የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
በጤና ተቋም ፕሮግራም ውስጥ ቀላል ፈውሶች
የጤና ተቋማት መቋቋም ስላለባቸው ቦታ ብዙ መመሪያ ተሰጥቶኛል፡፡ መመሪያውም ከትልልቅ ከተሞች ጥቂት ማይሎችን እንዲርቁና ከእነርሱ ጋር በተገናኘ ሁኔታ መሬት እንዲወሰድ ነው፡፡ ፍራፍሬና አትክልቶችን ማሳደግ አስፈላጊ ሲሆን ሕመምተኞችም ወጣ ብለው እንዲሰሩ መደፋፈር አለባቸው፡፡ በሳንባ ሕመም እየተሰቃዩ ያሉ ብዙ ሰዎች በአመት ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ ውጭ መሆን የሚችሉበት ሁኔታ ውስጥ ቢሆኑ ኖሮ መፈወስ ይችሉ ነበር፡፡ ከሳንባ ነቀርሳ የተነሳ የሞቱት አብዛኞቹ ብዙ ንጹህ አየርን ተንፍሰው ቢሆን ኖሮ በሕይወት መኖር ይችሉ ነበር፡፡ ወጣ ብለን የምንተነፍሰው ንጹህ አየር እንደ መድሃኒት መፈወስ የሚችል ሲሆን ወደ ፊት የሚታይ ጎጂ ውጤት አያስከትልም፡፡ Amh2SM 291.1
ከመጀመሪያው ጀምሮ መድሃኒቶች በጤና ተቋሞቻችን ውስጥ ባይቀመጡ እና በንጹህ ውኃ፣ በንጹህ አየር፣ በፀሐይ ብርሃንና በመስክ ውስጥ በሚያድጉ በአንዳንድ ቀላል እጽዋቶች ውስጥ ያሉ ቀላል ፈውሶች ጥቅም ላይ ውለው ቢሆን ኖሮ የተሻለ ይሆን ነበር፡፡ እነዚህ ፈውሶች ምስጢራዊ ስም ተሰጥቷቸው በሰብአዊ ሳይንስ የተቀመሙ መድሃኒቶችን ያህል ውጤታማ ናቸው፡፡ Amh2SM 291.2
ሕመም እያሰቃያቸው ያሉ በሺሆች የሚቆጠሩ ሰዎች ለሕይወታቸው በመድሃኒት መደብር ላይ ከመደገፍ ይልቅ መድሃኒቶችን በሙሉ በማስወገድ ጨጓራን በማስቆጣት ካልተቀሰቀሰ በስተቀር ቀላል የሆነውን ምግብ እንኳን መፍጨት የማይችል ደካማ እንዲሆን የሚያደርጉትን ሻይን፣ ቡናን፣ አስካሪ መጠጥን ወይም ቅመማቅመሞችን ሳይጠቀሙ ዝም ብለው በመኖር ጤንነታቸውን መመለስ ይችላሉ፡፡ ጌታ ደካማና አቅመቢስ ለሆኑት ሁሉ የእሱ ብርሃን ጥርት ባሉና በሚታዩ ጨረሮች እንዲበራ ለማድረግ ፈቃደኛ ነው፡፡ Manuscript 115, 1903 (General manuscript regarding Sanitarium work). Amh2SM 291.3