የልጅ አመራር

23/85

ምዕራፍ 21—ታታሪነት

ወጣቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ የሚሆንበት—ወጣቶች በአስተማማኝነት ደህንነታቸው የተጠበቀ ከሚሆንባቸው መንገዶች አንዱ ረብ ባለው ሥራ በመጠመድ ነው፡፡ ሙሉ ሰዓቶቻቸው ረብ ባለው እና በደስታ የተያዘ እንዲሆን የታታሪትን ልማድ የሚሰለጥኑ ልጆች በዕጣ ፈንታቸው የሚያማርሩበት እና ለቀን በሐሳብ የመባከን ሥራ ፈትነት ጊዜ የላቸውም፡፡ እነርሱ መጥፎ ልማዶችን ወይም ጓደኞችን ለመመስረት አነስተኛ አደጋ ውስጥ ናቸው፡፡ 203 CGAmh 115.1

በታታሪነት ውስጥ ያልተነገረለት ዋጋ አለ፡፡ ልጆች አንድ ፋይዳ ያለውን ነገር መስራትን ይማሩ፡፡ ወላጆች እዚህ ፋይዳ ላለው፣ ደስተኛ ሕይወት እና ለመጻኢ ከፍተኛ አገልግሎት እና ታላቅ ደስታ ልጆቻቸውን እንዴት በጥሩ ሁኔታ ማስተማር እንዳለባቸው እንዲገነዘቡ ከሰብዓዊ ጥበብ በላይ ያስፈልጋል። 204 CGAmh 115.2

ከዕድሜ እና ችሎታ ጋር የተመጣጠኑ ተግባሮችን መመደብ—ልጆች ከሕፃንነታቸው ጀምሮ ከዕድሜያቸው እና ከችሎታቸው ጋር ተመጣጣኝ የሆኑ ነገሮችን እንዲያከናውኑ ስልጠና ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ወላጆች ልጆቻቸው ይበልጥ ጥገኞች እንዳይሆኑ ማበረታታት አለባቸው፡፡ ከባባድ ችግሮች በቅርቡ በምድር ላይ ሊታዩ ነው፣ እናም ልጆች እነዚህን ችግሮች መግጠም በሚያስችላቸው አይነት ሁኔታ ስልጠና ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ 205 CGAmh 115.3

ልጆችዎ ፋይዳ ያላቸው፣ እንደ ዕድሜዎቻቸውም ኃላፊነቶችን የሚሸከሙ እንዲሆኑ አስተምሯቸው፣ ከዚያም ሥራ የመስራት ልማድ ለእነርሱ ሁለተኛ ተፈጥሮ ይሆናል፣ ፋይዳ ያለውም ስራ ለእነርሱ በጭራሽ አሳልቺ መስሎ አይታያቸውም። 4 CGAmh 115.4

የሥራ ፈትነት ፍሬ —ወላጆች ልጆቻቸው ምንም ነገር እንዳይሰሩ በመተው እግዚአብሔር የሰጣቸውን ሀላፊነቶች ችላ ከማለት የበለጠ የሚሰሩት ታላቅ ኃጢአት የለም። ምክንያቱም እነዚህ ልጆች ወዲያውኑ ሥራ ፈትነትን መውደድን ይማራሉ እናም ዘልዛላ፣ ከንቱ ወንዶች እና ሴቶች በመሆን ያድጋሉ፡፡ የራሳቸውን መተዳደሪያ ለመፈለግ ብቁ ሲሆኑ እና ወደ ሥራ ሲገቡ፣ ስንፍና በተሞላበት እና በጥገኝት ይሰሩና ጊዜያቸውን ሲያባክኑ ሥራቸውን በታማኝነት ያከናወኑ ያህል እኩል ይከፈለናል ብለው ያስባሉ፡፡ በዚህ የሰራተኛ መደብ እና ኃላፊነቱን በአግባቡ የሚወጣ ታማኝ ወኪል መሆን እንዳለበት በሚገነዘበው መካከል ልዩነት አለ፡፡ በየትኛውም የሥራ መስክ ቢሰማሩ፣ ወጣቶች “ለሥራ ከመትጋት የማይለግሙ፣ በመንፈስ የሚቃጠሉ፣ ለጌታ የሚገዙ” መሆን አለባቸው፤ በጥቂቱ ታማኝ ያልሆነ በብዙም ደግሞ ያልታመነ ነውና። 206 CGAmh 115.5

