረችው ይልቅ የዛሬዋ ዓለም ለክርስቶስ መርኅዎች ስምሙ መሆኗ አብቅቶአል፡፡ “ስቀለው! ስቀለው!” ብለው እንዲጮኹ ያነሳሳቸውና ደቀ መዛሙርቱን ያሳደደው ያው የጥላቻ መንፈስ ዛሬም በማይታዘዙ ልጆች ውስጥ ይሠራል፡፡ ታሪክ የጨለማው ዘመን በሚል ስያሜ የሚጠራውን—ወንዶችና ሴቶች ወደ እስር የተወረወሩበት፣ በግዞት የማቀቁበትና የሞቱበት--የ ስሚትፊልድን እሳት ባቀጣጠለው ባርቶሎሜላይ የታቀደው “የምርመራ” ግርፋትንና ጭፍጨፋን የመራውና ዛሬም በጥላቻና ተንኮል ጉልበት ተወጥሮ በማይለወጥ ልብ ውስጥ እየሠራ ያለው ያው መንፈስ ነው፡፡ የእውነት ታሪክትክክል በሆነውና በተሳሳተው መሃል ያለውን የእስካሁኑን ተጋድሎ መዝግቦ ይዞአል፡፡ ወንጌል--በተቃውሞ፣ በአደገኛ ሁናቴ፣ በእጦትና በሥቃይ መሃል --እስካሁን ለዓለም እየታወጀና ወደ ፊት እየገሰገሰ ይገኛል፡፡The Acts of the Apostles, pp. 84, 85. ChSAmh 215.2

ትሩፋኗ ቤተ hርስቲያን ታላቅ የፈተናና የሥቃይ ወቅት ይገጥማታል፡፡የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁና የየሱስ እምነት ያላቸው ሕዝቦች የዘንዶውና ሰራዊቱ ቁጣ በላያቸው እንደሆነ ይሰማቸዋል፡፡ ሰይጣን አመጻ ያደረገችውን ቤተ ክርስቲያን በቁጥጥሩ ስር በማዋሉ መላውን ዓለም ተገዢው አድርጎ ቢቆጥርም ነገር ግን ገናናነቱን እየተቃወሙ የሚገኙ ጥቂት ሕዝቦች አሉ፡፡ እነዚህን ሕዝቦች ከምድር ገጽ ማጥፋት ቢችል ኖሮ ያገኘው ድል የተሟላ በሆነለት ነበር፡፡ ሰይጣን የአሕዛብ መንግሥታት እስራኤልን እንዲያጠፉ ተጽእኖ እንዳሳደረባቸው ሁሉ በተመሳሳይ የእግዚአብሔርን ሕዝቦች ለማጥፋት በቅርቡ የምድር ኃይላትን ያናውጣል፡፡ ሁሉም ሰው የእግዚአብሔርን ሕግ ጥሶ ለሰብዓዊ አዋጆች እንዲታዘዝ ይጠየቃል፡፡ ለእግዚአብሔር እውነተኛ በመሆን እርሱን መታዘዝ በሚመርጡ ላይ “ወላጆቻቸው፣ ወንድሞቻቸው፣ዘመዶቻቸውና 3ደኞቻቸው እንኳ ሳይቀሩ” ክህደት ይፈጽሙባቸዋል፡፡ Testimonies, vol. 9, p. 231. ChSAmh 216.1

