የልጅ አመራር
ምዕራፍ 83—ሽልማት
የፍርድ ቀን ሥዕላዊ ትዕይንት— በአንድ ወቅት አንድ ብዙ ሕዝብ ተሰብስቦ ያየሁበት ሕልም አልሜ ነበር፤ እናም ድንገት ሰማያት ጥቁር ሆኑ፣ ነጎድጓድ ያስተጋባ ነበር፣ መብረቅ ብልጭ ድርግም ይል ነበር፣ እንዲሁም “ተፈጸመ” ሲል እጅግ ከባድ ከሆነ የነጎድጓድ ድምጽ በላይ የሆነ ድምፅ በሰማያት እና በምድር ይሰማ ነበር። ተሰብስበው ከነበሩ ሰዎች የተወሰኑት በገረጣ ፊት “አቤት፣ እኔ ዝግጁ አይደለሁም” በማለት በልቅሶ ዋይታ ወደ ፊት ወጡ፡፡ “ለምን አልተዘጋጃችሁም? በጸጋ የሰጠኋችሁን ዕድሎችን ለምን አልተጠቀማችሁም?” የሚሉ ጥያቄዎች ተጠየቁ፡፡ ለቅሶው በጆሮዬ ላይ እያቃጨለ ነቃሁ፡፡ ዝግጁ አይደለሁም፤ አልዳንኩም — ጠፍቻለሁ! ጠፍቻለሁ! ለዘላለም ጠፍቻለሁ!” CGAmh 535.1
በእኛ ላይ ካሉ ከባድ ሀላፊነቶች አንጻር፣ መጪውን ጊዜ ለመጋፈጥ ምን ማድረግ እንዳለብን እንድንገነዘብ እናሰላስል፡፡ በዚያ ቀን በእግዚአብሔር እና በምህረቱ ችላ መባል እና መናቅን፣ እውነቱን እና ፍቅሩን ባለመቀበል እንጋፈጣለን? በመጨረሻው ቀን በተከበረው ጉባኤ ላይ፣ አጽናፈ ዓለሙ በሚሰማበት፣ የኃጢአተኛው ኩነኔ ምክንያት ይነበባል። ለመጀመሪያ ጊዜ ወላጆች የልጆቻቸው ምስጢራዊ ሕይወት ምን እንደ ሆነ ይረዳሉ፡፡ ልጆች በወላጆቻቸው ላይ ምን ያህል ጥፋቶች እንደሠሩ ይመለከታሉ፡፡ የተሰወረው ነገር ስለሚገለጥ የልብን ሚስጥሮች እና አነሳሽ አጠቃላይ መንስኤዎች ይገለጣሉ። ከፍርዱ ጋር የተያያዙ ክብር ያላቸው ነገሮች ላይ ያሾፉ ሰዎች አስፈሪ እውነታውን ሲጋፈጡ ከስካራቸው ይበርዳሉ፡፡1117 CGAmh 535.2
የእግዚአብሔርን ቃል የናቁ ሰዎች ያኔ በመንፈስ አነሳሽነት ከተጻፉ ጽሁፎች ደራሲ ጋር ፊት ለፊት ይገናኛሉ፡፡ ስለ የፍርድ ቀን ምንም መረጃ ሳይኖረን መኖር አንችልም፤ ለረጅም ጊዜ የዘገየ ቢሆንም፣ አሁን ቅርብ ነው፣ በደጅም ላይ ነው፣ እጅግም ይፈጥናል፡፡ የሊቀ መልአኩ መለከት በቅርቡ ህዋንን ያሸብራል፣ ሙታንንም ይቀሰቅሳል፡፡ እረኛው ፍየሎችን ከበጎች እንደሚለይ ሁሉ በዚያን ቀን ኃጢአን ከጻድቃን ይለያሉ፡፡ CGAmh 536.1
እግዚአብሔር “ልጆቻችሁ የት አሉ?” በማለት ሲጠይቅ— እግዚአብሔር የሰጣቸውን ኃላፊነቶች ችላ ያሉ ወላጆች በፍርድ ላይ ያን ቸልተኝነት መጋፈጥ አለባቸው፡፡ ጌታ በዚያን ጊዜ “ለእኔ እንድታሠለጥኑልኝ የሰጠኋችሁ ልጆች የት አሉ? በቀኜ ለምን አልሆኑም?” ብዙ ወላጆች ያኔ ጥበብ የጎደለው ፍቅር የልጆቻቸውን ጉድለቶች እንዳያዩ ዓይኖቻቸውን እንዳሳወረ እና ለሰማይ ገጣሚ የማያደርጓቸውን ክፉ ባህሪያትን እንዲያሳድጉ እንዳደረገ ይመለከታሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ለልጆቻቸው ጊዜ እና ትኩረት፣ ፍቅር እና ርህራሄ እንዳልሰጧቸው ይመለከታሉ፤ ግዴታቸውን ችላ ማለታቸው ልጆቹ የሆኑትን እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡ 1118 CGAmh 536.2
