የልጅ አመራር

37/85

ምዕራፍ 35—ወለጆች ብርቱ ባህሪያትን እንዴት መገንባት እንዳለባቸው

እጅግ የተሻለ ጊዜ እና ሐሳብን ለሥራ መስጠት—ወላጆች በእቅፋቸው ውስጥ ሸክም የሚሆን አቅመ ቢስ ልጅ ይረከባሉ፤ እርሱ ምንም አያውቅም እንዲሁም እግዚአብሔርን መውደድ መማር አለበት፣ ጌታ በሚየዘው የአስተዳደግ መመሪያ እና ምክር ማደግ አለበት፡፡ በመለኮታዊው አምሳያ መሠረት መቀረጽ አለበት፡፡ CGAmh 175.1

ወላጆች ልጆቻቸውን በማልጠን ረገድ ያለባቸውን የሥራ አስፈላጊነት ሲገነዘቡ፣ ዘላለማዊ ዓላማን የሚያካትት መሆኑን ሲገነዘቡ፣ እጅግ የተሻለ ጊዜያቸውን እና ሀሳባቸውን ለዚህ ስራ ማዋል እንዳለባቸው ይሰማቸዋል። 331 CGAmh 175.2

የተካተቱ የመርኾዎችን መረዳት ማግኘት—በህፃናት እና በልጅነት ዓመታት የተገኙ ትምህርቶች፣ የተመሰረቱ ልማዶች፣ ካደጉ በኋላ ከሚሰጣቸው ትምህርቶች እና ስልጠናዎች ሁሉ በላይ በባህሪይ ግንባታ ላይ የላቀ ሚና አላቸው፡፡ CGAmh 175.3

ወላጆች ይህንን ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ የህፃናትን እንክብካቤ እና ስልጠና መሰረታዊ መርሆዎች መረዳት አለባቸው፡፡ እነርሱን በአካል፣ በአእምሮ እና በግብረ-ገብ ጤንነት ለማሳደግ ብቁ መሆን አለባቸው፡፡ 2 CGAmh 175.4

ከጥራዝ ነጠቅነት መራቅ—እኛ የምንኖረው ሁሉም ነገር ጥራዝ ነጠቅ ወደ መሆን የመጣበት ዘመን ውስጥ ነው፡፡ ልጆች ከጨቅላነታቸው ጀምሮ የሚሰጣቸው ሥልጠና እና ትምህርት ጥራዝ ነጠቅ በመሆኑ ጥቂት የባህሪይ መረጋጋትና ጽናት ብቻ አለ፡፡ ባህሪያቸው የተገነባው በተንሸራታች አሸዋ ላይ ነው። ራስን መካድ እና ራስን መግዛት በባህሪያቸው ውስጥ አልተቀረጸም። ተግባራዊ ህይወታቸው እስኪበላሽ ድረስ ልቅ በሆነ ሁኔታ እንክብካቤ ያገኛሉ፣ እንዲሁም ይሞላቀቃሉ፡፡ እንዳሻቸው የመሆን ፍቅር አዕምሮአቸውን ይቆጣጠራል፣ ልጆችም እስኪጠፉ ድረስ ይሞላቀቃሉ፡፡ 332 CGAmh 175.5

ልጆችን በጸሎት እና በእምነት ይመሸጓቸው—ለመፈጠር ምንም ጥያቄ ያለቀረቡ ልጆችን ወደ ዓለም አምጥታችኋል። ለመጻኢ ደስታቸው እና ዘላለማዊ ደህንነታቸው ኃላፊነት ወስዳችኋል። እነዚህን ልጆች ለእግዚአብሔር ለማሠልጠን— የክፉ ጠላትን የመጀመሪያ ዘዴ ጥንቃቄ በተሞላበት ቅናት ለመመልከት እና በእርሱ ላይ ሰንደቅ ዓለማን ለማንሳት ዝግጁ ለመሆን፣ ብታስተውሉ ወይም ባታስተውሉ ሸክሙ በእናንት ላይ ነው፡፡ ልጆቻችሁ ላይ የጸሎት እና የእምነት ምሽግ ገንቡ፣ ከዚያም በትጋት ተከታተሏቸው። ለቅጽበት እንኳ ከሰይጣንን ጥቃቶች ነጻ አይደላችሁም፡፡ ከንቁ እና ትጉህ ሥራ የምታርፉበት ጊዜ የላችሁም፡፡ የሥራ ምድባችሁን ትታችሁ ለቅጽበት እንኳ መተኛት የለባችሁም፡፡ ይህ በጣም ወሳኝ ጦርነት ነው፡፡ ዘላለማዊ ውጤቶች በዚህ ውስጥ ተካተዋል። ይህ ለራሳችሁና ቤለተሰባችሁ የሕይወት ወይም የሞት ጉዳይ ነው፡፡ 333 CGAmh 176.1

