የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

345/349

በፍጥረትም ሆነ በድነት አንድ ቤተሰብ

እግዚአብሔር ለዜግነት፣ ለዘር ወይም ለመደብ ልዩነት እውቅና አይሰጥም፡፡ እርሱ የሁሉም ሰብአዊ ዘር ፈጣሪ ነው፡፡ ሁሉም ሰዎች በፍጥረት አንድ ቤተሰብ እንደሆኑ ሁሉ በድነትም አንድ ናቸው፡፡ ክርስቶስ የመጣው እያንዳንዱን የመለያ ግድግዳ ለማፍረስና እያንዳንዱ ነፍስ ወደ እግዚአብሔር በነጻነት መቅረብ እንዲችል የቤተ መቅደሱን እያንዳንዱን ክፍል ክፍት ለማድረግ ነው፡፡… በክርስቶስ አይሁዳዊ ወይም ግሪክ፣ ባርያ ወይም ጨዋ የለም፡፡ ሁሉም በከበረው ደሙ ወደ እርሱ እንዲቀርቡ ተደርገዋል፡፡--Christ’s Object Lessons p. 386. Amh2SM 486.1

እግዚአብሔር በሀዘኔታ ከሚያያቸው ነገሮች ሁሉ እጅግ ያሳዘነው የጥቁር ዘሮች በባርነት መኖር ነው፡፡ ለእነርሱ በምንሰራው ሥራ በእግዚአብሔር ፈቃድ ከባርነት ነጻ ስለ መውጣታቸው፣ በፍጥረትም ሆነ በድነት ከእኛ ጋር ያላቸውን የጋራ ግንኙነት እና የነጻነት በረከቶችን ለማግኘት መብት እንዳላቸው እንድናስታውስ ይሻል፡፡-- Testimonies, vol. 7, p. 223. Amh2SM 486.2