ወላጆች፣ ዕድላችሁን ካልተጠቀማችሁ እግዚአብሔር ያዝንባችኋል፤ ምክንያቱም በፍርድ ቀን እግዚአብሔር “በመንጋዬ፣ በውብ መንጋዬ ላይ ምን አደረጋችሁ?” ይላል፡፡ CGAmh 536.3
ወደ ሰማይ ደርሳችኋል እንበል እና ከልጆቻችሁ መካከል ማንም እዚያ አልተገኘም፡፡ እግዚአብሔርን፣ “እነሆ እኔ፣ ጌታ ሆይ፣ የሰጠኸኝም ልጆች እነሆ” ማለት እንዴት ትችላላችሁ? ሰማይ የወላጆችን ችላ ማለትን መረጃ ይይዛል፡፡ ይህም በሰማይ መጽሐፍት ላይ ተመዝግቧል፡፡3 CGAmh 536.4
ቤተሰቦች በእግዚአብሔር ፊት ይገመገማሉ— ወላጆች እና ልጆች የመጨረሻውን ምዘና ሲጋፈጡ፣ ምን ዓይነት ትዕይንት ይቀርባል! ህይወታቸው በግብረ ገብ ብልሹ የሆኑ፣ ለምግብ አምሮት እና ለሚያረክስ ክፉ ምግባር ባሪያዎች የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ልጆች እንዲህ እንዲሆኑ ካደረጓቸው ወላጆቻቸው ጋር ፊት ለፊት ይጋፈጣሉ፡፡ ከወላጆቹ በቀር ይህን አስፈሪ ኃላፊነት መሸከም ያለበት ማን ነው? ጌታ እነዚህን ወጣቶች ብልሹዎች አደረጋቸውን? በፍፁም! ከመላእክት በጥቂት አሳንሷቸው በአምሳሉ ፈጥሯቸዋል፡፡ ታዲያ አስፈሪ የሕይወት ባህሪይን የመቅረጽ ሥራ የሰራው ማን ነው? የእግዚአብሔር አሻራ እንዳያርፍባቸው እና እጅግ ርኩስ ከመሆናቸው የተነሳ በቅዱሱ ሰማይ ውስጥ ካሉት ከንጹህ መላእክት ጋር ምንም ሥፍራ እንዳይኖራቸው ባህሪያቸውን ማን ቀየረ? በተዛባ የምግብ አምሮቶች እና ምኞቶች ረገድ የወላጆች ኃጢአት ወደ ልጆች ተላልፏልን? ደግሞም በአግባቡ እነርሱን ከማሠልጠን ቸል የምትል የተድላ አፍቃሪ እናት በተሰጣት ንድፍ መሠረት ሥራዋን አጠናቅቃለችን? እነዚህ ሁሉ እናቶች ልክ እነርሱ እንዳሉ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ይገመገማሉ፡፡1119 CGAmh 536.5
በሰማይ ውስጥ ሥዕላዊ መዝገብ አለ— ወላጆች እና ልጆች እያንዳንዳቸው በየቀኑ ባህሪይ እየቀረጻችሁ መሆኑን እና የዚህ ባህሪይ ገፅታዎች በሰማይ መዝገብ ላይ እየታተመ መሆኑን አስታውሱ፡፡ አንድ አርቲስት የወንዶችንና የሴቶች ፎቶዎችን እንደሚያነሳ፣ የፊት ገጽታዎችን ቅብ ሸራ ላይ እንደሚያስተላልፍ ሁሉ እግዚአብሔርም የሕዝቦቹን ፎቶግራፎች እያነሳ ነው። ምን ዓይነት ሥዕል መነሳት ይፈልጋሉ? ወላጆች፣ ለጥያቄው መልስ ስጡ! ታላቁ ሊቅ አርቲስት በመንግሥተ ሰማያት መዝገብ ውስጥ ምን ዓይነት ሥዕል እያነሳችሁ ይገኛል? ... ይህንን አሁን መወሰን አለብን፡፡ ከዚህ በኋላ ሞት በሚመጣበት ጊዜ ባህሪይ ውስጥ ያሉትን ጠማማ ሥፍራዎችን ለማረም ጊዜ አይኖርም፡፡ CGAmh 537.1