ጽኑ፣ ቆራጥ ውሳኔ አድርጉ—ወላጆች በአጠቃላይ በልጆቻቸው ላይ እጅግ ብዙ መተማመን ያሳያሉ፣ ብዙውን ጊዜ ወላጆች በእነርሱ ላይ እምነት ሲጥሉ እነርሱ በድብቅ ኃጢአቶች ውስጥ ይሆናሉ፡፡ ወላጆች፣ ልጆቻችሁን ጥንቃቄ በተሞላበት ቅንዓት ተከታተሏቸው። ስትነሱ እና ስትቀመጡ፣ ስትወጡና ስትገቡ “ትዕዛዝ በትዕዛዝ፣ ሥርዓት በሥርዓት፣ ጥቂት በዚህ፣ ጥቂት በዚያ” በማድረግ ምከሯቸው፣ ገስጹአቸው፡፡ ልጆች ገና በለጋ ዕድሜያቸው ሳሉ ለራሳችሁ አስገዟቸው፡፡ በብዙ ወላጆች ዘንድ ይህ በሚያሳዝን ሁኔታ ችላ ተብሏል። እነርሱ ከልጆቻቸው ጋር በተያያዘ መውሰድ ያለባቸውን ያህል ጥብቅ እና ቆራጥ አቋም አይወስዱም፡፡ 5 CGAmh 176.2

በትዕግሥት የከበረ ዘር መዝራት—“ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና።” ወላጆች ሆይ፣ ስራችሁ ልጆቻችሁ በእናንት ላይ እምነታቸውን እንዲጥሉ አድርጉ፣ እንዲሁም በፍቅር በትዕግስት የከበረ ዘር ዝሩ። በሥራችሁ ክብደት፣ ጭንቀት እና ድካም በጭራሽ ሳታጉረመርሙ፣ በእርካታ ሥሩ፡፡ በትዕግስት፣ በርህራሄ፣ በክርስቶስ ዓይነት ጥረት በክርስቶስ ኢየሱስ ፍጹም የሆነ አንድ ነፍስ ይዛችሁ ብትቀርቡ ሕይወታችሁ ከንቱ አይሆንም፡፡ የራስችሁን ነፍስ ተስፋ እና ትዕግስት ጠብቁ፡፡ በባህሪያችሁ ወይም በአመለካከታችሁ ላይ ምንም ዓይነት ተስፋ የመቁረጥ ምልክት አታስቀሩ፡፡ በእግዚአብሔር እርዳታ በጌታ የወይን ሥፍራ ሊሰራ እና ለኢየሱስ ነፍሳትን መማረክ የሚያስችል የባህሪይ ግንባታ በእጃችሁ ላይ ነው ያለው፡፡ ልጆቻችሁ ልማዶቻቸው እና ዝንባሌዎቻቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ዘወትር አበረታቷቸው። ለክብሩ ፍሬ እንድታፈሩ እግዚአብሔር በጉድለታችሁ ሲታገሳችሁ፣ ሲጠብቃችሁ እንደ ነበረ ሁሉ እናንተም በጉድለታቸው ታገሷቸው፡፡ ልጆቻችሁ በስመዘገቧቸው በጎ ባህሪያት ላይ የጎደሏቸውን ለመጨመር እንዲጥሩ አበረታቷቸው። 334 CGAmh 176.3

ለህግ መገዛትን አስተምሯቸው—አባቶችና እናቶች አስተዋዮች ሁኑ፡፡ ልጆቻችሁ ለህግ ተገዥ መሆን እንዳለባቸው አስተምሯቸው። 335 CGAmh 177.1

