የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
ለአደጋ ተጋልጦ ያለው ሥራ ልዩ ባሕርይ
መሰራት ካለበት ትልቅ ሥራ አንጻር ሰራተኞቻችን መጠነኛ በሆነ ደሞዝ ለመስራት ፈቃደኛ መሆን አለባቸው፡፡ ምንም እንኳን ትልቅ ደሞዝ ማግኘት ብትችሉም ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ ራስን በመካድ የኖረበትን የእርሱን ሕይወት ምሳሌ መገንዘብ አለባችሁ፡፡ በዚህ ሰዓት ሰራተኞች እየጠየቁ ያሉት ደሞዝ እጅግ ብዙ ነው፡፡ ብዙ ደሞዝ ጠይቃችሁ ከተቀበላችሁ ሌሎችም ተመሳሳይ ተግባር እንዲፈጽሙ በር እየተከፈተ ነው፡፡ በባትል ክሪክ የነበረውን የሥራ መንፈስ ለማበላሸት አስተዋጽኦ ያደረገው የሰራተኞች ከፍተኛ ደሞዝ መጠየቅ ነበር፡፡ ይህን እንቅስቃሴ የመሩት ሁለት ሰዎች ሲሆኑ ሌሎች ሶስት ወይም አራት ሰዎች የተቀላቀሉአቸው ሲሆን አብዛኞቹ ቢከተሉት ኖሮ ውጤቱም ከጊዜ በኋላ የዚህን መልእክት ሥራ ልዩ ባሕርይ ሊያበላሽ የሚችል ሕብረት ይሆን ነበር፡፡ የወቅቱ እውነት ሥራ የተመሰረተው ራስን በመካድና ራስን መስዋዕት በማድረግ ላይ ነበር፡፡ ይህ ራስ ወዳድነት ያለበት የመስገብገብ መንፈስ ሙሉ በሙሉ የዚህ መርሆዎች ተቃራኒ ነው፡፡ በጊዜ ሂደት መላውን አካል በሽተኛ እንደሚያደርግ እንደ አሰቃቂ ለምጽ ነው፡፡ በጣም እፈራዋለሁ፡፡ በሥራችን ጅምር ላይ ከነበረው ትህትናና ራስን መስዋዕት የማድረግ መንፈስ እንዳንለይ ልብ ማለት ያስፈልገናል፡፡ Amh2SM 197.1
በ---- ባለው የጤና ማሰልጠኛ ተቋም ውስጥ ሰፊ የሆነ ተጽእኖ ማድረግ አይከብድብህም፡፡ በራስህ በኩል ማግኘት አለብኝ ብለህ የምታስበውን ደሞዝ ባለመጠየቅ ራስ ወዳድነት የሌለበትን ድርሻ ብትጫወት እግዚአብሔር ሰርተህ በምታገኘው ያኖርሃል፡፡ በተቃራኒው ከፍተኛ ደሞዝ እንዲከፈልህ ብትጠይቅ ሌሎችም አንተ የጠየቅከውን ያህል ከፍተኛ ደሞዝ የመጠየቅ መብት እንዳላቸው ያስባሉ፤ ከዚህ የተነሳ የወቅቱን እውነት ሥራ በሌሎች ቦታዎች ለመገንባት ጥቅም ላይ መዋል ያለበት ገንዘብ ለከፍተኛ ደሞዝ ክፍያ ይውላል፡፡ Amh2SM 198.1
ወሳኝ የሆኑ ውሳኔዎችን ስንወስን ጥያቄውን በሁሉም አቅጣጫ ማጥናት አለብን፡፡ በሥራው ውስጥ ሀላፊነት እንደሚሰማቸው ሰዎች እንድንሰራ ቦታ እንደተሰጠን ሁልጊዜ ማስታወስ አለብን፡፡ አንዳንዶች ደሞዛቸውን በመመደብ ዓለማዊ ሥርዓትን ይከተላሉ፤ ነገር ግን ጌታ ነገሮችን የሚመለከተው እነዚህ ሰዎች እንደሚመለከቱት አይደለም፡፡ የእኛን ተግባሮችና ሀላፊነቶች የሚመለከተው በክርስቶስ ራስን የመካድ ምሳሌ ነው፡፡ ወንጌል ለዓለም መቅረብ ያለበት ቃልና ተግባር ተጣጥመው ነው፡፡ Amh2SM 198.2
የጤና ማሰልጠኛ ተቋሞቻችን እንደ ዓለም ወግ መመራት የለባቸውም፡፡ በጤና ሀላፊው እንኳን ከፍተኛ የሆነ ደሞዝ መውሰድ እንደ አስፈላጊ ነገር ሆኖ መታየት የለበትም፡፡ እኛ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ነን፡፡--Letter 370, 1907. Amh2SM 198.3