ለእኛ በየግላችን ይህ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ መሆን አለበት፡፡ በየቀኑ የእኛ ምስል ለጊዜው እና ለዘለዓለም እየተወሰደ ነው። እያንዳንዳቸው “ዛሬ የእኔ ምስል እየወሰደ ነው” ይበሉ፡፡ በየሰዓቱ፣ በየዕለቱ እራሳችሁን ጠይቁ፣ “ቃሌ ለሰማያዊ መላእክት ምን ይመስላቸዋል? በብር ምስሎች ውስጥ እንዳሉ የወርቅ ፖም ናቸው ወይንስ እንደ ሚወርድ በረዶ ፣ የሚያቆስሉ እና የሚጎዱ ናቸው?”… CGAmh 537.2
ቃላቶቻችን እና ድርጊቶቻችን ብቻ ሳይሆን ሀሳቦቻችን እኛ ምን እንደምንመስል ስዕል ይስላሉ፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ነፍስ ጥሩ እና መልካም ያድርግ፡፡ ስለ እናንተ የተሰራው ስዕል ከማታፍሩበት አንዱ ይሁን፡፡ የምንወደው እያንዳንዱ ስሜት በገጽታ ላይ የራሱን አሻራ ያኖራል። በሰማያዊ መዝገብ ላይ እንዲሆን የምንመኘውን የቤተሰባችን መዝገብ እንድናስመዘግብ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ 1120 CGAmh 537.3
ግድየለሾች ናችሁ?— አቤት፣ ወላጆች የልጆቻቸውን ዘላለማዊ ደህንነት በሚገባ በጸሎት እና በጥንቃቄ ይመልከቱ! ግድየለሾች ነን ወይ? ብለው ራሳቸውን ይጠይቁ፡፡ ይህንን የተከበረ ሥራ ችላ ብለን ይሆን? ልጆቻችን የሰይጣን ፈተናዎች ስፖርት እንዲሆኑ ፈቅደናልን? ልጆቻችን ተሰጥኦአቸውን፣ ጊዜያቸውን እና ተጽዕኖአቸውን እውነትን በመቃወም እና ክርስቶስን በመቃወም እንዲጠቀሙ ስለፈቀድን ከእግዚአብሔር ጋር ማስተካከል ያለብን የከበረ ኃላፊነት የለብንምን? እንደ ወላጆች ኃላፊነታችንን ችላ በማለት የሰይጣን መንግሥት ተገዥዎች ቁጥር እንዲጨምር አላደረግንምን? 1121 CGAmh 538.1
እናቶች ልጆቻቸውን በአግባቡ ማስተማርን ቸል ካሉ፣ ልጆቻቸውን ለታዛዥነትና ተገዥነት ለማሰልጠን ጊዜ እና ጥንቃቄ የተሞላበት ትዕግሥት ቢያሳዩ ኖሮ ይሆን ከነበረው ይልቅ ሸክሞቻቸውን እና ችግሮቻቸው የበለጠ ከባድ በማድረግ ችላ ማለታቸው በእነርሱ ላይ እንደገና አጸፋ መልስ ይኖረዋል፡፡ እሾህ ሥር እንዳይሰድ እና የተትረፈረፈ ምርት እንዳያፈራ እናቶች የልጆቻቸውን ባህሪያትን ምስረታ የመጀመሪያ እና ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ጉዳይ ማድረጋቸው በመጨረሻ ሽልማትን ያስገኛል፡፡7 CGAmh 538.2
