የልጅ አመራር
ክፍል 19—የፍርድ ዘመን
ምዕራፍ 82—ሰዓቱ ረፍዷል
ሰይጣን ሠራዊቱን እያሰለፈ ነው— ሰይጣን ሠራዊቱን እያሰለፈ ነው፣ በመሆኑም በግላችን ከፊታችን ላለው አስፈሪ ተጋድሎ ዝግጁ ነን? የጠላቶቻችንን አቋም እና የትግል ስልቶቻቸውን ለመረዳት እራሳችንን እና ቤተሰባችንን እያዘጋጀን ነውን? ልጆቻችን በሁሉም የመርህ እና የኃላፊነት ጉዳዮች ላይ ጽኑ እና የማይለወጡ እንዲሆኑ የውሳኔ ልምዶች እየቀረጹ ነውን? ሁላችንም የዘመን ምልክቶችን እንድንገነዘብ እናም በተጋድሎው ወቅት እግዚአብሔር መጠጊያችን እና ከለላችን ይሆን ዘንድ እራሳችንን እና ልጆቻችንን ማዘጋጀት እንድንችል ዘንድ እጸልያለሁ።1108 CGAmh 530.1
ለድንገተኛ መጥለቅለቅ ተዘጋጁ— መተላለፍ ገደቡን ደርሷል ማለት ይቻላል። ግራ መጋባት ዓለምን አጥለቅልቋታል፣ ደግሞም በሰው ልጆች ላይ ታላቅ ሽብር በቅርቡ ይመጣል። መጨረሻው እጅግ ቀርቧል፡፡ የእግዚአብሔር ህዝብ እንደ ድንገተኛ መጥለቅለቅ በዓለም ላይ ሊመጣ ላለው ነገር መዘጋጀት አለበት፡፡ CGAmh 530.2
ጊዜያችን ውድ ነው፡፡ ለመጪው፣ የዘላለማዊነት ሕይወት ለማዘጋጀት የምንችልባቸው ጥቂት፣ በጣም ጥቂት፣ የአመክሮ ቀናት አሉን፡፡2 CGAmh 530.3
ብዙ ቤተሰቦች አልተዘጋጁም— በሌሊት ራእይ በሰንበት እና እሁድ ቀን፣ በሰዎች ፊት ምስክርነትን የምሰጥ ይመስለኝ ነበር። በእነዚህ በሁለቱም አጋጣሚዎች ሙሉ በሙሉ ጥቅጥቅ ያለ ግዙፍ ድንኳን ውስጥ ያለሁ ይመስለኝ ነበር፡፡ ጌታ ለህዝቡ ወሳኝ የሆነ መልእክት ሰጠኝ፡፡ ሸክሜ ጌታን ለመገናኘት ዝግጁ ላልሆኑት ቤተሰቦቻችን ነበር፡፡ በጥብቅ ልብን በመመርመር እና የዓላማ ትጋት ጌታን መሻትን ለሕዝቦቻችን የማመልከት አንድ ልዩ ሸክም በላዬ ላይ ነበር…፡፡ CGAmh 530.4
በእውነት የተለወጡ ወላጆች ሕይወታቸውን በእግዚአብሔር ቃል ስልጠና ሥር እያደረጉ መሆናቸውን በቤት ሕይወታቸው ውስጥ ያሳያሉ ...፡፡ ለእናት እና አባት ትክክለኛ የልጆቻቸው ሥልጠና የሕይወታቸው እጅግ አስፈላጊ ሥራ ነው፡፡ 1109 CGAmh 530.5
ወሳኝ ጥያቄዎች ለወላጆች— አባቶች እና እናቶች፣ መዝገባችሁ እንዴት ነው ያለው? ለአደራችሁ ታማኞች ናችሁን? ልጆቻችሁ ላይ የአስተሳሰብ፣ የቃል እና የድርጊት ርኩሰት እንደሚያስከትልባቸው የምታውቁትን አካሄድ የመከተል ዝንባሌ እንዳያችሁ፣ በመጀመሪያ እግዚአብሔር እንዲረዳችሁ በመጠየቅ የሚደርስባቸውን አደጋዎችን ለማሳየት ሞክራችኋልን? በራሳቸው የመረጡት መንገድ የመከተልን አደጋ ለእነርሱ አመልክታችኋልን? እናቶች፣ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ሥራ— ሟች ለሆነው ሰብአዊ ሰው የተሰጠውን ትልቁን ሥራ ችላ ብላችኋልን? እግዚአብሔር የሰጣችሁን ኃላፊነት ከመሸከም አሻፈረኝ ብላችኋልን? በፊታችን ላለው የመከራ ጊዜ፣ የእግዚአብሔር ፍርድ ርኩስ እና ያልተቀደሱ ሰዎች ላይ በሚወርድበት ጊዜ፣ ልጆቻችሁ የፈለጉትን ሁሉ እንዲያደርጉ ስለተዋችኋቸው ይረግሟችሁ ይሆን? 1110 CGAmh 531.1