ፈተና ወደ እያንዳንዱ ነፍስ የሚመጣበት ጊዜ እሩቅ አይደለም፡፡ በተሳሳተው የሰንበት ቀን እንድናርፍ ጫና ይደርስብናል፡፡ ፍልሚያው በእግዚአብሔርና በሰዎች ትእዛዛት መካከል ይሆናል፡፡ ራሳቸውን ደረጃ በደረጃ ለዓለማዊው ፍላጎት በማስገዛት ከዚህ ምድር ወግና ልማድ ጋር ያስማሙ—ፌዝ፣ ስላቅ፣ በእስር የመውደቅ አደጋንና ሞትን በመጋፈጥ ፋንታ ይህን በሚፈጽሙ ኃይላት ቁጥጥር ስር ይውላሉ፡፡ ወርቅ ከጉድፍ በሚለይበት በዚያን ወቅት... ለአስደናቂ ችሎታቸው አድናቆታችንን የቸርናቸው አያሌ ኮከቦች ጨለማ ወስጥ ይወድቃሉ፡፡ የhርስቶስን ጽድቅ ያልለበሱ ነገር ግን የቤተ መቅደሱ ማስዋቢያ ጌጦች አድርገን እንቆጥራቸው የነበሩ በራሳቸው የሐፍረት ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ይወድቃሉ፡፡ Prophets and Kings, p. 188. ChSAmh 216.2

በሰብዓዊው ሕግ ዋጋ ቢስ በተደረገው የእግዚአብሔር ሕግ ጎን ያለማቋረጥ በቆምን መጠን የመታሰር፣ የንብረት መጥፋት ብሎም ሕይወት እስከ ማጣት የሚደርስ አስከፊ ሁናቴ ከፊታችን እንደሚኖር ይጠበቃል፡፡Testimonies, vol. 5, p. 712. ChSAmh 216.3

ጊዜው በጥድፊያ እየገሰገሰ እንደመሆኑ የhርስቶስ ሥቃይ ተካፋይ መሆን ምን ማለት እንደሆነ ለእውነት በመቆም ተሞክሮ ውስጥ ያለፉ ብቻ ያውቁታል፡፡ የቀረው የመሥሪያ ጊዜ አጭር መሆኑን የሚመለከተው ታላቁ ጨቋኝ በቅርቡ በሰብዓዊው ፍጡር ላይ መንሰራፋቱ አክትሞ መላ ኃይሉን እንደሚያጣ ስለሚያውቅ በሰብዓዊው ፍጡር ላይ ጥፋት ለማድረስ በሙሉ አቅሙ እየሠራ ይገኛል፡፡ አምላካዊው እውነት፣ ፍትሕና ርትd-በባእድ አምልኮምና በተሳሳተ አስተምህሮ ተረግጧል፡፡ የእያንዳንዱ የእውነት ባላንጣ ኃይል እየበረታና ተቀባይነት እያገኘ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ Southern Watchman, Oct. 31, 1905. ChSAmh 217.1

ቤተ ክርስቲያን በሰላማዊና የብልጽግና ዘመኖቿ ያልሠራችውን ሥራ እጅግ ተስፋ አስቆራጭ፣ ተቃዋሚና ቀውስ የበዛባቸው ከልካይ ሁናቴዎች ውስጥ ሆና መሥራት ይኖርባታል፡፡ የአምላካዊውን የማስጠንቀቂያ ድምጽ ከመሰማት ያገደው ወይም ከመግለጽ እንዲቆጠብ ያደረገው ከዓለም ጋር የተመቻቸ ሁኔታ በብርቱ የጠላት ተቃውሞ ወቅት በይፋ መቅረቡ የግድ ይሆናል፡፡ በዚያን ወቅት ሥራው ያለማቋረጥ ዘገምተኛ እንዲሆን ተጽእኖ ያሳደረውጥልቅ እምነት የሌለው ወግ አጥባቂ ክፍል እምነቱን ክዶ ረዘም ላሉ ጊዜያቶች የድጋፍ አዝማሚያ ያሳይ ወደ ነበረው የጠላት ጎራ ጎን ይሰለፋል፡፡ ከሐዲዎች አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ ጭቆናና የግፍ ተግባራት በቀድሞ ወንድሞቻቸው ላይ በመፈጸም በእነርሱ ላይ ያላቸውን ንዴትና ቁጣ የሚገልጽ መራራ ጠላትነት ያሳያሉ፡፡ እነሆ ይህ ተግባራዊ የሚሆንበት ቀን ከፊታችን ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባላት እያንዳንዳቸው በግል ይፈተናሉ—የእምነታቸውም ጥንካሬ ይታያል፡፡ ለእውነት ምስክር እንዲሆኑ በሚያደርጓቸው አጣብቂኝ ሁናቴዎች ውስጥ ይወድቃሉ፡፡ ብዙዎች በተናጥል ወይም ለብቻቸው በሸንጎ ወይም በፍትሕ አዳራሾች ፊት እንዲናገሩ ይጠራሉ፡፡ እንዲህ ያለው አስቸኳይ ክስተት ሲፈጠር ሊረዳቸው ይችል በነበረ ተሞክሮ ውስጥ ለማለፍ ችላ ካሉያለ አንዳች ጥቅም በከንቱ በባከኑት መልካም ዕድሎችና ችላ በተባሉ ልዩ መብቶችና ጥቅሞች ነፍሳቸው በጸጸት ስሜት ውስጥ ትወድቃለች፡፡Testimonies, vol. 5, p. 463. ChSAmh 217.2