ልጆች ታማኝ ያልሆኑ ወላጆችን ይኮንኗቸዋል— የእግዚአብሔር እርግማን በእርግጥም ታማኝ ባልሆኑ ወላጆች ላይ ይወርዳል። እዚህ የሚያቆስላቸውን እሾህ መትከላቸው ብቻ ሳይሆን ፍርድ በሚሆንበት ጊዜ ታማኝ አለመሆናቸውንም መጋፈጥ አለባቸው፡፡ ብዙ ልጆች በፍርድ ቀን ይነሱ እና ወላጆቻቸው እነርሱን ባለመከልከላቸው ሳቢያ የጠፉ እንደሆነ እነርሱን በመክሰስ ያወግዟቸዋል፡፡ የሐሰት ርህራሄ እና የወላጆች ጭፍን ፍቅር የልጆቻቸውን ጥፋት ያለ እርማት እንዲያልፏቸው ሰበብ በመሆን ልጆቻቸው በዚህ ምክንያት የጠፉ ሲሆን የነፍሳቸው ደም ታማኝነት በጎደላቸው ወላጆች ላይ የሚያርፍ ይሆናል፡፡ 1122 CGAmh 538.3
ልጆች ለታማኝ ወላጆች የምስጋና መታሰቢያ ያቀርቡላቸዋል— ፍርድ በሚቀመጥበት ጊዜ እና መጽሐፍት ሲከፈቱ፤ “መልካም አድርገሃል” የሚል የታላቁ ፈራጅ ቃል በሚታወጅበት ጊዜ እና የዘላለማዊነት የክብር ዘውድ በአሸናፊው ራስ ላይ ሲያርፍ፣ ብዙዎች ከአጽናፈ ሰማይ በተሰበሰበው ጉባኤ ፊት ዘውዳቸውን ከፍ በማድረግ ወደ እናታቸው እየጠቆሙ “በእግዚአብሔር ጸጋ ታግዛ የሆንኩነትን ሁሉ እንድሆን አድርጋለች፡፡ መመሪያዋ፣ ጸሎቷ፣ ለዘላለም በመዳኔ ተባርኳል።” 9 CGAmh 539.1
የታማኝነት ሥልጠና ውጤቶች ይገለጣሉ— ከራስ ወዳድነት ነጻ በሆነ መንፈስ የሠሩ ሁሉ የድካማቸውን ፍሬ ያያሉ። የእያንዳንዱ ቀና መርህ እና የከበረ ተግባር አሠራር ይታያል። የዚህ የተወሰነ ነገር ውጤት እዚሁ የምናይ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በዓለም ላይ እጅግ የከበረ የሥራ ውጤት ለሠሪው ጊዜያዊ ሕይወት ላይ መተያቱ ምን ያህል ያነሰ ነው! ከአቅማቸው እና ከእውቀታቸው በላይ ለሆነው ከራስ ወዳድነት ነፃ ሆነው እና ሳይታክቱ የሚሰሩ ስንቶች ናቸው! ወላጆች እና አስተማሪዎች በመጨረሻው እንቅልፍ ጊዜያቸው፣ የሕይወታቸው ሥራ በከንቱ የተከናወነ እየመሰላቸው ያንቀላፋሉ፤ ታማኝነታቸው ፈጽሞ የማያቋርጥ የበረከት ምንጮችን እንደከፈቱ አያውቁም፤ በእምነት ብቻ ያሠለጠኗቸውን ልጆች ለባልንጀሮቻቸው በረከት እና መነሳሳት እንደሚሆኑ ይመለከታሉ፣ ተጽዕኖውም በሺህ እጥፍ ራሱን ይደጋግማል...፡፡ ሰዎች ከመቃብሮቻቸው በላይ ሌሎች የተባረኩ አዝመራዎችን የሚያጭዱትን ዘር ይዘራሉ፡፡ ሌሎች ፍሬውን እንዲበሉ ዛፎችን ይተክላሉ፡፡ መልካም ሥራ ለመስራት የሚንቀሳቀሱ ወኪሎችን ማቆማቸውን በማወቅ እዚህ ረክተዋል፡፡ የእነዚህ ሁሉ ድርጊት እና ውጤት በመጪው ዓለም የሚታይ ይሆናል፡፡ 1123 CGAmh 539.2