ልጆች ተገቢ የቤት ውስጥ ሥልጠና ካላቸው ሳይታሰብ ብዙዎች የሚቀበሉትን ትምህርት በማግኘት ጎዳና ላይ አይገኙም፡፡ ልጆቻቸውን አስተዋይ በሆነ መንገድ የሚወዱ ወላጆች ከደካማ ልምዶች ጋር እና የቤት ውስጥ ሥራዎችን እንዴት እንደሚሰሩ ባለማወቅ እንዲያድጉ አይፈቅዱላቸውም፡፡ ግድየለሽነት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የለውም፣ የእርሱን ሥራ ለመስራትም አመቺ አይደለም። 207 CGAmh 116.1

ጊዜን በጥበብ መጠቀም—ብዙ ሥራ ፈትነት ባለበት ሥፍራ ሰይጣን ህይወትንና ባህሪይን ለማበላሸት ከፈተናዎቹ ጋር ይሠራል። ወጣቶች ፋይዳ ባለው ሥራ ያልሰለጠኑ እንደሆነ፣ ሀብታምም ሆኑ ድሃ፣ አደጋ ላይ ናቸው፣ ምክንያቱም ሰይጣን በራሱ መንገድ መሠረት ሥራን ያገኝላቸዋል፡፡ በመርህ ያልተገደበ ወጣት ጊዜን እያንዳንዱ የሰው ልጅ መልስ የሚሰጥበት ውድ ሀብት፣ የእግዚአብሔር አደራ፣ አድርጎ አይቆጥረውም፡፡ 208 CGAmh 116.2

ልጆች አባት እና እናትን እንዲረዱ፣ እራሳቸውንም እንዲችሉ ጊዜያቸውን በጥሩ ሁኔታ ጥቅም ላይ ማዋልን መማር አለባቸው፡፡ ራሳቸውን አስፈላጊ የሆነውን ማንኛውንም ሥራ ከመሥራት በላይ አድርገው እንዲያስቡ ሊፈቀድላቸው አይገባም፡፡ 209 CGAmh 116.3

የጊዜ እሴት ከሂሳብ በላይ ነው። የባከነ ጊዜን በጭራሽ መልሶ ማግኘት አይቻልም... ፡፡ የሚባክኑ ጊዜያቶች ላይ መሻሻያ ማድረግ ውድ ሀብት ነው፡፡ 210 CGAmh 117.1

ማናቸውንም የስንፍና ልማዶችን ማሸነፍ—በቃሉ ውስጥ እግዚአብሔር የልጆችን ትምህርት እቅድን አውጥቷል፣ እናም ወላጆች ይህን ዕቅድ መከተል አለባቸው። ልጆቻቸውን ማናቸውንም የስንፍና ልማድ እንዲያሸንፉ ሊያስተምሯቸው ይገባል። እያንዳንዱ ልጅ በዓለም ውስጥ የሚያከናውነው ሥራ እንዳለው መማር አለበት፡፡ 211 CGAmh 117.2

ደካማነትና ስንፍና የክርስቲያን ዛፍ የሚሸከማቸው ፍሬዎች አይደሉም፡፡ 212 CGAmh 117.3

ስንፍና ትልቅ እርግማን ነው፡፡ እግዚአብሔር የሰው ልጆችን በነርቭ፣ የአካል ክፍሎች እና ጡንቻዎች ባርኮታል፣ እና እነርሱ በስንፍና ምክንያት እንዲበላሹ መተው ተገቢ አይደለም፣ ነገር ግን በእንቅስቃሴ እንዲጠናከሩ እና በጤንነት እንዲጠበቁ ያስፈልጋል። ምንም አለመሥራት ትልቅ አለመታደል ነው፣ ምክንያቱም ስራ ፈትነት ከዚህ በፊትም ሆነ ለወደፊት ለሰብአዊ ሰው እርግማን ሆኗል፡፡ 213 CGAmh 117.4

ልጆች፣ ቤት ውስጥ በጭራሽ ታማኝ ያልሆኑ ባለአደራዎች መሆናችሁን አታረጋግጡ፡፡ ኃላፊነትዎን ከመወጣት በጭራሽ አይለግሙ፡፡ በጥሩ ሁኔታ ጠንክሮ መሥራት ጽኑ ጅማትንና ጡንቻዎችን ይፈጥራል። የቤቱን ብልፅግና በማሳደግ ሂደት ውስጥ፣ እጅግ የበለፀጉ በረከቶችን ለራስዎ ያመጣሉ፡፡ 214 CGAmh 117.5

