የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

114/349

አስርቱን ትዕዛዛት ባለመቀበል

እነዚህ ማህበራት ከመጨረሻ ዘመን ምልክቶች አንዱ ናቸው፡፡ ሰዎች ለመቃጠል በክምር እየታሰሩ ናቸው፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባላት ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን የእነዚህ ማህበራት አባል መሆን ማለት መላውን አስርቱን ትዕዛዛት አለመቀበል ስለሆነ የእነዚህ ማህበራት አባላት ሆነው የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት መጠበቅ አይችሉም፡፡ {2SM 143.3} Amh2SM 143.3

«ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም ኃይልህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው” (ሉቃስ 10፡27)፡፡ እነዚህ ቃላቶች መላውን የሰው ተግባር ያጠቃልላሉ፡፡ እነዚህ ቃላት እያሉ ያሉት መላ ህልውናን፣ አካልን፣ ነፍስንና መንፈስን ለእግዚአብሔር አገልግሎት መቀደስ እንደሚያስፈልግ ነው፡፡ ሰዎች የጎረቤቶቻቸውን የተግባር ነጻነት የሚነፍግ ነገርን ለመደገፍ ቃል እየገቡ እነዚህን ቃላት እንዴት መታዘዝ ይችላሉ? ደሃው የህብረተሰብ ክፍል በተወሰኑ ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር እንዳይሸጥና እንዳይገዛ በመከልከል በፍትሃዊነት ሲታይ የሚገባቸውን ነገር የሚቀማ ውህደት እየፈጠሩ እነዚህን ቃላት እንዴት መታዘዝ ይችላሉ?--Letter 26, 1903. {2SM 143.4} Amh2SM 143.4