የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
ግላዊነታችንን (ልዩነታችንን) ጠብቀን ማቆየት
ሥራችንን በከተማዎች ማዕከል ማድረግ እንደሌለብን ለዓመታት የተለየ ብርሃን ተሰጥቶኛል፡፡ እነዚህን ከተሞች የሚሞላው ግርግርና ምስቅልቅል፣ በሰራተኛ ማህበራትና በሥራ ማቆም አድማ የሚፈጠሩ ሁኔታዎች ለሥራችን ታላቅ እንቅፋት ይሆናሉ፡፡ ሰዎች ልዩ በሆኑ ንግዶች የተሰማሩትን ሰዎች በአንዳንድ ማህበራት ግዞት ሥር ለማምጣት እየፈለጉ ናቸው፡፡ ይህ የእግዚአብሔር እቅድ ሳይሆን እኛ በምንም መንገድ ቢሆን እውቅና መስጠት የሌለብን ኃይል እቅድ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እየተፈጸመ ነው፤ ክፉዎች ራሳቸውን በነዶ እያሰሩ ለመቃጠል እያዘጋጁ ናቸው፡፡ {2SM 143.1} Amh2SM 143.1
አሁን በአደራ የተሰጡንን ችሎታዎች ሁሉ ለዓለም የመጨረሻውን የማስጠንቀቂያ መልእክት ለመስጠት መጠቀም አለብን፡፡ በዚህ ሥራ ግላዊነታችንን ጠብቀን ማቆየት አለብን፡፡ ከምስጢር ማህበራት ወይም ከንግድ ማህበራት ጋር አንድነት መፍጠር የለብንም፡፡ ያለማቋረጥ ከክርስቶስ ትዕዛዝ እየጠበቅን በእግዚአብሔር ነጻ ሆነን መቆም አለብን፡፡ እንቅስቃሴዎቻችን ሁሉ ለእግዚአብሔር ሊፈጸም ያለውን ሥራ አስፈላጊነት በመገንዘብ መሆን አለባቸው፡፡--Testimonies, vol. 7, p. 84 (1902). {2SM 143.2} Amh2SM 143.2