የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
ጌታ መጽናናትሽ ሊሆን
ባሏ ለሞተባት ሴት የተሰጠ የማጽናኛ መልእክት
ውድ እህቴ ሆይ፣
የደረሰብሽን ሀዘን የሚገልጽ በእህት ጂ የተጻፈ ደብዳቤ አሁን በእጄ ውስጥ ገብቷል፡፡ ውድ እህቴ ሆይ፣ ስለደረሰብሽ ሀዘን አዝናለሁ፡፡ ልጎበኝሽ በምችልበት ቦታ ሆኜ ብሆን ኖሮ እጎበኝሽ ነበር፡፡… Amh2SM 266.2
ውድ እህቴ ሆይ፣ ጌታ በሀዘን እንድትቆዝሚ አይፈልግም፡፡ ባለቤትሽ እኔ ይኖራል ብዬ ከገመትኩት በላይ ለሆነ ጊዜ እንዲኖር ተደርጓል፡፡ እግዚአብሔር በምህረቱ እንዳኖረው ሁሉ አሁንም ከብዙ ሥቃይ በኋላ በምህረቱ በኢየሱስ እንዲያርፍ ፈቅዷል፡፡… የአንቺና የእኔ ባለቤቶች በእረፍት ላይ ናቸው፡፡ አሁን ሕመምና ስቃይ የለባቸውም፡፡ በእረፍት ላይ ናቸው፡፡ Amh2SM 266.3
እህቴ ሆይ፣ በስቃይና በሀዘን ውስጥ ስላለሽ አዝናለሁ፡፡ ነገር ግን ክቡር ኢየሱስ፣ ክቡር አዳኝ በሕይወት ይኖራል፡፡ ለአንቺ በሕይወት ይኖራል፡፡ በፍቅሩ እንድትጽናኚ ይፈልጋል፡፡ አትጨነቂ፤ በጌታ ታመኚ፡፡ ያለ ሰማያዊ አባትሽ እውቅና አንዲት ድንቢጥ እንኳን በምድር ላይ አትወድቅም፡፡… Amh2SM 266.4
እህቴ ሆይ፣ በጌታ ተጽናኚ፡፡ “ክርስቶስም ስለእኛ በሥጋ መከራን ስለተቀበለ…እናንተም ደግሞ ያን ሀሳብ እንደ ዕቃ ጦር አድርጋችሁ ያዙት” (1ኛ ጴጥ. 4፡ 1)፡፡ በመከራሽ ነፍስሽን በእግዚአብሔር ላይ እንድታቆዪ አደፋፍርሻለሁ፡፡ ጌታ ረዳትሽ፣ ብርታትሽ እና መጽናናትሽ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ወደ እርሱ በመመልከት ታመኝበት፡፡ መጽናናታችንን ከክርስቶስ መቀበል አለብን፡፡ የዋህነትንና የልብ ትህትናን በእርሱ ትምህርት ቤት ተማሪ፡፡ እያንዳንዱ የምትናገሪው ቃል የእግዚአብሔርን በጎነት፣ ምህረት እና ፍቅር ያሳይ፡፡ በቤት ውስጥ ላሉት ሁሉ መጽናኛ እና በረከት ለመሆን ወስኚ፡፡ ጣፋጭ፣ ንጹህ፣ ሰማያዊ ከባቢ አየርን ፍጠሪ፡፡. . . . Amh2SM 266.5
የነፍስን መስኮቶች ወደ ሰማይ በመክፈት የጽድቅ ፀሐይ ብርሐን እንዲገባ ፍቀጂ፡፡ አታማርሪ፡፡ አትዘኚ፣ አታልቅሽም፡፡ የጨለማውን ወገን አትመልከቺ፡፡ የእግዚአብሔር ሰላም በነፍስሽ ይንገስ፡፡ እንደዚህ ሲሆን መከራሽን ሁሉ ለመሸከም ብርታት ይኖርሻል፣ ለመሸከም የሚያስችል ጸጋ ስላለሽ ደስ ይልሻል፡፡ እግዚአብሔርን አመስግኚ፤ ስለ እርሱ መልካምነት አውሪ፤ ስለ እርሱ ኃይል ተናገሪ፡፡ ነፍስሽን የከበበውን ከባቢ አየር ጣፋጭ አድርጊ፡፡ Amh2SM 266.6
የሀዘን ቃላትን በመናገር እግዚአብሔርን አታዋርጂ፣ ነገር ግን በልብ፣ በነፍስና በድምጽ እርሱን አመስግኚ፡፡ ሁሉንም ነገር በብሩህ ጎኑ ተመልከቺ፡፡ ወደ ቤትሽ ደመናን ወይም የጨለማ ጥላን አታምጪ፡፡ የፊትሽ ብርሃንና አምላክሽ የሆነውን እርሱን አመስግኚ፡፡ ይህን አድርጊና ሁሉም ነገር እንዴት በተስተካከለ ሁኔታ እንደሚሄድ ተመልከቺ፡፡ Amh2SM 267.1
አንቺንም ሴት ልጅሽንም እወዳችኋለሁ፡፡--Letter 56, 1900. Amh2SM 267.2