የልጅ አመራር

54/85

ምዕራፍ 52—ትምህርት ቤትን መምረጥ

አስከፊ ኪሳራዎችን እናስተናግዳለን— አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሄር ልጆቻቸውን ለማሠልጠን ምን ማድረግ እንዳለባቸው ለመኑሄና ለሚስቱ እንደነገራቸው ሁሉ በሚሰማ ድምጽ ለወላጆች ቢናገራቸው ምኞቴ ሆኖ አገኛለሁ፡፡ የቤት ውስጥ ሥልጠናን ችላ በማለት በእያንዳንዱ የሥራ ዘርፍ ውስጥ አስከፊ ኪሳራዎችን እናስተናግዳለን፡፡ የኃይማኖት ተጽዕኖ ቅድሚያ የሚያገኙበትን የትምህርት ቤቶች አስፈላጊነት በአእምሯችን ወስጥ እንዲሰርጽ ያደረገው ይህ ነበር። ታላቁን ክፋት ለመጻረር ማንኛውንም ነገር ማደረግ ካለብን በየሱስ ኃይል እናደርገዋለን፡፡ 586 CGAmh 286.1

አንድ ወሳኝ ጉዳይን መጋፈጥ — ወላጆች፣ አሳዳጊዎች፣ ልጆቻችሁን ተፅኖዎቻቸው በትክክለኛው ሁኔታ ከተከወነ የቤት ውስጥ ትምህርት ቤት ጋር ተመሳሳይ የሆኑ የሥልጠና ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያኑሯቸው፤ እነዚህ ትምህርት ቤቶች አስተማሪዎች ልጆችን ከአንዱ ጉዳይ ወደ ሌላ ጉዳይ የሚያስኬዱበት ትምህርት ቤት፣ እና መንፈሳዊ ሁኔታው የመዳን ሽታ የሚሆኑበት ትምህርት ቤቶች መሆን አለባው…፡፡ መንፈሳዊ ከሆኑ ወላጆች ጥበብን ያዘለ ትምህርት እና ስልጠና የተቀበሉ ወጣቶቻችን በእውነት እየተቀደሱ መቀጠል አለመቀጠላቸው በዋናነት የሚመረኮዘው ቤታቸውን ትተው ከሄዱ በኋላ ክርስቲያናዊ ትምህርት ከሚሹ መካከል ሲሆኑ ነው፡፡ 587 CGAmh 286.2

የትኞቹ የአስተማሪዎች ክፍል ነው?— ዓለም ላይ ሁለት የአስተማሪዎች ክፍል አለ፡፡ አንደኛው ክፍል እግዚአብሔር የብርሃኑ መተላለፊያ መስመር ያደረጋቸው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሰይጣን እንደ ወኪል የሚጠቀምባቸው፣ ክፉ ለመሥራት ጠቢባን የሆኑ ናቸው፡፡ አንደኛው ክፍል የእግዚአብርን ባህሪይ የሚያሰላስሉ እና እግዚአብሔር ወደ ዓለም በላከው በየሱስ እውቀት የሚያደጉ ናቸው፡፡ ይህ ክፍል ነፍሳትን ለማነቃቃት ሰማያዊ ግንዛቤን፣ ሰማያዊ ጥበብን ለማምጣት ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ የሰጡ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ የተፈጥሮ ችሎታውን ለእግዚአብሔር የስገዛ እና ሐሳቡ በክርስቶስ ምርኮ ሥር የገባ ነው፡፡ ሌላው ከጨለማ ንጉስ ጋር ሕብረት የሚፈጥር፣ ሌሎችን የክፋትን ዕውቀት ለማስተማር ምቹ ሁኔታን ለማግኘት ዘወትር ንቁ የሚሆን ክፍል ነው፡፡ 588 CGAmh 286.3

እግዚአብሔር መሰረት የሆነበትን ትምህረት ቤት ምረጡ — ከቤት ውጭ የሚሆን ትምህርት ቤትን ለልጆቻቸው በማቀድ ረገድ፣ ወላጆች ከዚህ ወዲያ እነርሱን ወደ የሕዝብ ትምህርት ቤት መላክ ከአደጋ ነጻ አለመሆኑን መገንዘብ እና መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት ያደረገ ትምህርት ወደሚያገኙበት ትምህርት ቤት እነርሱን ለመላክ ጥረት ማድረግ አለባቸው፡፡ በእያንዳንዱ ክርስቲያን ወላጅ ላይ የጌታን እውቀት እንዲያገኙ እና ለእግዚአብሔር ፈቃድ እና መንገድ በመታዘዝ የመለኮታዊ አካል ተካፋዮች እንዲሆኑ የሚያስችል ትምህርት ለልጆቹ የመስጠት ከባድ ግዴታ አለበት፡፡ 589 CGAmh 287.1