በመልእክቱ አዲስ የሆኑ ወላጆች መመሪያ ያስፈልጋቸዋል— የመጨረሻውን የምህረት መልእክት ለዓለም የሚያስተላልፉ ሁሉ ለወላጆች የቤት ኃይማኖትን በተመለከተ መመሪያ መስጠት ግዴታቸው እንደሆነ ሊሰማቸው ይገባል፡፡ ታላቁ የተሃድሶ እንቅስቃሴያቸው ለአባቶች፣ ለእናቶች እና ለልጆች የእግዚአብሔርን ሕግ መርሆዎች በማቅረብ መጀመር አለበት፡፡ የሕጉ መጠይቆች ሲቀርቡ እና ወንዶችና ሴቶች ታዛዥ የመሆን ግዴታቸውን ካመኑ ለእነርሱ ብቻ ሳይሆን ለልጆቻቸውም የውሳኔ ኃላፊነታቸውን አሳዩአቸው፡፡ ዓለምን ጠራርጎ ወደ ጥፋት እየወሰዷት ካሉ ክፋቶች ለአምላክ ቃል መታዘዝ ብቸኛው መከላከያ መሆኑን አሳየአቸው።5 CGAmh 531.2
ወጣቶቻችን እርዳታ እና ማበረታቻ ይፈልጋሉ— ለወጣቶች የምንሰራበት ጊዜአችን እና ዕድላችን አሁን ነው፡፡ አሁን በአደገኛ ቀውስ ውስጥ እንደሆንን እና እውነተኛ እግዚአብሔርን መምሰልን እንዴት መለየት እንደምንችል ማወቅ እንደሚያስፈልገን ንገሯቸው፡፡ ወጣቶቻችን ሊረዱ፣ ሊነቃቁ እና ሊበረታቱ ይገባል፣ ሆኖም ግን በትክክለኛው መንገድ መሆን አለበት፤ ምናልባት እንደሚፈልጉት ሳይሆን የተቀደሰ አእምሮ እንዲኖራቸው በሚረዳ መንገድ መሆን አለበት። ከምንም በላይ የሚቀድስ ኃይማኖት ያስፈልጋቸዋል፡፡ 1111 CGAmh 531.3
አትዘግይ— መጪ ክስተቶች በመንገዳችን ላይ ጥላቸውን እያጠሉ ነው። አባቶች እና እናቶች፣ አሁን ለልጆቻችሁ ከፍተኛ ጥረት እንድታደርጉ እማፀናችኋለሁ፡፡ በየቀኑ ኃይማኖታዊ ትምህርት ስጧቸው፡፡ እግዚአብሔርን እንዲወዱ እና ለትክክለኛው መርሆዎች ታማኞች እንዲሆኑ አስተምሯቸው። በመንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ተጽዕኖ በሚመራው በከበረ ልባዊ እምነት አሁን ሥሩ፡፡ አንድ ቀን፣ አንድ ሰዓት አትዘግዩ፡፡ 1112 CGAmh 532.1
ጥንቃቄ የተሞለበት ሥራ ሥሩ— ወላጆች፣ ልባችሁን በእግዚአብሔር ፊት ዝቅ አድርጉ። ልጆቻችሁ ላይ ጥንቃቄ የተሞለበት ሥራ ጀምሩ፡፡ ልጆቻችሁን መሄድ በሚገባቸው መንገድ የማሰልጠ ቃሉን ቸል ማለታችሁን ይቅር እንዲላችሁ ጌታን ተማጸኑ፡፡ ስህተቶቻችሁን እና ውድቀቶቻችሁን ማየት እንድችሉ ብርሃን እና መመሪያን፣ ጥሩ ህሊና እና ግልጽ ማስተዋልን ጠይቁ። እግዚአብሔር ከትሁት እና ከተጸጸተ ልብ የሚመጡ እንደነዚህ ያሉትን ጸሎቶችን ይሰማል። 8 CGAmh 532.2
መናዘዝ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል— ለቤተሰቦቻችሁ ያለባችሁን ግዴታ መወጣት ካልቻላችሁ፣ ኃጢአታችሁን በእግዚአብሔር ፊት ተናዘዙ። ልጆቻችሁን በዙሪያችሁ በመሰብሰብ ችላ ባይነታችሁን ተቀበሉ፡፡ ቤት ውስጥ ተሃድሶ ለማምጣት ፍላጎት እንዳላችሁ ንገሯቸው፣ ደግሞም ቤት መሆን ያለበትን እንዲሆን ለማድረግ እንዲረዷችሁ ጠይቋቸው። በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የሚገኙትን መመሪያዎችን አንብቡላቸው። ከእነርሱ ጋር አብራችሁ ጸልዩ፤ እንዲሁም ሕይወታቸውን እንዲያተርፍ እና በመንግስቱ ውስጥ መኖሪያ ቤት ለማዘጋጀት እንዲረዳቸው እግዚአብሔርን ጠይቁት። በዚህ መንገድ የተሃድሶ ሥራ ልትጀምሩ ትችላላችሁ፤ ከዚያም የጌታን መንገድ መጠበቁን ቀጥሉበት። 1113 CGAmh 532.3
