የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

75/349

ያለ በቂ ማስረጃ

አና ፊሊፕስን በተመለከተ በተቻለ መጠን ትንሽ ብቻ ማለት እፈልጋለሁ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ንግግርና መነሳሳቱ አነስተኛ ሲሆን የተሻለ ነው፡፡ «በሽቶ ውስጥ የሞተ ዝንብ” አለ፡፡ ይህ ከመድረሱ በፊት በጉዳዩ ላይ የምንጠብቀውን ነገር በተመለከተ የተሟላ ንባብ ያለውን ደብዳቤ ትቀበላለህ፡፡ ጉዳዩ ጥበብ በጎደለው ሁኔታ ስለተያዘ ልገልጽልህ ከምችለው በላይ አዝናለሁ፡፡ ብዙ የዚህ አይነት እንቅስቃሴዎች ስለሚኖሩ መሪ የሆኑ ወንድሞቻችን በዚህ ጉዳይ ላይ እንዳደረጉት የዚህ ዓይነት ባሕርይ ያላቸውን ነገሮች እየተቀበሉ እውቅና ከሰጡ በልምምዳችን ውስጥ ከታዩት ጠራርገው ከሚወስዱ የአክራሪነት ማዕበሎች መካከል አንዱ ያገኘናል፡፡ እንግዳ የሆኑ ነገሮች ይፈጸማሉ፡፡ ሰይጣን አሁን ሥራውን ጀምሯል፡፡ በእነዚህ ነገሮች ላይ እምነት መጣልና ስለ ትክክለኛ ባሕርያቸው በቂ ማስረጃ ሳይኖር እውቅና በመስጠት ቁጥጥር ያልተደረገባቸውን ልክስክስ አረፍተ ነገሮች መናገር ከሰይጣን መሳሪያዎች አንዱ ነው፡፡ ማንም እንዳይታለል ይህን ጉዳይ በተመለከተ ጌታ ኢየሱስ በእርግጠኝነት በቂ ማስጠንቀቂያዎችን ሰጥቷል፡፡ {2SM 92.1} Amh2SM 92.1

እነዚህን በሚመስሉ ጉዳዮች ላይ በመጠን የምንኖር መሆናችን ይታይ፡፡ ጌታ ቅርብ ነው፡፡ እግዚአብሔር በአና ፊሊፕስ አማካይነት ለሕዝቡ እየተናገረ ለመሆኑ በቂና ግልጽ ማስረጃ ሳይኖራቸው የእሷን ውጤቶች ለቤተ ክርስቲያኖቻችን ሰዎች እንዲደርሱ ባደረጉት ሁኔታ መስራት አያዋጣንም፡፡ አገልጋዮቻችን ጉዳዩ ከእግዚአብሔር መሆኑን በእርግጠኝነት ካላወቁ በስተቀር አንድን ነገር መለኮታዊ መረጃ እንዳለው ነገር በጥድፊያ ወደ ሰዎች ይዘው መሮጥ እግዚአብሔር እንዳያደርጉ የነገራቸውን ነገር ማድረግ ነው፡፡ ለማሳሳት ሆን ተብለው የታቀዱ ብዙ ነገሮች የእውነትን አንዳንድ ምልክቶች ይዘው ይመጣሉ፡፡ እነዚህ ነገሮች እንደ ታላቅ የእግዚአብሔር ኃይል ተደርገው ሲቀመጡ ጠላት ወዲያውኑ ነፍሳትን ከወቅቱ እውነት ለማራቅ ያዘጋጀውን ነገር በዚያ ውስጥ ለመሸመን ዝግጁ ነው፡፡ ... {2SM 92.2} Amh2SM 92.2