የፕሮቴስታንቱ ዓለም እንደ መርዶክዮስ በደጃፍ ሆነው ሰንበትን የሚጠብቁ ጥቂት አኻዝ ያላቸውን ወገኖች እየተመለከተ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝቦች በጸባያቸውም ሆነ ባሕሪያቸው ለአምላካዊው ሕግ የከበረ ዋጋ መስጠታቸው፤ ጌታን መፍራታቸውን ትተው ሰንበቱን ለሚጥሱ የማያቋርጥ ግሳጼ ነው፡፡ ሁከት ፈጣሪው ሰርጎ ገብ በሆነ መንገድ መወገድ ይኖርበታል፡፡--Testimonies, vol. 5, p. 450. ChSAmh 218.1

ሰይጣን ሰብዓዊውን ወግና ልማድ _ ለመቀበል በሚቃወመው በማስተዋል በሚላለሰው ትሑት መንጋ ላይ ቁጣውን የሚገልጽበት ጊዜ ቅርብ ነው፡፡ ምድራዊ ሥልጣንና ዝና ያላቸው ሰዎች በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ለማሴር ሕገ-ጠል እና ክፉ የሆነውን አካል ይቀላቀላሉ፡፡ ሐብት፣ ዕውቀትና ትምህርት የሚፈጥሩት ቅንጅት እነዚህን ሰዎች በንቀት እንዲጀቦኑ ያደርጋቸዋል፡፡ የቤተ hርስቲያን መሪዎችን፣ አገልጋዮችንና አባላትን የሚያሳድዱ በእነርሱ ላይ ያሴራሉ፡፡ በትዕቢት በተሞላ አንደበትና ብዕር በሚያደርሱባቸው ማስፈራራት እምነታቸውን ገርስሰው ለመጣል ይመኛሉ፡፡ የሐሰት ገጽታ በተላበሰ ቁጡ አቀራረብ ጥልቅ የሆነውን የሕዝብ ስሜት ይበጠብጣሉ፡፡ “ተብሎ ተጽፎአልና” የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሰንበት የሚቃረን አምላካዊ ቃል የሌላቸው እነዚህ ሰዎች ይህን ጉድለት ሊተካላቸው የሚችል ጨቋኝ ሕጎች ያወጣሉ፡፡ ሕግ አውጪዎች በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነትና ድጋፍ ለማሰባሰብ--የእሑድ ቀን አምልኮ ተፈጻሚነት እንዲያገኝ ያነሳሳሉ... በእውነትና በሐሰት መካከል የሚካሄደው ታላቁ የመጨረሻ ተቃርኖ በዚህ ውጊያ ወቅት ገቢራዊ ይሆናል፡፡-- Testimonies, vol. 5, pp. 450, 451. ChSAmh 218.2