የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

233/349

ምዕራፍ 30—የኤለን ኋይት ፈውስ የሚያመጡ ነገሮችን መጠቀም

ኤለን ኋይት በተደጋጋሚ ስለ ቀላል ፈውሶች ትናገራለች፡፡ ይህንን ማለቷ ምን ማለት እንደሆነ ስትገልጽ ንጹህ አየር፣ የፀሐይ ብርሐን፣ እረፍት፣ የአካል እንቅስቃሴ፣ ተመጣጣኝ ምግበ፣ ከምግብና ከመጠጥ መገታት፣ ውኃን መጠቀምና በመለኮት ኃይል መታመን እንደሆነ ትናገራለች፡፡ ገጽ 287-289ን እና The Ministry of Healing, ገጽ 127ን ይመልከቱ፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ ሚስስ ኋይት በጥቂት አጋጣሚዎች፣ በግል ከሰዎች ጋር ባደረገቻቸው ግንኙነቶች፣ እሷ ስለምታውቃቸውና ስለተጠቀመቻቸው ቀላል ሕክምናዎች ትጠቅሳለች፤ ማንኛውም የዚህ ዓይነት ሕክምና በተለምዶ የተጠቀሰው በአንድ አጋጣሚ ብቻ ነው፡፡ ከሰዎች ጋር ባደረገቻቸው ግንኙነቶች ውስጥ በችግር ጊዜ ካልሆነ በስተቀር የማትጠቀማቸውን መድኃኒቶች እንድትጠቀም የመሯትን ጥቂት አንገብጋቢ ሁኔታዎችን ጠቅሳለች፡፡ Amh2SM 292.1

ስለ አንዳንድ ሕክምናዎች የተሰጡትን እነዚህን ማጣቀሻዎች በመገምገም አንባቢው መገንዘብ ያለበት አራት ነጥቦች አሉ፡፡ Amh2SM 292.2

1. ይህ ስብሰባ በተደረገበት ጊዜ እነዚህ መግለጫዎች እስከታወቁበት ድረስ ቀጥለው ያሉት ገጾች ሚስስ ኋይት ቀላል ባሕርይ ስላላቸው የተወሰኑ ቀላል ሕክምናዎች የጠቀሰቻቸውን ወሳኝ አረፍተ ነገሮች ይዘረዝራሉ፡፡ Amh2SM 292.3

2. በኤለን ኋይት መጻሕፍት ውስጥ እንደሚገኘው አጠቃላይ ለሆኑ የጤና ምክሮች ከተሰጡት ከ2000 በላይ ገጾች ጋር ሲነጻጸር እነዚህን ዓረፍተ ነገሮች በጽሁፍ መልክ ለማስቀመጥ ያስፈለጉት ገጾች በጣም ጥቂት፣ አሥራ አንድ ገጾች ያህል ናቸው፡፡ Amh2SM 292.4

3. ሚስስ ኋይት ለሃምሳ አመታት ስለ ጤና እና ለሕመምተኞች ስለመጠንቀቅ ለሕትመት የሚሆኑ ነገሮችን በስፋት ጽፋለች፡፡ ነገር ግን በጣም ደስ የሚለውና ወሳኝ እውነታው፣ ለሕዝቅያስ ቁስል የታዘዘውን «የሾለ ፍሬ ጥፍጥፍ» በአጭሩ ከመጥቀስና ከልጆቿ አንዱ በታመመ ጊዜ ውጤታማ ያልሆኑ «ቀላል ዕፆች” ስለመጠቀም ብልጭ ከሚል ማውሳት በስተቀር እጽዋት ስለሚሰጡት የመድሃኒትነት ጥቅምም ሆነ ስለ ሌሎች ቀላል ሕክምናዎች በማናቸውም የታተሙ መግለጫዎቿ ላይ አልጠቀሰችም፡፡ በቀላሉ ለመግለጽ ያህል፣ ይህ እውነታ እጽዋትን መጠቀም እሷ እንደዚህ በተሟላ ሁኔታ ባስቀመጠችው በመላው የጤና ፕሮግራም ውስጥ መሠረታዊ የሆነ ጠቀሜታ አለው ብሎ ለመደምደም አይፈቅድም፡፡ Amh2SM 292.5

4. ሚስስ ኋይት እነዚህን ስለሚመስሉት ቀላል ሕክምናዎች ስትገልጽ ሳለ ሌሎችና የበለጠ ውጤታማ የሆኑ ሕክምናዎች ወደ ፊት ሊኖሩ አይችሉም ብላ በአንድም ቦታ አትናገርም፡፡ Amh2SM 293.1

የሚስስ ኋይት ጽሁፎች የእጽዋት መድሃኒትነትን የሚያረጋግጡ ብቻ ሳይሆኑ በሽታን ለማከም ዋና መንገዶች ናቸው የሚሉ አንዳንድ ሰዎች ስላሉ፣ እና በዚህ ነጥብ ላይ ያልታተመ እጅግ ብዙ ነገር ስላለ፣ ቀጥለው ያሉ መግለጫዎችን በማሳተማቸው የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች አእምሮዎች እንደሚረዱና መረጃው ግልጽ ሆኖ መጠበቅ እንደሚችል የኋይት ጽሁፎች ባለአደራዎች ያምናሉ፡፡ በማንኛውም ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ከደራሲው በበለጠ ሁኔታ አንባቢው ለእነዚህ አረፍተ ነገሮች ታላቅ ዋጋ መስጠት የለበትም፡፡ እሷ ለሕትመት በቅተው ለሕዝብ በቀረቡ ስራዎቿ ውስጥ ሕመምተኛውን ስለማከም ሰፊ መርሆዎችን አስቀምጣለች፡፡ Amh2SM 293.2