የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
ምዕራፍ 10—የአና ፊሊፕስ ራዕዮች
[በባትል ክሪክ የምትኖር ወጣት ሴት በ1893 ዓ.ም ግምቶቿና ሕልሞቿ የእግዚአብሔር መንፈስ ፍንጭ በመስጠት ያሳወቃቸው ነገሮች ናቸው ብላ ወደማመን ተመርታ ነበር፡፡ ምስክርነቶቼ ብላ የምትጠራቸው ነገሮች የመሪነት ቦታ ባለው ሠራተኛ እጆች ገብተው በመለኮት ምሪት የተሰጡ መልእክቶች እንደሆኑ በመቆጠር በባትል ክሪክ ቤተ ክርስቲያን ፊት በተነበቡ ጊዜ በሥራዋ ተደፋፈረች፡፡ በሚቀጥለው ጧት በዚህ ቦታ የቀረበውን መልእክት ይህ ሠራተኛ ተቀበለ፡፡ ኣና ፊሊፕስ ይህ ሲነበብ ሰምታ ማታለያውን ለይታ ስላወቀችና መሳሳቷን ስላመነች ያለፈውን ሥራዋን ጣለችና በቤተ ክርስቲያን ሥራ ውስጥ የታመነች፣ ውጤታማ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ ሆነች፡፡---አሰባሳቢዎች] Amh2SM 85.1