ወላጆች ልጆቻቸውን ይዘው ወደ ተስፋይቱ ምድር ሊመጡ ይችላሉ— እግዚአብሔር በሕይወት ጎዳና ሁሉ ላይ እንዲበራ ከዙፋኑ ብርሃን እንዲበራ አድርጓል። እንደ የጥንቷ እስራኤል ሁሉ በቀን የደመና ዓምድ፣ በሌሊትም የእሳት አምድ በፊታችን እየሄደ ነው፡፡ የጥንት የእግዚአብሔር ሕዝቦች ልጆቻቸውን ይዘው ወደ ተስፋይቱ ምድር የማምጣት ልዩ ዕድል እንደነበረባቸው ሁሉ በዛሬው ጊዜም የክርስቲያን ወላጆች ልዩ ዕድል አላቸው፡፡ 1124 CGAmh 539.3
ለእግዚአብሔር የሚሆን ቤተሰብ ትፈልጋላችሁ፤ ቤተሰባችሁ የእግዚአብሔር እንዲሆን ትፈልጋላችሁ፡፡ ወደ ከተማይቱ በሮች ወስዳችኋቸው “እነሆኝ እኔ፣ ጌታ ሆይ፣ የሰጠኸኝም ልጆች እነሆ” ማለት ትፈልጋላችሁ፡፡ እነርሱ ለአካለ መጠን የደረሱ ወንዶች እና ሴቶች ሊሆኑ ይችላሉ፣ ሆኖም ግን እነርሱ ሁሉም እኩል ልጆቻችሁ ናቸው፤ አሸናፊዎች ሆነው እስኪቆሙ ድረስ ትምህርታችሁ እና በንቃት እነርሱን መጠባቃችሁ በእግዚአብሔር ዘንድ ተባርኳል፡፡ “እነሆኝ እኔ፣ ጌታ ሆይ፣ የሰጠኸኝም ልጆች እነሆ” ማለት ትችላላችሁ፡፡ 1125 CGAmh 540.1
የተሰበሩ የቤተሰብ ሰንሰለቶች እንደገና ይጠገናሉ— ኢየሱስ እየመጣ ነው፣ በደመናዎች እና በታላቅ ክብር እየመጣ ነው። ብዙ የሚያበሩ መላእክት እርሱን አጅበው ይመጣሉ። እርሱ የሚወዱትን እና ትእዛዛቱን የጠበቁትን ለማክበር እና ወደ እርሱ ለመውሰድ ይመጣል። እነርሱንም ሆነ ተስፋዎቹን አልረሳቸውም፡፡ የቤተሰብ ሰንሰለት እንደገና ይጠገናል። 1126 CGAmh 540.2
የሐዘንተኛ እናት መጽናኛ— ስለ ልጅሽ ድነት በተመለከተ ጥያቄ አቅርበሻል። “ሕፃናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተውአቸው አትከልክሏቸውም፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ናትና” የሚሉት የክርስቶስ ቃላት መልስሽ ናቸው። ትንቢቱን አስታውሺ፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል:-የዋይታና የልቅሶ ድምጽ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እምቢ አለች...፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል:- ድምጽሽን ከልቅሾ አይንሽንም ከእንባ ከልክዪ፤ ለሥራሽ ዋጋ ይሆናልና፣ ከጠላትም ምድር ይመለሳሉ፡፡ ለፍጻሜሽም ተስፋ አለ፣ ይላል እግዚአብሔር፣ ልጆችሽም ወደ ዳርቻቻ ይመለሳሉ፡፡” CGAmh 540.3
