የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

136/349

የማያምኑ ሰዎች ተቀጠሩ

በሞሪያ ተራራ ላይ የሚገነባውን ቤተ መቅደስ እንዲቆጣጠር ሰለሞን የፈለገው የሥራ ሀላፊ ከእነዚህ ከሃዲዎች መካከል ነበር፡፡ የዚህን የተቀደሰ ሕንጻ እያንዳንዱን ክፍል አሰራር በተመለከተ ጥቃቅን መመሪያዎች ሳይቀሩ ለንጉሱ በጽሁፍ ተሰጥቶት ነበር፣ ንጉሱም የተፈለገውን ሥራ በትክክል የሚሰሩ የተለየ ሙያ ያላቸውን የተቀደሱ ረዳቶች እንዲሰጥ በእምነት ወደ እግዚአብሔር መመልከት ይችል ነበር፡፡ ነገር ግን ሰለሞን በእግዚአብሔር ላይ እምነቱን የሚገልጽበትን ይህን መልካም አጋጣሚ ማየት አቃተው፡፡ ወደ ጢሮስ ንጉስ እንዲህ በማለት ላከ፣ «አሁንም አባቴ ዳዊት ካዘጋጃቸው በእኔ ዘንድ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ካሉት ብልሃተኞች ጋር የሚሆን፥ ወርቁንና ብሩን፥ ናሱንና ብረቱን፥ ሐምራዊውንና ቀዩን ሰማያዊውንም ግምጃ የሚሠራ፥ ቅርጽንም የሚያውቅ ብልሃተኛ ሰው ላክልኝ (2ኛ ዜና 2፡7)፡፡ {2SM 175.1} Amh2SM 175.1

የፌንቃውያን ንጉስ ኪራምአቢን በመላክ ለንጉሱ ጥያቄ መልስ ሰጠ፣ «አሁንም ከብልሃተኞችህ ጋር ከጌታዬም ከአባትህ ከዳዊት ብልሃተኞች ጋር ይሆን ዘንድ ኪራምአቢ የሚባል ብልሃተኛና አስተዋይ ሰው ሰድጄልሃለሁ። እናቱ ከዳን ልጆች ናት፥ አባቱም የጢሮስ ሰው ነው ወርቁንና ብሩንም፥ ናሱንና ብረቱን፥ ድንጋይንና እንጨቱን፥ ሐምራዊውንና ሰማያዊውን ቀዩንም ግምጃ፥ ጥሩውንም በፍታ ይሠራ ዘንድ፥ ቅርጽም ሌላም ነገር ሁሉ ያደርግ ዘንድ ያውቃል» (2ኛ ዜና 2፡13፣14)፡፡ ይህ ከፍተኛ ችሎታ የነበረው ሰው፣ ኪራምአቢ፣ በእነቱ በኩል ከመቶ አመታት በፊት ለቤተ መቅደሱ ግንባታ እግዚአብሔር የተለየ ጥበብ የሰጠው የኤልያብ ተወላጅ ነበር፡፡ በመሆኑም በሰለሞን የሰራተኞች ድርጅት ላይ በመሪነት ከተለመደው ውጭ የሆነ ችሎታ ስላለው ትልቅ ደሞዝ የሚጠይቅ ያልተቀደሰ ሰው ተሹሟል፡፡ {2SM 175.2} Amh2SM 175.2

የኪራምአቢ ጥረቶች ለእግዚአብሔር ከፍተኛ አገልግሎት ለመስጠት ከመፈለግ የመነጩ አልነበሩም፡፡ የዚህን ዓለም አምላክ፣ ገንዘብን የሚያመልክ ሰው ነበር፡፡ ለከፍተኛ ደሞዝ ሲስገበገብ እንደታየው ሁሉ ሁለመናው በራስ ወዳድነት መርሆዎች የተሞላ ነበር፡፡ ቀስ በቀስ እነዚህ የስህተት መርሆዎች አብረውት በሚሰሩት ዘንድም መንጸባረቅ ጀመሩ፡፡ ከቀን ወደ ቀን ከእርሱ ጋር አብረው ሲሰሩና የእነርሱን ደሞዝ ከእርሱ ደሞዝ ጋር ማነጻጸር ሲጀምሩ የሥራቸውን የተቀደሰ ባሕርይ ማየት አቃታቸውና በእነርሱና በእርሱ ደሞዝ ልዩነት ላይ ማተኮር ጀመሩ፡፡ ቀስ በቀስ ራስን የመካድ መንፈስ አጡና የምኞት መንፈስን አስተናገዱ፡፡ የዚህ ውጤት ከፍተኛ ደሞዝ መጠየቅ ሲሆን የጠየቁት ተሰጥቷቸዋል፡፡ {2SM 175.3} Amh2SM 175.3

