የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

119/349

የእውነት ሰይፍ በሥራ ላይ

ክርስቶስም ደግሞ በቀጥታ ለእያንዳንዱ ክፍል ሰዎች ተናገረ፡፡ በመሰል ሰዎች ላይ የበላይነትን የያዙትን፣ ኃይለኛ ስሜታቸውና አግባብ የሌለው ጥላቻቸው ብዙዎች እንዲሳሳቱ እና እግዚአብሔርን እንዲሳደቡ ያስገደዳቸውን ሁሉ ገሰጻቸው፡፡ የእውነት ሰይፍ በይቅርታዎችና በግምቶች ደንዝዞ ነበር፤ ነገር ግን ክርስቶስ ነገሮችን በትክክለኛ ስማቸው ጠራቸው፡፡ ምሳር ከዛፍ ስር ተቀምጦ ነበር፡፡ የእግዚአብሔርን በግ በእምነት እንደ አዳኛቸው አድርገው ስላልተመለከቱትና ስላልተቀበሉት የአምልኮ ኃይማኖታዊ መልክ የአይሁድን ሕዝብ ሊያድናቸው እንደማይችል አሳያቸው፡፡ {2SM 150.3} Amh2SM 150.3

በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት የዮሐንስን የመሰለ ሥራና መልእክት ይከናወናል፡፡ ጌታ በመረጣቸው መሳሪያዎቹ አማካይነት ለሕዝቡ መልእክቶችን ሲሰጥ ስለነበር እሱ የሚልካቸውን ተግሳጾችና ማስጠንቀቂያዎች ሁሉም መስማት ይችላሉ፡፡ {2SM 150.4} Amh2SM 150.4

የእግዚአብሔር ልጅ አገልግሎቱን ከመጀመሩ በፊት አስቀድሞ የመጣው መልእክት «የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና» (ማቴ. 3፡2) ኃጢአተኖች ንስሃ ግቡ፣ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ንስሃ ግቡ የሚል ነበር፡፡ የእኛ መልእክትም የ«ሰላምና ደህንነት” (1ተሰ. 5፡3) አይሆንም፡፡ በክርስቶስ ቶሎ መምጣት እንደሚያምን ሕዝብ የምንሰራው ሥራና መሸከም ያለብን መልእክት አለን፡፡ ያውም «አምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ» (አሞጽ 4፡12) የሚል ነው፡፡ መመዘኛ ደንብን ማንሳትና የሶስተኛውን መልአክ መልእክት--የእግዚአብሔርን ትዕዛዛትና የኢየሱስን ኃይማኖት መሸከም አለብን፡፡ {2SM 150.5} Amh2SM 150.5