የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

242/349

ለማያቋርጥ ጥረት የተሰጠ ሽልማት

የባለቤቴን ጤንነት ለመመለስ በተደረገው ጥረት ለአሥራ ስምንት ወራት ከእግዚአብሔር ጋር የማያቋርጥ ትብብር ካደረግኩ በኋላ ወደ ቤት መልሼ ወሰድኩት፡፡ ወደ ወላጆቹ ወስጄ «አባት፣ እናት፣ ይኸውላችሁ ልጃችሁ» አልኳቸው፡፡ Amh2SM 308.1

እናቱ «ኤለን፣ ለዚህ አስደናቂ ለሆነ የጤና መመለስ ከእግዚአብሔርና ከአንቺ ሌላ ምሥጋና የሚገባው ማንም የለም፡፡ ጥረትሽ ውጤት አስገኝቷል» አለችኝ፡፡ Amh2SM 308.2

ጤንነቱ ከተመለሰ በኋላ በሕይወቱ ዘመን ከሰራቸው ሥራዎች ሁሉ የተሻለ ሥራ የሰራባቸውን በርካታ ዓመታት በሕይወት ኖረ፡፡ ለአሥራ ስምንት ወራት ልፋት ያለበትን እንክብካቤ ላደረግኩበት እነዚህ ጠቃሚ ሥራ የተሰራባቸው ዓመታት እጥፍ ድርብ አድርገው አልካሱምን? Amh2SM 308.3

ይህንን አጭር የሕይወት ልምምድ ትረካ የሰጠኋችሁ የታመሙትን ሰዎች ወደ ጤንነት ለመመለስ ስለምንጠቀምባቸው የተፈጥሮ ዘዴዎች የሆነ የማውቀው ነገር እንዳለ ላሳያችሁ ነው፡፡ ከእርሱ ጋር ስንተባበር እርሱ ድርሻውን ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አምነን ከሰራን እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ተአምራቶችን ይሰራልናል፡፡ የወንድሞቼ ጥረቶች እጅግ የተሳኩ እንዲሆኑ ትርጉም ያለው መንገድ እንዲከተሉ ልመራቸው የምችለውን ነገር ሁሉ ለማድረግ እሻለሁ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ተባብረው ቢሆን ኖሮ ወደ መቃብር የሄዱት ብዙዎች ዛሬ በሕይወት ሊኖሩ ይችሉ ነበር፡፡ እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ ማገናዘብ የምንችል ወንዶችና ሴቶች እንሁን፡፡ Manuscript 50, 1902. Amh2SM 308.4