የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
የመተማመን ንግግር
ወንድሞቼ ሆይ፣ «በነገር ሁሉ ተማምኜባችኋለሁና ደስ ይለኛል» (2 ቆሮ. 7፡16)፡፡ በምድር ላይ ካለው የእግዚአብሔር ሥራ ዕድገት ጋር የተገናኙ ጠቃሚ እርምጃዎችን በተመለከተ አንዳንዶች እየያዙ ያሉትን አመለካከት ሳይ አሁንም የጠለቀ ስጋት ይሰማኛል፡፡ ነገር ግን በመላው የሥራ መስክ ባሉ ሠራተኞች ላይ እምነት አለኝ፤ አብረው ሲሰበሰቡ እና በጌታ ፊት ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ ለአገልግሎቱ በአዲስ መልክ ራሳቸውን ሲቀድሱ ፈቃዱን ማድረግ እንዲችሉ ይደረጋሉ፡፡ አሁንም ቢሆን ነገሮችን በትክክለኛ ብርሃን ማየት የማይችሉ አንዳንዶች አሉ፣ ነገር ግን እነዚህ ግለሰቦች አብረው ከሚሰሩአቸው ሰዎች ጋር ዓይን ለዓይን መተያየትን ሊማሩና ጌታን ከልባቸው በመሻትና ፈቃዳቸውን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ፈቃድ አሳልፈው በመስጠት በዚህ ወቅት አስከፊ የሆኑ ስህተቶችን ከመፈጸም ሊርቁ ይችላሉ፡፡ Amh2SM 401.4
በቅርቡ በሌሊት ወቅት በፊቴ ባለፉ ነገሮች በጥልቀት ተነክቻለሁ፡፡ በብዙ ስፍራዎች ታላቅ እንቅስቃሴ፣ የመነቃቃት ሥራ፣ የሚካሄድ ይመስል ነበር፡፡ ሕዝባችን ለእግዚአብሔር ጥሪ ምላሽ እየሰጠ በመስመር ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ ወንድሞቼ ሆይ፣ እግዚአብሔር እየተናገረን ነው፡፡ ድምጹን መስማት የለብንምን? ፋኖሳችንን በመወልወል ጌታቸው እንዲመጣ እንደሚጠብቁ ሰዎች መሥራት የለብንምን? ጊዜው ብርሃንን መሸከምንና ተግባርን የሚጠይቅ ጊዜ ነው፡፡ Amh2SM 402.1
ወንድሞቼ ሆይ፣ «በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤ በትህትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሱ፤ በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ» (ኤፌ. 4፡ 1-3)፡፡ General Conference Bulletin, May 19, 1913, pp. 33, 34. Amh2SM 402.2