ይህ ተስፋ የአንቺ ነው፡፡ በጌታ መጽናናት እና መታመን አለብሽ፡፡ ብዙ ልጆች ከመከራው ጊዜ በፊት እንደሚሞቱ ጌታ ብዙ ጊዜ መመሪያ ሰጥቶኛል። ልጆቻችንን እንደገና እናያቸዋለን፡፡ በሰማያዊ አደባባዮች ውስጥ እነርሱን እናገኛቸዋለን፣ እናውቃቸዋለንም፡፡ በጌታ ታመኑ፣ አትፍሩም፡፡ 1127 CGAmh 541.1
ልጆች በእናቶች ክንዶች እቅፍ ላይ ይደረጋሉ— አቤት፣ አስደናቂ ቤዛነት! ለረጅም ጊዜ የተነገረለት፣ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው፣ በጉጉት ሲታሰብ የነበረው፣ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ግንዛቤ ያልተገኘለት ነገር ነው። CGAmh 541.2
ሕያዋን ጻድቃን “በድንገት፣ በቅጽበተ አይን” ይለወጣሉ። በእግዚአብሔር ድምፅ ይከብራሉ፤ የማይሞቱ ሆነው ከሚነሱ ቅዱሳን ጋር አሁን ጌታቸውን በአየር ላይ ለመገናኘት ይነጠቃሉ፡፡ መላእክት “ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ፡፡” ትናንሽ ልጆች በቅዱሳን መላእክት አማካይነት በእናቶቻቸው እቅፍ ላይ ይደረጋሉ፡፡ ለረጅም ጊዜ በሞት የተለዩ ወዳጆች መቼም ላይለያዩ በመገናኘት የደስታ መዝሙር እያዜሙ አብረው ወደ እግዚአብሔር ከተማ ይወጣሉ።1128 CGAmh 541.3
ለረጅም ጊዜ በተስፋ ሲጠበቅ የነበረ ቀን— የመጀመሪያዎቹ ጥንዶች አሳዛኝ የሆነ እርምጃቸውን ከኤደን ካዞሩበት ቀን ጀምሮ እምነት ያላቸው ልጆች የአውዳሚውን ኃይል ለመስበር እና አጥተውት ወደ ነበረው ገነት እንደገና ለመመለስ ቃል የተገባውን ሰው መምጣት ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡1129 CGAmh 541.4
መንግስተ ሰማያትን በመከራ ካገኘን ርካሽ ነው ...፡፡ ክብሩን ለመውረስ ምን መሆን አለብን እንዳየሁ እና ከዚያም ኢየሱስ ይህን የበለፀገ ርስት ሊያስገኝልን ምን ያህል እንደተሰቃየ ባየሁ ጊዜ፣ በእርሱ ድህነት እና ስቃይ እኛ ባለጸጎች እንድንሆን እርሱ እንደተሰቀየ በማወቅ በክርስቶስ ስቃይ እንድንጠመቅ፣ በፈተናዎች እንዳናፈገፍግ፣ ነገር ግን በትዕግስት እና በደስታ እንድንሸከመው ጸለይኩኝ፡፡ 1130 CGAmh 541.5
ሰማይ ሁሉ ነገራችን ነው!— ሰማይ ለእኛ ሁሉ ነገራችን ነው፡፡ ይህን ጉዳይ አደጋ ላይ መጣል የለብንም፡፡ እዚህ ላይ ምንም ነገር አደጋ ላይ መጣል የለብንም፡፡ እርምጃዎቻችን የጌታን ትዕዛዝ የሚከተሉ መሆናቸውን ማወቅ አለብን፡፡ በታላቁ ድል የመንሳት ተግባር ላይ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ እርሱ ለሚያሸንፉት ዘውድ ይሰጣቸዋል፡፡ ለጻድቃን ነጭ ልብስ ይሰጣቸዋል፡፡ ክብርን፣ ሞገስን እና ዘላለማዊነትን ለሚሹ ሁሉ ዘላለማዊነትን ይሰጣቸዋል፡፡ ወደ እግዚአብሔር