የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
ምዕራፍ 4—በመንፈስ እንደሚመሩ የሚናገሩ ሰዎችን ማታለያ በተመለከተ የተሰጡ ማስጠንቀቂያዎች
[በሕዳር 12 ቀን 1908 ዓ.ም ካሊፎርኒያ ውስጥ ወደ ነበረችው ሰይንት ሄሌና አንድ ቀናኢ የሆነ ሰው ከሚስቱ ጋር መጣ፡፡ ሚስስ ኋይትን ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ፈለጉና ለሶስት አመታት ያህል የነበሩአቸውን አስገራሚ ልምምዶች ተረኩላት፡፡ እነዚህ ልምምዶች ሊመጡላቸው የጀመሩት ለመንፈስ ቅዱስ መውረድ በርካታ ቀናት ከጾሙና ከጸለዩ በኋለ እንደነበረ ነገሯት፡፡ የጾምና የጸሎት ልምምዳቸውን ሲገልጹ «ታላላቅ የላብ ጠብታዎች በቅንድቦቻችን ላይ እስኪጠራቀሙ ድረስ” በማለት ይናገራሉ፡፡ የቀድሞዎቹ ሐዋርያት እንደተቀበሉት ሁሉ እነርሱም መንፈስ ቅዱስን እንደተቀበሉ አምነዋል፡፡ በልሳን እንደተናገሩና ሌሎችም የእነርሱን ልምምድ መለማመድ እንዲችሉ ተግተው እንደሰሩ ተናገሩ፡፡ {2SM 40.1] Amh2SM 40.1
አንድ ልጅ በሰመመን ውስጥ እንዲገባ በማድረጋቸው ተከሰው ወደ እስር ቤት ገብተው ነበር፡፡ ጠበቃውና የከተማው ከንቲባ ጉዳዩን ከሰሙ በኋላ እነዚህ ሰዎች አእምሮን በመሳት ድንበር ላይ ካልሆኑ፣ በአስጊ ሁኔታ አእምሮአቸውን ለመሳት ተቃርበዋል በማለት ተናግረው ነበር፡፡ በእስር ቤት ውስጥ እያሉ «በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት» አእምሮን እንደሳተ ሰው እንዲሆኑ እንደተነገራቸው ተናገሩ፡፡ የዚህ ውጤት እግዚአብሔር «እነዚህ ሰዎች ወደ ውስጥ መግባትን እንዲፈሩ” እግዚአብሔር ፍርሃት እንዲልክባቸው ነበር፡፡ {2SM 40.2} Amh2SM 40.2
እነርሱ በሰመመን ውስጥ ለማስገባት በመሞከራቸው የተከሰሱበት ልጅ የትንቢት መንፈስ ሥጦታ እንደነበረውና ወዴት መሄድ እንዳለባቸው እንደሚመራቸው አመኑ፡፡ በጸሎት አማካይነት በሽተኞችን እንደፈወሱ፣ አጋንንትን እንዳወጡና ሌሎች ብዙ ድንቅ ነገሮችን እንዳደረጉ ተናገሩ፡፡ ባልዬው ስለ ሚስቱ ሲናገር እንዲህ አለ፡- «መንፈስ በእሷ አማካይነት ይሰራል፣ ይህ በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ የሚፈሰው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እንደሆነ እናምናለን፡፡» {2SM 40.3} Amh2SM 40.3
ከዚህ ቀጥለው ያሉት አረፍተ ነገሮች ስለዚህና ይህን የሚመስሉ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ ኤለን ኋይት የተናገረቻቸው አረፍተ ነገሮች ናቸው፡፡ --COMPILERS.}{2SM 40.4} Amh2SM 40.4