የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

138/349

ኃይለኛ ለሆነው ድርጅታዊ ሥራ ስጋቶች

የእግዚአብሔር ሥራ ባለው ስፋቱ ሁሉ አንድ ስለሆነ በሁሉም ዘርፎች ተመሳሳይ የሆኑ መርሆዎች መቆጣጠር አለባቸው፣ ተመሳሳይ የሆነ መንፈስ መታየት አለበት፡፡ የሚስዮናዊ ስራን ማህተም መያዝ አለበት፡፡ የሥራው እያንዳንዱ ክፍል ከሁሉም የወንጌል መስኮች ጋር የተገናኘ ስለሆነ አንዱን የስራ ክፍል የሚቆጣጠረው መንፈስ በሁሉም የስራ ዘርፎች ይታያል፡፡ ከሰራተኞች መካከል የተወሰኑት ከፍተኛ ደሞዝ የሚከፈላቸው ከሆነ በሥራው የተለያዩ ዘርፎች ከፍተኛ ደሞዝ እንዲከፈላቸው የሚጠይቁ ሌሎች ሰዎች አሉ፣ ከዚህ የተነሳ ራስን መስዋዕት የማድረግ መንፈስ ቀስ በቀስ ከእይታ ይጠፋል፡፡ ሌሎች ተቋሞችና ኮንፍራንሶች ያንኑ መንፈስ ይይዛሉ፣ እግዚአብሔር ለራስ ወዳድነት በፍጹም እውቅና ስለማይሰጥ የእርሱ መልካም ፈቃድ ከእነርሱ ይወገዳል፡፡ በመሆኑም ኃይለኛ የሆነው ሥራችን ወደ ፍጻሜ ይመጣል፡፡ ሥራው ወደ ፊት መቀጠል የሚችለው በማያቋርጥ መስዋዕትነት ብቻ ነው፡፡{2SM 178.1} Amh2SM 178.1

እግዚአብሔር የእያንዳንዱን ነፍስ እምነት ይፈትናል፡፡ ክርስቶስ ዘላለማዊ በሆነ መስዋዕትነት ገዝቶናል፡፡ እርሱ ሀብታም ቢሆንም በእርሱ ድህነት ዘላለማዊ ሀብት ባለቤቶች እንድንሆን ስለ እኛ ደሃ ሆነ፡፡ እኛ ያለን ችሎታና እውቀት ሁሉ ለእርሱ አገልግሎት እንድንጠቀም ከጌታ በተውሶ የተሰጠን ነው፡፡ በእርሱ መስዋዕትነት ከክርስቶስ ጋር ተካፋዮች መሆን ለእኛ መልካም እድል ነው፡፡ {2SM 178.2} Amh2SM 178.2