ከተማ የሚገባ ሁሉ ድል አድራጊ ሆኖ ይገባል፡፡ እንደ እግዚአብሔር ልጅ እንጂ እንደ ተኮናኝ ወንጀለኛ ሆኖ አይገባም፡፡ እንዲሁም ወደዚያ ለሚገቡ ሁሉ የሚደረግ አቀባበል “እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፣ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ” ይሆናል። ማቴ 25 34፡፡ 1131 CGAmh 542.1
የክርስቶስ ደስታ ተካፋዮች— በሁለቱም በሮች በኩል የመላእክት አጃቢዎችን እናገኛለን፤ ወደ ውስጥ ዘልቀን በምንገባበት ጊዜ “እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፣ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ” ሲል ይናገራል፡፡ እዚህ ጋር የደስታ ተካፋዮች እንድትሆኑ ይነግራችኋል፣ ደግሞስ ያ ምንድን ነው? አባቶች ሆይ፣ እርሱ የነፍሳችሁን ድካም የማየት ደስታ ነው። እናቶች ሆይ እርሱ የጥረታችሁን ዋጋ የማየት ደስታ ነው። እነሆ ልጆቻችሁ፤ የሕይወት አክሊል በራሳቸው ላይ ነው፣ እናም የእግዚአብሔር መላእክት በጥረታቸው ልጆቻቸውን ለኢየሱስ ክርስቶስ የማረኩትን እናቶች ስሞችን ዘላለማዊ ያደርጋሉ፡፡ 1132 CGAmh 542.2
የከበረ የድል ቀን— አሁን ቤተክርስቲያን ትግል ላይ ናት። አሁን እኛ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ ለጣዖት አምልኮ የተሰጠ በጨለማ ውስጥ ካለው ዓለም ጋር እየተጋፈጥን ነው…፡፡ ነገር ግን ውጊያው የሚካሄድበት፣ ድሉ የሚገኝበት ቀን ይመጣል፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሰማይ እንደሆነው ሁሉ በምድርም ይሆናል...፡፡ ሁሉም የክርስቶስ ጽድቅ ካባ የሆነውን የምሥጋናና የውዳሴ ልብሶችን ለብሰው ደስተኞች እና የተባበሩ ቤተሰቦች ይሆናሉ። ተፈጥሮ ሁሉ እጅግ በሚልቅ ተወዳጅነቱ ለእግዚአብሔር የምስጋና እና የውዳሴ መታሰቢያ ያቀርባል፡፡ ዓለም በሰማይ ብርሃን ትታጠባለች፡፡ የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን ይሆናል፣ የፀሐይ ብርሃን ደግሞ ከአሁኑ በሰባት እጥፍ ይልቃል፡፡ ዓመታት በደስታ ይቀጥላሉ። እግዚአብሔር እና ክርስቶስ “ከእንግዲህ ወዲህ ኃጢአት አይኖርም፣ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም” ብለው ሲያውጁ በትዕይንቱ ላይ የንጋት ኮከቦች በአንድነት ይዘምራሉ፣ የእግዚአብሔርም ልጆች ለደስታ እልል ይላሉ፡፡ CGAmh 542.3