ይህን የመስገብገብ መንፈስ ያለውን ሰው ከመቅጠር የተነሳ ስራ ላይ የዋለው ክፉ ተጽእኖ ወደ ሁሉም የእግዚአብሔር አገልግሎት ዘርፎች ተዛመተና በመላው የሰለሞን መንግሥት ውስጥ ተስፋፋ፡፡ ከፍተኛ ደሞዝ ከመጠየቃቸው የተነሳ የተሰጠው ክፍያ ብዙዎች ቅንጦትን እንዲለማመዱና ገንዘብን ያለ አግባብ እንዲጠቀሙ እድል ሰጣቸው፡፡ ሩቅ ቦታ መድረስ የሚችሉ ውጤቶች ያሉአቸው እነዚህ ተጽእኖዎች በአንድ ወቅት ከሟች ሰዎች መካከል እጅግ ጠቢብ ተብሎ ለሚታወቀው ሰው አሰቃቂ ክህደት ዋና መንስኤዎች እንደሆኑ ማየት ይቻላል፡፡ በክህደቱ ንጉሱ ብቻውን አልነበረም፡፡ አባካኝነትና ሙስና በሁሉም በኩል ይታይ ነበር፡፡ ድሆች በሀብታሞች ተጨቁነው ነበር፤ በእግዚአብሔር አገልግሎት ውስጥ ራስን መስዋዕት የማድረግ መንፈስ በአብዛኛው ጠፍቶ ነበር፡፡ {2SM 176.1} Amh2SM 176.1

እዚህ ላይ ዛሬ ላለው ለእግዚአብሔር ሕዝብ የሚሆን እጅግ ጠቃሚ የሆነ ትምህርት አለ፡፡ ይህ ትምህርት ብዙዎች ለመማር ዘገምተኛ የሆኑበት ትምህርት ነው፡፡ በዓለም ውስጥ የመመኘት መንፈስ፣ ከፍተኛ ስልጣንና ከፍተኛ ደሞዝ የመፈለግ መንፈስ በዝቶአል፡፡ በቀድሞ ዘመን የነበረው ራስን የመካድና መስዋዕት የማድረግ መንፈስ እምብዛም አይታይም፡፡ ነገር ግን እውነተኛ የኢየሱስ ተከታይ የሆነ ሰውን መቀስቀስ የሚችለው መንፈስ ይህ ብቻ ነው፡፡ ብዙዎች ለመማር ዘገምተኛ የሆኑበት እጅግ አስፈላጊ የሆነ ጠቃሚ የሆነ ትምህርት እዚህ አለ፡፡ የመመኘት መንፈስ፣ ከፍተኛ ስልጣንና ደሞዝ መፈለግ በዓለም በዝቷል፡፡ የድሮ ዘመን ራስን የመካድና መስዋዕት የማድረግ መንፈስ በጣም ቀንሷል፡፡ ነገር ግን እውነተኛ የኢየሱስ ተከታይ የሆነን ሰው የሚያነሳሳው መንፈስ ይህ ብቻ ነው፡፡ መለኮታዊው ጌታችን እንዴት መስራት እንዳለብን ምሳሌ ሰጥቶናል፡፡ እርሱ «በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ» (ማቴ. 4፡19) ብሎ ለጠራቸው ለአገልግሎታቸው ደሞዝ አልሰጣቸውም፡፡ ከእርሱ ጋር ራስን መካድንና መስዋዕትነትን መካፈል ነበረባቸው፡፡ {2SM 176.2} Amh2SM 176.2

የሰራተኞችን አለቃ እንከተላለን የሚሉ እና ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ ሰራተኞች በመሆን በአገልግሎቱ ውስጥ የሚሰማሩ ሰዎች በስራቸው ውስጥ የፍጽምና አምላክ በምድራዊው ቤተ መቅደስ ግንባታ ላይ የጠየቀውን ረቂቅነትንና ችሎታን፣ ብልሃትንና ጥበብን ማምጣት አለባቸው፡፡ በክርስቶስ ምድራዊው አገልግሎት ወቅት እንደነበረው ሁሉ አሁንም ለእግዚአብሔር መሰጠትና የመስዋዕትነት መንፈስ ተቀባይነት ያለው አገልግሎት የመጀመሪያው መስፈርት ሆኖ መታየት አለበት፡፡ እግዚአብሔር በሥራው ውስጥ የራስ ወዳድነት አንድ ክር እንኳን አብሮ እንዲሸመን አይፈልግም፡፡ {2SM 176.3} Amh2SM 176.3