የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
ራዕዮች የሚባሉ ነገሮችን ሁሉ ፈትኑ
ከእግዚአብሔር ለሚስስ አና ፊሊፕስ የተሰጡ ራዕዮች በሚል ተጽፎ የተሰራጨውን ነገር ሲስተር ኋይት አጽድቃለች የሚል ዘገባ በስፋት ስለተሰራጨ መናገር ግዴታዬ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ እነዚህን ነገሮች እኔ አላጸደቅኳቸውም፡፡ እነዚህ ነገሮች ሰዎችን በእርግጠኝነት ወደ ስህተት እንደሚመሩ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶኛል፡፡ ወደ ጽንፎች ሊመሩ የሚችሉ አረፍተ ነገሮች በውስጣቸው ተሸምነው ይገኛሉ፣ የሚቀበሉአቸው ሰዎችም የስህተት ድርጊትን እንዲፈጽሙ ይመራሉ፡፡ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በተሰጣቸው ብርሃን መሠረት የበለጠ በጥንቃቄ ቢንቀሳቀሱ መልካም ነው፡፡ እነዚህን ራዕይ የሚባሉ ነገሮችን ከመቀበላቸውና እግዚአብሔር ከሰጣቸው ብርሃን ጋር በተገናኘ ሁኔታ ለሰዎች ከማቅረባቸው በፊት መፈተን አለባቸው፡፡ ሕዝባችን አሰቃቂ ስህተቶችንና ጊዜያቸውን ያልጠበቁ እንቅስቃሴዎችን የማድረግ አደጋ ውስጥ እንዳሉ አያለሁ፡፡ ብቅ እያሉ ስላሉት ስለ እነዚህ ነቢያት እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ «እኔ ሳልልካቸው የሚሮጡ ናቸውና አትመኑአቸው፡፡” {2SM 90.2} Amh2SM 90.2
ነገር ግን የሚያሳዝነኝ ነገር ቢኖር ከወንድሞቻችን መካከል አንዳንዶቹ የአና ፊሊፕስን እንቅስቃሴዎች ከሲስተር ኋይት ምስክርነቶች ጋር በማገናኘት ሁለቱም አንድ እንደሆኑ ለሕዝብ ማቅረባቸው ነው፡፡ ብዙዎች ሁሉንም ከእኔ እንደመጣ አድርገው ተቀብለዋል፡፡ የእነዚህ ዓይነት ምርቶች በትክክለኛ ባሕርያቸው ሲታዩ፣ ውሸቶች ከእግዚአብሔር እንደመጡ እውነቶች ሆነው ሲቀርቡ፣ ግለሰቦች እነዚህን ነገሮች ከእግዚአብሔር የመጡ መልእክቶች እንደሆኑ በማመን ሥራ ላይ ሲያውሉ፣ መለኮታዊ ማረጋገጫ የሌላቸው እንቅስቃሴዎች ይፈጠራሉ፤ በትንቢት መንፈስ ትክክለኛ ሥራ ላይ ጥርጣሬ ያርፋል፡፡ እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሚልካቸው ምስክርነቶች የእነዚህ የውሸት ንግግሮችን መጥፎ ምልክት ይይዛሉ፡፡ እነዚህ ራዕዮች በሕትመት ሥራ አማካይነት ለአመታት በሕዝብ ፊት የቀረቡ ነገሮች ድግግሞሽ ናቸው፤ ነገር ግን ወደ ስህተት የሚመሩ ነገሮች ከእነዚህ ነገሮች ጋር ተቀላቅለዋል፡፡... {2SM 90.3} Amh2SM 90.3
ለወንድሞቻችን የምሰጠው ማስጠንቀቂያ አለኝ፣ ያውም ከክርስቶስ ቀድመው ከመሮጥ ይልቅ መሪያቸውን እንዲከተሉ ነው፡፡ በእነዚህ ጊዜያቶች በዘፈቀደ የሚሰራ ስራ አይኑር፡፡ ሚዛናዊ ያልሆኑ አእምሮዎች አስደናቂ የሆነ ብርሃንን ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደተቀበሉ እንዲያስቡ የሚመሩአቸውን አይነት ጠንካራ አባባሎችን ከመናገር ተጠንቀቁ፡፡ ከእግዚአብሔር መልእክትን ለሰዎች የሚያደርስ ሰው ራሱን በደንብ መቆጣጠር መቻል አለበት፡፡ የድፍረት መንገድ በእምነት መንገድ አጠገብ እንዳለ ሁል ጊዜ በአእምሮው ውስጥ መያዝ አለበት፡፡ Amh2SM 91.1
የሞኝነት ንግግር የሆነ ክፍልን እንደሚጎዳ እርግጠኛ በመሆንና ኃይለኛ የሆነ ፈረስን ለመቆጣጠር እንደሚያስቸግር ሁሉ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ የሆኑ ተጽእኖዎች እንቅስቃሴ ላይ እንዲሆኑ እንደሚያደርግ በመገንዘብ በምንም ሁኔታ ቢሆን የሞኝነት አባባሎችን ማነገር የለበትም፡፡ አንዴ የተለቀቀ ስሜት በተረጋጋ ውሳኔ ላይ የበላይነትን ካገኘ፣ በትክክለኛው መንገድ በመሄድ ላይም ቢሆን፣ ከመጠን በላይ የሆነ ፍጥነት ሊኖር ይችላል፡፡ ከመጠን በላይ የሚሄድ ሰው ከአንድ በበለጠ መንገድ አደጋ ይገጥመዋል፡፡ ከትክክለኛው መንገድ ተነጥሎ ወደ ስህተት መንገድ የሚሄድበት ጊዜ ረዥም አይሆንም፡፡ {2SM 91.1} Amh2SM 91.2
ስሜት በአእምሮ ውሳኔ ላይ የበላይነት እንዲያገኝ አንዴም ቢሆን መፈቀድ የለበትም፡፡ የተፈቀደ ነገርን ከመጠን በላይ መጠቀም አደጋ አለው፣ ያልተፈቀደ ነገር በእርግጠኝነት ወደ ውሸት መንገዶች ይመራል፡፡ እያንዳንዱን ሀሳብና መርህ ወደ ፊት በማስቀጠል ረገድ እና በእያንዳንዱ በሚሰጥ ውክልና ውስጥ በጥንቃቄ የተሞላ፣ ልባዊ የሆነ፣ እንደ ዓለት የጸና፣ ጠቃሚ የሆነ ሥራ ከሌለ በስተቀር ነፍሳት ይጠፋሉ፡፡…ከእግዚአብሔር ራዕይን ተቀብለናል የሚሉትን በተመለከተ ታላቅ ጥንቃቄ መደረግ አለበት፡፡ በጥንቃቄ ነቅቶ መጠበቅና ብዙ መጸለይ ያስፈልጋል፡፡ የአንድ ሰው አእምሮም ቢሆን ከእግዚአብሔር ሥራ ጋር ግንኙነት ባላቸው ጠቃሚ ነገሮች ላይ ግምት እንዲወስድ ወይም በሕዝብ ፊት እንዲያቀርብ መተው ስለሌለበት በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ታላቅ ሥራ ውስጥ ድርሻቸውን እየተጫወቱ ያሉ ሰዎች የሚመጣውን እያንዳንዱን አዲስ ነገር በተመለከተ አብረው መምከር ያስፈልጋቸዋል፡፡ --Letter 6a, 1894. {2SM 91.2} Amh2SM 91.3