እነዚህ መጻኢ የክብር ራእዮች፣ በእግዚአብሔር እጅ የተሳሉ ትዕይንቶች፣ ለልጆቹ ተወዳጅ መሆን አለባቸው…፡፡ CGAmh 543.1
እነዚህን የማይታዩ ነገሮች ራዕዮችን ዘወትር በፊታችን ማስቀመጥ አለብን፡፡ ለዘላለማዊ ነገሮች እና ለጊዜያዊ ነገሮች ትክክለኛውን ዋጋ መስጠት የምንችለው በዚህ መንገድ ነው። ለከፍተኛ ሕይወት በሌሎች ላይ ተጽዕኖ እንድናሳድር ኃይል የሚሰጠን ይህ ነው፡፡ 1133 CGAmh 543.2
እግዚአብሔር “መልካም ሰርተሃል” ይል ይሆን?—በታላቁ ነጭ ዙፋን ፊት ስትቆሙ፣ ያኔ ስራችሁ እንዳለ ይገለጣል። መጽሐፍት ተከፍተው፣ የእያንዳንዱ ሕይወት መዝገብ ይታወቃል፡፡ በዚያ ሰፊ ሕዝብ መካከል ብዙዎች ለራዕዮቹ ዝግጁ አይደሉም፡፡ በአንዳንድ ጆሮዎች ላይ “በሚዛን ተመዝነህ ቀለህ ተገኝተሃል” የሚሉ ቃላት በአስገራሚ ግልጽነት ይደመጣሉ። ፈራጁ በዚያ ቀን ለብዙ ወላጆች “ግዴታችሁን በግልጽ የሚያሳይ ቃሌ ነበራችሁ፡፡” አስተምህሮውን ለምን አልታዘዛችሁም? የእግዚአብሔር ድምፅ እንደሆነ አላወቃችሁም ነበር? እንዳትሳሳቱ መጻሕፍትን እንድትመረምሩ አላዘዝኳችሁምን? የራሳችሁን ነፍስ ብቻ አላጠፋችሁም፣ ነገር ግን በአስመሳይ አምልኮአችሁ ሌሎች ብዙዎችን አሳስታችኋል፡፡ ከእኔ ጋር ምንም ድርሻ የላችሁም ፡፡ ከእኔ ተለዩ፣ ከእኔ ተለዩ” ይላቸዋል፡፡ CGAmh 543.3
ሌላው ቡድን በክርስቶስ በመታመን ገርጥተው እና እየተንቀጠቀጡ ቆመዋል፣ ሆኖም ግን በራሳቸው ብቁ አለመሆን ስሜት ጫና ሥር ነበሩ። የጌታን ውዳሴ በደስታ እንባ እና በምስጋና ይሰማሉ። የማያቋርጥ የድካም ፣ ሸክም የመሸከም ፣ የፍርሃት እና የጭንቀት ቀናት ከመልአክ በገና ሙዚቃ ይልቅ ውብ የሆነ ያ ድምፅ “መልካም፣ አንተ በጎ ታማኝ ባሪያ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” የሚሉ ቃላት ሲደመጡ ይረሳሉ፡፡ የተዋጀው ሠራዊት፣ በእጃቸው የድል የዘንባባ ቅርንጫፍ ይዘው፣ በራሳቸው ላይ ዘውድ ጭነው ቆመዋል፡፡ እነዚህ በታማኝነት፣ በትጋት ሥራ ለሰማይ ብቁ የሆኑ ናቸው፡፡ በምድር ላይ የተከናወነው የሕይወት ሥራ በጥሩ ሁኔታ እንደተከናወነ በሰማይ ቤት ዕውቅና ይሰጠዋል፡፡ CGAmh 543.4
ወላጆች ሊነገር በማይችል ደስታ ለልጆቻቸው የተሰጠውን ዘውድ፣ ካባውን፣ በገናን ይመለከታሉ። የተስፋና የፍርሃት ቀናት ተጠናቀዋል፡፡ በእንባ እና በጸሎት የተዘራው ዘር በከንቱ የተዘራ ሊመስል ይችላል፣ ሆኖም ግን መከራቸው በመጨረሻ በደስታ ይሰበሰባል። ልጆቻቸው ተቤዥተዋል፡፡ አባቶች እና እናቶች ሆይ፣ በዚያ ቀን የልጆቻችሁ ድምፅ የደስታ መዝሙርን ከፍ አድርገው ያዜማሉን? The Signs of the Times, July 1, 1886. 1134 CGAmh 544.1