የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

344/349

አንድ ወንድማማችነት

ክርስቶስ ወደዚህች ምድር የመጣው በምህረትና በይቅርታ መልእክት ነው፡፡ አይሁድና አህዛብ፣ ጥቁርና ነጭ፣ ባርያና ጨዋ በአንድ የጋራ ወንድማማችነት በመገናኘት በእግዚአብሔር ፊት እኩል ሆነው ለሚታዩበት ኃይማኖት መሰረት ጣለ፡፡ አዳኙ ለእያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር ገደብ የለሽ ፍቅር አለው፡፡ በእያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር ውስጥ ሊሻሸል የሚችል ችሎታ መኖሩን ያያል፡፡ በመለኮታዊ ጉልበትና ተስፋ ሕይወቱን አሳልፎ ለሰጣቸው ሰዎች ሰላምታ ያቀርባል፡፡ በእርሱ ብርታት በመልካም ሥራና በመንፈስ ኃይል የተሞላ ሕይወትን መኖር ይችላሉ፡፡-- Testimonies, vol. 7, p. 225. Amh2SM 485.4