ልጅ በራሱ መንገድ እንዲሄድ፣ ለራሱ ሕግ ተገዢ እንዲሆን፣ እና እጅግ ስለምትወዱትም ለማረም ችላ ብላችሁ ብትተው ይህ ምህረት ወይም ርህራሄ አይደለም፡፡ እርሱን እና ሌሎች ሰዎችን ሁሉ የሚያስቸግር ባህሪይ እንዲያዳብር የሚፈቅድ ምን ዓይነት ፍቅር ነው? ከእንዲህ ዓይነቱ ፍቅር ራቁ! እውነተኛ ፍቅር የነፍስ ጊዜያዊና ዘላለማዊ የሆነውን መልካም ነገርን ይመለከታል። 336 CGAmh 177.2

ወላጆች ልጆችን ወደ ዓለም ለማምጣት እና ከባህል እና ክርስቲያናዊ ስልጠና ውጭ እንዲያድጉ ችላ ለማለት ምን መብት አላቸው? ወላጆች ኃላፊነት ሊወስዱ ይገባል፡፡ ቁጥጥርን አስተምሯቸው፤ መተዳደር እንጂ ማስተዳደር እንደሌለባቸው አስተምሯቸው። 9 CGAmh 177.3

አካላዊ፣ አእምሯዊ፣ እና መንፈሳዊውን ያቀናጁ—በአግባቡ ሚዛናዊ ባሕርይን ለመመስረት አካላዊ፣ አእምሯዊና መንፈሳዊ ችሎታዎች መዳበር አለባቸው። ይህንን በተሳካ ሁኔታ ለመፈጸም ልጆች ክትትል ማግኘት፣ መጠበቅ እና መሰልጠን አለባቸው፡፡ 337 CGAmh 177.4

የኢየሱስ አካላዊ አወቃቀር፣ እና የእርሱ መንፈሳዊ እድገት፣ “ሕጻኑ በቁመት አደገ” በሚሉ በእነዚህ ቃላት ቀርቦልናል፡፡ በልጅነት እና በወጣትነት ለአካላዊ እድገት ትኩረት መሰጠት አለበት፡፡ ከወጣትነት በኋላ ላለው ጊዜ የጥሩ ጤና መሠረት ይጣል ዘንድ ወላጆች ልጆቻቸውን በአመጋገብ፣ በመጠጥ፣ በአለባበስ እና በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጥሩ ልማዶችን ማሠልጠን አለባቸው፡፡ የአካል ኃይል እንዳይቀጭጭ እና ወደ ሙላት እንዲያድግ፣ አካል ልዩ እንክብካቤ ሊደረግለት ይገባል፡፡ በተገቢው የኃይማኖት ስልጠና፣ ልክ እንደ ክርስቶስ በመንፈስ ያድጉ ዘንድ ይህ ልጆችን እና ወጣቶችን በሚመች ሁኔታ ውስጥ ላይ ያደርጋቸዋል፡፡ 338 CGAmh 177.5

ጤና ከአዕምሮ እና ከግብረ-ገብ ጋር ይዛመዳል—እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ላለው የይገባኛል ጥያቄ የልጆቻችሁን የግብረ-ገብ ስሜቶችን ለማነሳሳት የእግዚአብሔርን ሕግጋት በአካላቸው መዋቅር እንዴት መታዘዝ እንዳለባቸው በልባቸውና በአዕምሮአቸው ውስጥ መቀረጽ አለበት፤ ምክንያቱም ጤና ከአእምሮአቸው እና ከግብረ-ገብ ጋር ትልቅ ግንኙነት አለው፡፡ እነርሱ ጤና እና የልብ ንጽህና ካላቸው፣ ከዚያም ለዓለም ለመኖር እና በረከት ለመሆን በተሻለ ሁኔታ ዝግጁ ይሆናሉ። አዕምሮአቸውን በትክክለኛው አቅጣጫ እና በትክክለኛው ጊዜ ሚዛናዊ ማድረግ እጅግ ወሳኝ ሥራ ነው፣ ምክንያቱም ይህ የሚወሰነው እጅግ ወሳኝ በሆነ ጊዜ በሚደረግ ውሳኔ ላይ ነው፡፡ CGAmh 178.1

ታዲያ ወላጆች የልጆቻቸው አካላዊ እና ግብረ-ገብ ጤንነት ቅድሚያና የላቀ ሥፍራ በመስጠት፣ በተረጋጋ ሁኔታ በትኩረት፣ በጥበብ እና በፍቅር ማሰብና መተግበር ይችሉ ዘንድ አዕምሮአቸው በተቻለ መጠን ግራ ከመጋባት፣ አላስፈላጊ ነገሮች ላይ ከመጨነቅ በተቻለ መጠን ነፃ መሆን ምን ያህል አስፈላጊ ነው፡፡ 12 CGAmh 178.2

