የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

118/349

በሁሉም ክፍሎች የተሰማ

ሁሉም ሊሰሙት ወደ ምድረበዳ ሄዱ፡፡ ያልተማሩ አሳ አጥማጆችና ገበሬዎች በዙሪያው ካሉ አገሮች እና በቅርብና በሩቅ ካሉ ክልሎች መጡ፡፡ የሮም ወታደሮች ከሄሮድስ የወታደር ሰፈር ሊሰሙት መጡ፡፡ የጎሳ መሪዎች ማንኛውንም የረብሻ ወይም የአመጽ መንፈስ ያለውን ነገር ጸጥ ለማሰኘት ሰይፋቸውን በጎናቸው ሻጥ አርገው መጡ፡፡ ስስታሞች የሆኑ ቀራጮች በዙሪያው ካሉ አገሮች መጡ፤ ከምኩራብ ብራና ያለባቸውን ቦርሳዎች የያዙ ካህናት መጡ፡፡ ሁሉም ተመስጠው ሰሙ፤ ሁሉም፣ ፈሪሳውያን፣ ሰዱቃውያንና ቀዝቃዛ የሆኑ፣ ልባቸው የማይነካ የዘመኑ ፌዘኞች፣ ፌዛቸው ከእነርሱ ርቆ፣ የኃጢአተኛነት ስሜት ልባቸውን ወግቶ ከፊቱ ሄዱ፡፡ ክርክሮች አልነበሩም፣ «አንደኛ፣» «ሁለተኛ፣» «ሶስተኛ፣» እየተባሉ በዝርዝር የሚሰጡ በስሱ የተበለቱ ንድፈ ሀሳቦች አልነበሩም፡፡ ነገር ግን አጭር በነበሩ አረፍተ ነገሮች ውስጥ ንጹህ የሆነ በአገሩ የሚታወቅ አንደበተ ርቱዕነት ተገልጾ ነበር፤ እያንዳንዱ ቃል የተሰጡትን ክብደት የነበራቸውን ማስጠንቀቂያዎች እርግጠኛነትና እውነት ተሸክሞ ነበር፡፡ {2SM 148.3} Amh2SM 148.3

የዮሐንስ የማስጠንቀቂያ መልእክት ለነነዌ ሕዝብ ከተሰጠው ማስጠንቀቂያ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነበር፣ «በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች አለ» (ዮናስ 3፡4)፡፡ የነነዌ ሕዝብ ንስሃ ገብተው እግዚአብሔርን ስለጠሩ እግዚአብሔር ለእርሱ ያቀረቡትን ምስጋና ተቀበለ፡፡ ንስሃቸው ትክክለኛ መሆኑን እንዲያሳዩና ከኃጢአታቸው እንዲመለሱ አርባ የመጠበቂያ ዓመታት ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ነነዌ ምስሎችን ወደማምለክዋ ተመለሰች፤ ብርሃን መጥቶ ተቀባይነት ስላጣ ኃጢአቷ ከበፊቱ የበለጠ ጥልቅና ተስፋ ቢስ ሆነ፡፡ {2SM 149.1} Amh2SM 149.1

ዮሐንስ እያንዳንዱን ክፍል ወደ ንስሃ ጠራ፡፡ ፈሪሳውያንን እና ሰዱቃውያንን ከእግዚአብሔር ቁጣ ሽሹ አላቸው፡፡ አብርሃም አባታችን ነው ማለታችሁ ምንም አይጠቅማችሁም አላቸው፡፡ ይህ ንጹህ መርሆዎችንና የባሕርይ ቅድስናን አይሰጣችሁም፡፡ የመስዋዕት አገልግሎቶች የሚወክሉትን የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደውን የእግዚአብሔርን በግ ካላወቃችሁ በቀር መስዋዕቶቹ ምንም አይጠቅሟችሁም፡፡ ከእግዚአብሔር መስፈርቶች ተለይታችሁ የራሳችሁን የተዛቡ ሀሳቦች ትከተላላችሁ፤ የአብርሃም ልጆች የሚያደርጓችሁን እነዚያን ባሕርያት ታጣላችሁ፡፡ {2SM 149.2} Amh2SM 149.2

ምንጩ መስመሩን ተከትሎ እየተጥመዘመዘ ይሄድባቸው የነበሩ የተመሰቃቀሉ አለቶችን በማመልከት እንዲህ አላቸው፣ «ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል» (ማቴ. 3፡9)፡፡ {2SM 149.3} Amh2SM 149.3

መጥምቁ ዮሐንስ ዝቅተኛ ሥራ የነበራቸውንም ሆነ ከፍተኛ ደረጃ የነበራቸውን ሰዎች ኃጢአት በግልጽ በመገሰጽ ተጋፈጠ፡፡ ቢሰሙም ባይሰሙም እውነትን ለነገስታትና ለመሳፍንት ተናገረ፡፡ በግላቸው እና ወደ ግለሰቦቹ እያመለከተ ተናገረ፡፡ ኃይማኖታቸው ንጹህ የሆነ የፈቃድ መታዘዝና ጽድቅ ሳይሆን መልክ ብቻ የያዘ ስለነበረ የምኩራብ ፈሪሳውያንን ገሰጻቸው፡፡ ለሄሮድስ ከሄሮዲያዳ ጋር ስለነበረው ጋብቻ እሷን እንድታገባ ሕጉ አይፈቅድልህም እያለ ተናገረ፡፡ እግዚአብሔር እያንዳንዱን ሰው እንደ ሥራው ስለሚፈርደው ወደፊት ስለሚመጣው ቅጣት ነገረው፡፡. . . {2SM 149.4} Amh2SM 149.4

«ቀራጮችም ደግሞ ሊጠመቁ መጥተው፡- መምህር ሆይ፥ ምን እናድርግ? አሉት” (ሉቃስ 3፡12)፡፡ ቀረጣችሁንና ቀረጥ መሰብሰቢያ ቤታችሁን ተው አላቸውን? እንደዚህ አላለም፡፡ እንዲህ ነበር ያላቸው፣ «ከታዘዘላችሁ አብልጣችሁ አትውሰዱ” (ሉቃስ 3፡13)፡፡ አሁንም ቀራጮች ከነበሩ በእጃቸው ትክክለኛ የሆኑ ክብደቶችንና የእውነት ሚዛኖችን መያዝ ይችሉ ነበር፡፡ አለመታመንን እና ጭቆናን ባመጡ ነገሮች ላይ ተሃድሶ ማካሄድ ይችሉ ነበር፡፡ {2SM 150.1} Amh2SM 150.1

«ጭፍሮችም ደግሞ፡- እኛ ደግሞ ምን እናድርግ? ብለው ይጠይቁት ነበር። እርሱም፦ በማንም ግፍ አትሥሩ ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፥ ደመወዛችሁም ይብቃችሁ አላቸው» (ሉቃስ 3፡14)፡፡ . . . {2SM 150.2} Amh2SM 150.2