ከጨዋታ በፊት ሥራ መሰራት ያለበት ለምንድነው?—እናቴ ሥራ መሥራትን አስተማረችኝ። “ሁልጊዜ ከመጫወቴ በፊት ብዙ ሥራ መሥራት ያለብኝ ለምንድን ነው?” ብዬ እናቴን እጠይቃት ነበር፡፡ እርሷም “አዕምሮሽ ፋይዳ ያለውን ሥራ መስራት እንዲሰለጥን፣ እና ሌላው ነገር ደግሞ አንቺን ከመጥፎ ድርጊት ለመጠበቅ ነው፤ ስታድጊ ለዚህ ነገር ተመሰግኚኛለሽ” ትለኝ ነበር፡፡ “ከትናንሽ ሴት ልጆቼ [ሴት የልጅ ልጅ]” አንዷ ለምንድነው ሹራብ መሥራት ያለብኝ? ብላ ስትጠይቀኝ፣ አያቶች እንዴት ሹራብን መስራት እንደተማሩ ትነግሪኛላሽ? ለምን፣ መሰለሽ፣ እነርሱ ትናንሽ ሴት ልጆች ሳሉ ነው የጀመሩት” ስል መለስኩላት፡፡ 14 CGAmh 117.6

የዕለት ተዕለት መርሃ-ግብር ጠቀሜታ—በተቻለ መጠን በቀኑ ውስጥ ምን ምን መከናወን እንዳለበት ከግምት ውስጥ ማስገባት ጥሩ ነው። ትኩረትዎን የሚሹ የተለያዩ ተግባሮችን በማስታወሻ ይያዙ፣ እና እያንዳንዱን ሥራ ለማከናወን የተወሰነ ጊዜ ይመድቡ፡፡ እያንዳንዱ ነገር በጥንቃቄ፣ በደንብና እና በፍጥነት ይከናወን። የክፍል ውስጥ ሥራን ለማከናወን ዕጣ በእርሶ ላይ ቢወድቅ፣ ክፍሎቹ በደንብ አየር የሚያገኙ መሆናቸውን እና የአልጋ ልብስ ለፀሐይ ብርሃን የተጋለጠ መሆኑን ይመልከቱ። ስራውን ለመስራት በርካታ ደቂቃዎችን ይስጡ፣ እና ዓይንዎን የሚስቡ ወረቀቶችን እና መጽሃፍትን ማንበብ አይተው፣ ነገር ግን ለእራስዎ እንዲህ ይበሉ ፣ “አይ፣ ሥራዬን የማከናውንባቸው ብዙ ደቂቃዎች አሉኝ፣ እናም በተመደበላቸው ጊዜ ሥራዬን ማከናወን አለብኝ ... ፡፡” CGAmh 118.1

በተፈጥሮ የተወሰነ እንቅስቃሴ ያላቸው “ለሥራ ከመትጋት የማይለግሙ፣ በመንፈስ የሚቃጠሉ፣ ለጌታ የሚገዙ” የሚለውን የሐዋሪያውን ቃል በማስታወስ ንቁ፣ ፈጣን፣ ሀይለኛ ለመሆን ይሹ። CGAmh 118.2

ምግብን ለማዘጋጀት ዕጣ ቢወድቅብዎ፣ በጥንቃቄ ስሌትን ያድርጉ፣ እና ምግቡን ለማዘጋጀት ተገቢውን ሁሉ ጊዜ ይስጡ”፣ በጠረጴዛውም ላይ በጥሩ ቅደም ተከተል እና በትክክለኛው ሰዓት ያኑሩ። ከተመደበው ጊዜ አምስት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ ምግብ እንዲቀርብ ማድረግ ከአምስት ደቂቃዎች በኋላ ከማቅረብ ይልቅ የሚያስመሰግን ነው፡፡ ነገር ግን በዝግታ፣ እርምጃ ለመውሰድ በሚያዘገይ እንቅስቃሴዎች ቁጥጥር ስር ከሆኑ፣ ልምዶችዎ የሰነፍ አይነት ከሆኑ ከአጭር ሥራ ውስጥ ረጅም ስራን ይፈጥራሉ፣ እናም መታደስ እና ይበልጥ ፈጣን መሆን ከዘገምተኞች የሚጠበቅ ተግባር ይሆናል፡፡ ከፈለጉ፣ ዝብርቅርቅ እና የመዘግየት ልምዳቸውን ማሸነፍ ይችላሉ፡፡ ሰሃኖችን ሲያጥቡ ጠንቃቃ እና በተመሳሳይ ጊዜ ፈጣን ሥራ የሚሰሩ መሆን አለባቸው፡፡ እስከዚህ ድረስ ፈቃድዎን በሥራ ላይ ያውሉ፣ እጆችዎም ከፍጥነተዎ ጋር ይንቀሳቀሳሉ፡፡ 215 CGAmh 118.3