ብዙውን ጊዜ የራሳቸው የወንጀል አስተዳደር ልጆች እንዲህ እንዲሆኑ ያደረጋቸው ቢሆንም ወላጆች ልጆቻቸውን ከቀድሞው ይልቅ ለመቆጣጠር በጣም አስቸጋሪ በመሆናቸው ይገረማሉ፡፡ በጠረጴዛዎቻቸው ላይ የሚያቀርቡት የምግብ ጥራት እና ልጆቻቸው እንዲመገቡ ማበረታታት የእንስሳነት ስሜትን የሚቀሰቅስ እና የግብረ-ገብ እና ማሰብ ችሎታዎችን የሚያዳክም ነው፡፡ 339 CGAmh 178.3

ንጹህ ምግብ አእምሮን መመገብ በጣም አስፈላጊ ነው— ወራዳ፣ አስነዋሪ አስተሳሰቦች ወይም እንደፈለጉ መሆን እንዳይኖር የምትወዷቸውን ልጆች ችሎታዎች እና ምርጫዎችን ያሰልጥኑ፣ አዕምሮአቸውን አስቀድማችሁ ያዙ፡፡ የክርስቶስ ጸጋ የክፉ ብቸኛ ማርከሻ ወይም መከላከያ ነው። ከፈለጋችሁ የልጆቻችሁ አእምሮ በንጹህ፣ ብልሹ ባልሆኑ ሀሳቦች ወይም በሁሉም ሥፍራ በሞሉ ክፋቶች - ማለትም ትዕቢት እና ቤዛቸውን በመርሳት እንዲሞላ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ አእምሮም ልክ እንደ አካል ጤና እና ጥንካሬን ለማግኘት ንጹህ ምግብ ሊያገኝ ይገባል፡፡ ልጆቻችሁ ከራሳቸው ውጭ እና ከራሳቸው በላይ የሚያስቡትን አንድ ነገር ስጧቸው። በንጹህ እና በተቀደሰ ሁኔታ ውስጥ የሚኖር አዕምሮ ቀላል፣ ከንቱ፣ ግብዝ እና ራስ ወዳድ አይሆንም፡፡ 340 CGAmh 179.1

የምንኖረው ሐሰተኛ እና ጥራዝ ነጠቅ የሆኑ ነገሮች ሁሉ ከእውነተኛው፣ ከተፈጥሮአዊው እና ዘላቄታ ካለው ነገር በላይ የሚሆንበት ዘመን ውስጥ ነው። አዕምሮ በተሳሳተ አቅጣጫ ከሚመራው ነገር ሁሉ ነፃ መሆን አለበት፡፡ ለአዕምሮ ኃይሎች ጥንካሬን በማይጨምሩ የማይረቡ ታሪኮች መሞላት የለበትም፡፡ ሀሳቦች ለአዕምሮ ከምናቀርበው ምግብ ጋር ተመሳሳይ ባህሪይ ይኖራቸዋል፡፡ 341 CGAmh 179.2

የድንቅ አዕምሮ ባለቤት መሆን በቂ አይደለም—በልጅዎ ድንቅ ብልህነት ሊደሰቱ ይችሉ ይሆናል፤ ነገር ግን በተቀደሰ ልብ ቁጥጥር ስር ካልሆነ በስተቀር፣ ከእግዚአብሔር ዓላማዎች በተቃራኒ የሚሰራ ይሆናል፡፡ በእኛ ላይ ካለው የእግዚአብሔር የይገባኛል ጥያቄ ከፍተኛ ስሜት ውጭ፣ ሌላው ነገር በዚህ ዓለምም ሆነ በመጪው ዓለም ለስኬት ወሳኝ የሆነውን የባህሪይ መረጋጋትን፣ የአእምሮን ዕውቀት እና ጥልቅ ግንዛቤ ሊሰጠን አይችልም፡፡ 342 CGAmh 179.3

