የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

160/349

ተቋሞቻችንን ሁሉ ለስጋት የሚዳርግ ነገር

ጳውሎስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ክፋቶች እንደሚመጡ በማየቱ እንዲህ አለ፣ «በእግዚአብሔር ቅናት እቀናላችኋለሁና፣ እንደ ንጽህት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤ ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፣ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽህና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ” (2ኛ ቆሮ. 11፡ 2፣ 3)፡፡ Amh2SM 196.3

ዛሬ ትምህርት ቤቶቻችንን፣ ተቋሞቻችንን፣ ቤተ ክርስቲያኖቻችንን በስጋት ላይ እየጣለ ያለው ይህ ክፋት ነው፡፡ ካልታረመ በስተቀር የብዙዎችን ነፍሶች ለአደጋ ያጋልጣል፡፡ አንድ ሰው በማያምኑ ሰዎች መካከል ከፍተኛ ደሞዝ የሚያስገኝለትን ሥራ እየሰራ ስለሆነ በከፍተኛ ደረጃ አድልዎ ሊደረግልኝ ይገባል ብሎ ያስባል፡፡ እርካታ ባለማግኘቱ ከፍተኛ ደሞዝ ለሚከፍለው አካል ራሱን ይሸጣል፡፡ በተቋሞቻችን ውስጥ የሚሰሩ ሰዎችን መቆጣጠር ያለባቸውን መርሆዎች ከአደጋ ለመጠበቅ ሲባል በኃላፊነት ላይ ላሉት ሁሉ «ይህ የራስ ወዳድነትና የምኞት ክፉ እርሾ ስለሆነ እንደዚህ ካሉ ነገሮች ሁሉ ራሳችሁን ለዩ» እንድል ጌታ አዞኛል፡፡ Amh2SM 196.4

ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር እየለኩና ራሳቸውን ከእርስ በርሳቸው ጋር እያወዳደሩ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን መጻሕፍት ጸሐፊዎችና ሥራ መሪዎች ቢሆኑ እንኳን እነርሱን በሥራቸው ላይ እንዲቆዩ ማድረግ እጅግ አስከፊ ሥራ ነው፡፡ ከእንደዚህ ዓይነት ሰው ጋር እግዚአብሔር አብሮ ስላልሆነ ይህንን ሰው የሙጥኝ ብሎ መያዝ አደጋ አለው፡፡ የዚህን ሰው ነፍስ የከበበው የአለማመን ከባቢ አየር ነው፡፡ ይህ ሰው ያደረገው ንጽጽር አጭበርባሪ ወደመሆን መርቶታል፡፡ ለራሱ እንዲህ ይላል፣ «እንደዚህ ያለ ሰው ይህን ያህል ካገኘ እኔም የእርሱን ያህል ማግኘት አለብኝ፡፡» በሕግ ውስጥ ከተጻፈው የበለጠ ጠቢብ በመሆን ለራሱ ጥቅም ገንዘብ ይሰበስባል፡፡ በመሆኑም የእግዚአብሔርን ግምጃ ቤት ይዘርፋል፡፡ እግዚአብሔር ይህን ሰው የሚመለከተው የአካንን ኃጢአት እንደተመለከተ ነው፡፡ እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች ለሥራው ጥሩ ቅርጽ እንደማይሰጡ ያያል፡፡ ከባድ በሆኑ የሥራ መስኮች እየሰሩ ላሉትና ከፊል ደሞዛቸውን በእነዚህ የሥራ መስኮች ውስጥ ያሉ ሰዎችን ፍላጎቶች ለማሟላት ለሚሰጡ ሰዎች የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች መስጠት አይችሉም፡፡ እያንዳንዱን ይህን የመሰለ ነገር እግዚአብሔር ይመለከትና ማግኘት ያለባቸውን ሁሉ ማግኘት እንዳለባቸው በማሰብ በራስ ወዳድነት ለራሳቸው በመጠንቀቅ በዚህ መልክ ራሳቸውን በሚለኩ ላይ ፍርድ ያስተላልፋል፡፡ --Manuscript 97, 1899. Amh2SM 196.5