ለልጆች የጥብቅ ታዛዥነት አርአያ ሁኗቸው— ልጆች በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ እግዚአብሔርን መታዘዝ አስፈላጊ መሆኑን ይገነዘቡ ዘንድ የወላጆች ልዩ ሥራ የእግዚአብሔርን ሕጎች ለልጆቻቸው ግልጽ ማድረግ እና ለእነርሱ መታዘዝን ማበረታታት ነው፡፡ ይህ የሙሴ ሥራ ነበር፡፡ እርሱ ለወላጆቻቸው ጥብቅ የመታዘዝ ምሳሌ የመስጠት ግዴታቸውን ወላጆችን ማዘዝ ነበረበት፡፡ ከማናቸውም ነገሮች በላይ ዛሬ በቤት ሕይወት ውስጥ መከናወን ያለበት ይህ ሥራ ነው፡፡ ይህ የሦስተኛውን መልአክ መልእክት ማጀብ አለበት፡፡ ወላጆች የእግዚአብሔርን ሕግ መተላለፍ ምን ማለት እንደሆነ ለልጆቻቸው ማስተማርን ቸል ለማለት አለማወቅ ሰበብ መሆን አይችልም፡፡ ብዙ ብርሃን በርቷል፤ በመሆኑም ማንም በጨለማ መራመድ አያስፈልገውም፣ ማንም አላዋቂ መሆን የለበትም። እግዚአብሔር የእስራኤል ልጆች አስተማሪ እንደነበረው ሁሉ ዛሬም በእርግጥ አስተማሪያችን ነው፣ እናም ሁሉም ህጎቹን የመታዘዝ እጅግ በተቀደሱ ግዴታዎች የታሰሩ ናቸው። 1114 CGAmh 533.1
ለድነታቸው ጸልዩ፣ ሥሩም— ልብ ራስን ስለ መቆጣጠር እና ራስን ስለ መካድ መሰልጠን እንዳለበት ልጆቻችሁን አስተምሯቸው። የሕይወት ዓላማዎች ከእግዚአብሔር ሕግ ጋር የሚስማሙ መሆን አለባቸው፡፡ ልጆቻችሁ ከክርስቶስ ተለይተው በማደጋቸው በጭራሽ እርካታ አይሰማችሁ፡፡ በራድ እና ግድየለሾች ሆነው ሳሉ በጭራሽ ምቾት አይሰማችሁ፡፡ ቀንና ሌሊት ወደ እግዚአብሔር ጩኹ፡፡ ለልጆቻችሁ ነፍስ ድነት ጸልዩ፣ ሥሩም፡፡ “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው።” ይህ የባህሪይን ሚዛን የሚጠብቅ መንኮራኩር፣ ዋና ምንጭ ነው። ያለ ጌታ ፍርሃት የተፈጠሩበትን ታላቅ ዓላማ መፈፀም ይሳናቸዋል፡፡ 1115 CGAmh 533.2
እንደ ባህርይ ገንቢዎች ሥሩ— የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ወላጆች የባህሪይ ገንቢነት ኃላፊነታቸውን ይበልጥ በተሟላ ሁኔታ መገንዘብ አለባቸው፡፡ ልጆቻቸውን በመቀደስ እና ለእነርሱ በመስራት የእርሱን ሥራ የማጠናከር ዕድልን እግዚአብሔር በፊታቸው አስቀምጧል፡፡ በቤቶቻቸው ኃይማኖታዊ ተጽዕኖዎች የተነሳ ልባቸውን ለእርሱ አሳልፈው የሰጡ እና የህይወታቸውን ከፍተኛ አገልግሎት ለእርሱ ለመስጠት የሚሄዱ ብዙ ወጣቶች ከህዝባችን ቤት ተሰብስበው ሲወጡ ማየት ይፈልጋል። በቤት ኃይማኖት መመሪያ፣ በጠዋት እና በማታ አምልኮ ተጽዕኖ፣ እግዚአብሔርን የሚወዱ እና የሚፈሩ ወላጆች የማይለዋወጥ ምሳሌ በመመራት እና በመሰልጠን፣ እግዚአብሄርን አስማሪያቸው አድርገው ለእርሱ መገዛትን የተማሩ እና እንደ ታማኝ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ለእርሱ ተቀባይነት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅተዋል። እንደነዚህ ያሉት ወጣቶች የክርስቶስን ኃይል እና ፀጋ በዓለም ውስጥ ለመወከል ተዘጋጅተዋል። 1116 CGAmh 534.1