በባህሪይ እድገት ውስጥ ከፍ ያሉ ነጥቦች ላይ ያልሙ—ልጆቻችንን ታታሪ እንዲሆኑ ማስተማር ከቻልን ከአደጋው ግማሹ አከተመ ማለት ነው፣ ምክንያቱም ስራ ፈትነት ሁሉም ፈተናዎች ወደ ኃጢአት እንዲያመሩ ስለሚያደርግ ነው። ልጆቻችን አይናውጣ ሳይሆኑ የማያስቸግሩ፣ ብኩኖች ሳይሆኑ በጎ አድራጊና ራሳቸውን የሚሰው፣ ንፉጎች ሳይሆኑ ቆጣቢዎች እንዲሆኑ እናስተምራቸው፡፡ ከሁሉም በላይ፣ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ስላለው የይገባኛል ጥያቄ፣ ሃይማኖትን ወደ ሁሉም የህይወት ክፍሎች የማስገባት ኃላፊነት እንዳለባቸው፣ እግዚአብሔርን አልቀው እንዲወዱ፣ እና ጎረቤታቸውን እንዲወዱ፣ ለደስታ አስፈላጊ የሆኑ ትናንሽ የህይወት ትህትናዎችን ችላ እንዳይሉ እናስተምራቸው፡፡ 343 CGAmh 179.4

የሰማይን ጥበብ ለማግኘት ጸልዩ—ወላጆች በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሚያስገኙላቸውን ባህሪያትን እንዲያዳብሩ ልጆቻቸውን በትክክል ማሠልጠን እንዲችሉ፣ ጥበብ እና መለኮታዊ እርዳታን ለማግኘት በትጋት ለእግዚአብሔር ማሳወቅ እና መጸለይ አለባቸው። ጭንቀታቸው በዓለም ውስጥ እድናቆትን እና ክብርን እንዲያገኙ ልጆቻቸውን እንዴት ማስተማር እንዳለባቸው ሳይሆን፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይት ያለውን ውብ ባህሪያትን ለመመስረት እንዴት ሊያስተምሯቸው እንደሚገባ መሆን አለበት፡፡ የወጣቶች አዕምሮ እንዴት መያዝ እንዳለበት ማወቅ ይቻል ዘንድ ሰማያዊ ጥበብን ለማግኘት ብዙ ጸሎትና ጥናት ያስፈልጋል፣ ምክንያቱም በአብዛኛው ወላጆች ለልጆቻቸው አእምሮ እና ፈቃድ በሚሰጡት መመሪያ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ 344 CGAmh 180.1

ሥነ ምግባራዊ እና መንፈሳዊ መመሪያ መሰጠት አለበት—ወላጆች ባህሪያቸው በደንብ ያደጉ ልጆችን—ፈተናን ለመቋቋም የግብረ-ገብ ኃይል የሚኖራቸው እና ህይወታቸው ለእግዚአብሔር ክብር እና ለባልንጀሮቻቸው በረከት የሚሆኑ ልጆችን ለዓለም የመስጠት ግዴታቸው ላይ መንቃት አለባቸው። በጽኑ መርሆዎች ወደ ተግባር ሕይወት የሚገቡ ሰዎች በዚህ የግብረ-ገብ ብልሹነት ጊዜ ውስጥ ጥቃት ሳይደርስባቸው ጸንተው መቆም እንዲችሉ ይዘጋጃሉ፡፡ 345 CGAmh 180.2

ልጆች ለራሳቸው እንዲመርጡ አስተምሯቸው—ወጣቶች እና ትናንሽ ልጆች ሰማያዊውን መጎናጸፊያ ይኸውም በምድሪቷ ቅዱስ የሆኑት ሁሉ የሚለብሱት “ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር” (ራዕይ 19፡8) እንዲመርጡ ይማሩ። ይህ ክርስቶስ እንከን የሌለበት ባህሪይ የሆነው ልብስ፣ ለእያንዳንዱ የሰው ልጅ በነፃ ይሰጣል፡፡ ነገር ግን የሚቀበሉት ሁሉ ይቀበሉት እና እዚህ ይለብሳሉ። CGAmh 180.3

ልጆች አዕምሮአቸውን ለንጹህ፣ ተወዳጅ ሀሳቦች ሲከፍቱ እና ተወዳጅ እና ጠቃሚ ተግባሮችን ሲያደርጉ፣ ውብ የሆነውን የእርሱን የባህሪይ ልብስ እየለበሱ እንደሆነ ይማሩ። ይህ ልብስ እዚህ ውብ እና ተወዳጅ ያደርጋቸዋል፣ ከዚህም በኋላ ለንጉሱ ቤተ መንግስት የመግቢያ አርማቸው ይሆንላቸዋል፡፡ 20 CGAmh 181.1