አካልን ከአእምሮ ጋር ያዋህዱ—ልጆች ከእኛ ጋር እንዲኖሩ ወደ ቤተሰቦቼ ተልከው “እናቴ ልብሶቼን እንዳጥብ አትፈልግም” ሲሉኝ፣ እኔም “መልካም፣ እኛ አጥበንልህ እኛ ጋር ለምትኖርበት ተጨማሪ ግማሽ ዶላር እናስከፍልህ?” ስላቸው ” ኦህ፣ አይሆንም! እናቴ ለእኔ ተጨማሪ መክፈል አትፈልግም።” ይሉኛል፡፡ ከዚያም እኔ “መልካም፣” “እንግዲህ በጠዋት የራስህን ሥራ ትሰራለህ፡፡” እኛን እንድትጠብቅ የእግዚአብሔር ዕቅድ አይደለም፡፡ አንተ በአልጋህ ላይ እያለህ እናትህ ተነስታ ቁርስ ከምታቀርብል ይልቅ፣ አንተው'እናቴ፣ ማለዳ አትነሺ፡፡ እነዚህን ሸክሞች እኛ እንሸከማለን፣ ተግባሮቹን እንፈጽማለን ማለት አለብህ፡፡’ ጠጉራቸው እያሸበተባቸው ያሉትን ጠዋት ጠዋት እንዲያርፉ ማድረግ አለባችሁ፡፡”እላቸው ነበር፡፡ CGAmh 119.1

ይህ ለምን አይሆንም? ችግሩ የቱ ጋር ነው ያለው? በቤተሰብ ውስጥ ልጆቻቸው ምንም ዓይነት ሸክም ሳይሸከሙ እንዲያድጉ ከሚፈቅዱላቸው ወላጆች ጋር ነው፡፡ እነዚህ ልጆች ወደ ትምህርት ቤት በሚሄዱበት ጊዜ፣ “እናቴ እኔ ሥራ እንድሰራ እንደማትፈልግ ትናገራለች” ይላሉ፡፡ እንደነዚህ ያሉ እናቶች ሞኞች ናቸው፡፡ ልጆቻቸውን ያበላሻሉ እና ከዚያ ትምህርት ቤት እንዲያበላሻቸው ይልኳቸዋል...፡፡ እነርሱ ሊኖራቸው ከሚችል እጅግ በጣም ጥሩ ሥነ-ምግባር ውስጥ ሥራ አንዱ ነው፡፡ ከእናቶቻቸውም ይልቅ ለእነርሱ ከባድ አይደለም፡፡ የአካል ሥራን ከአእምሮ ጋር ያዋህዱ፣ እናም የአዕምሮ ኃይሎች በተሻለ ሁኔታ ያድጋሉ፡፡ 216 CGAmh 119.2

መንገዶችን ይፍጠሩ—ወላጆች ልጆቻቸው ፋይዳ ባለው ነገር እንዲጠመዱ ለማድረግ መንገዶችን እና ዘዴዎችን መፍጠር አለባቸው፡፡ ልጆች እንደ ነጻ ስጦታ አንድ ነገር መስጠት ይችሉ ዘንድ የሚሰሩበት ትንሽ መሬት ይሰጣቸው። 217 CGAmh 119.3

በሚችሉት ሁሉ እንዲረዱዎት ያድርጓቸው፣ እነርሱ የሚሰጡዎትን ድጋፍ እንደሚያደንቁም ያሳዩዋቸው፡፡ የቤተሰቡ ድርጅት አካል እንደሆኑ እንዲሰማቸው ያድርጉ፡፡ ስራቸውን በፍጥነት እና በጥንቃቄ መስራት ይችሉ ዘንድ እንዲያቅዱ በተቻለ መጠን አእምሯቸውን እንዲጠቀሙ አስተምሯቸው። በተሰጣቸው የሥራ ሰዓት ውስጥ ምንም ደቂቃ እንዳይባክን በስራቸው ውስጥ ፈጣን እና ታታሪ እንዲሆኑ ያስተምሯቸው፡፡ 18 CGAmh 120.1

ሥራ የተከበረ ነው—ትናንሽ ልጆች ገና እጆቻቸው ትናንሽ እና ጥንካሬያቸውም ጥቂት ሆነው ሳሉ እንዲረዱን እናስተምራቸው፡፡ ሥራ ክቡር እንደሆነ፣ ከሰማይ ለሰው የተሰየመ፣ አእምሮ እና አካልን በጥሩ ሁኔታ ለማጎልበት አስፈላጊ ሆኖ በኤደን ውስጥ ለአዳምና ሔዋን በትዕዛዝ የተሰጣቸው እንደሆነ፣ በአእምሮአቸው ውስጥ እንዲሰርጽ እናርድግ። ጉዳት የለሽ አስደሳች ነገር ንቁ ታታሪነት ሲከተለው እንደሚያስደስት ብቻውን በጭራሽ በግማሽ እንኳ የሚያረካ እንዳልሆነ እናስተምራቸው፡፡ 218 CGAmh 120.2