እግዚአብሔር ለእስራኤል የሰጠውን ምክር ላይ ይመልከቱ—የእግዚአብሔር ፍርድ በግብፅ ምድር ላይ በወረደ ጊዜ፣ እስራኤላውያን ልጆቻቸውን በቤታቸው ውስጥ እንዲያቆዩ ብቻ ሳይሆን ከብቶቻቸውም እንኳ ከእርሻቸው እንዲያመጡ እግዚአብሔር መመሪያ ሰጥቶ ነበር…፡፡ CGAmh 287.2

የእግዚአብሔር ፍርድ በግብፅ ምድር ላይ ሲወርድ በነበረበት ጊዜ እስራኤላውያን ልጆቻቸውን በቤታቸው ውስጥ እንደጠበቁ ሁሉ እኛም በዚህ አደገኛ ጊዜ ልጆቻችን ከዓለም ለይተን መጠበቅ አለብን፡፡ የእግዚአብሔር ትእዛዛት እኛ ከምንረዳው እጅግ የላቀ መሆኑን ልናስተምራቸው ይገባል፡፡ እነርሱን የሚጠብቁ የእግዚአብሔር ሕግ ተላላፊዎችን ልምድ አይኮርጁም፡፡ CGAmh 287.3

ወላጆች ትምህርቶቹን በመታዘዝ የእግዚአብሔርን ቃል በአክብሮት መያዝ አለባቸው። በዚህ ዘመን ለሚኖሩ ወላጆችም ሆነ ለእስራኤላውያን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል: “እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውም ይህን ቃል በልብህ ያዝ፡፡ ለልጆችህም አስተምረው፣ በቤትህም ስትቀመጥ፣ በመንገድህም ስትሄድ፣ ስትተኛም ስትነሳም ተጫወተው፡፡ በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ፡፡ በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው፡፡” CGAmh 287.4

ይህ ግልፅ የሆነ መመሪያ ቢኖርም እንኳን፣ አንዳንድ የእግዚአብሔር ህዝብ ልጆቻቸው በግብረ ገብ ብልሹ ከሆኑ ሰዎች ጋር የሚቀላቀሉበት የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲማሩ ይፈቅድላቸዋል። በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ልጆቻቸው መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትም ሆነ መሠረታዊ መርኾዎቹን መማር አይችሉም። ክርስቲያን ወላጆች ሆይ፣ ልጆቻችሁ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ መርኾዎችን ይማሩ ዘንድ ዝግጅት ማድረግ አለባችሁ። 590 CGAmh 288.1

የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ገለል ሲደረግ; ልጆች ግራ ይጋባሉ — ልጆቻችን ከአምላክ ቃል ጋር የሚስማሙ ሐሳቦችን በሕዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ካሉ አስተማሪዎች ይቀበላሉ? ኃጢአት በእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚጠላ ተደርጎ ይቀርባልን? ለእግዚአብሔር ትእዛዛት ሁሉ መታዘዝ እንደ የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ ይስተማራል? ልጆቻችንን እውነትን እንዲማሩ ወደ ሰንበት ትምህርት ቤት እንልካቸዋለን፤ ከዚያም ወደ መደበኛ ትምህርት ቤት ሲሄዱ ውሸትን ያዘሉ ትምህርቶችን እንዲማሩ ይሰጣቸዋል፡፡ እነዚህ ነገሮች አዕምሮን ግራ ያጋባሉ፣ እንዲህም መሆን የለበትም፤ ወጣቶች እውነትን የሚያጣምሙ ሀሳቦችን ከተቀበሉ፣ የዚህ ትምህርት ተጽዕኖ እንዴት ይቀለበሳል? CGAmh 288.2

እንደዚህ በመሰሉ ሁኔታዎች ውስጥ ከእኛ መካከል አንዳንድ ወጣቶች ለሃይማኖታዊ ጥቅሞች አድናቆት የሌላቸው መሆኑ ያስደንቀናል? ወደ ፈተና መግባታቸው ያስደንቀናልን? ችላ ተብለው ባሉበት፣ ጉልበታቸው ምንም ጥቅም ለሌላቸው ፈንጠዚያዎች መዋሉ፣ ለሃይማኖታቸው ያላቸው ምኞት መዳከሙ እና መንፈሳዊ ህይወታቸው የጨለመ መሆኑ ያስደንቀናል? አእምሮ እንደሚመገበው የምግብ ባህሪይ ነው፣ አዝመራውም ከተዘራው ዘር ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ እነዚህ ሀቆች ከመጀመሪያዎቹ የወጣቶቹ ዓመታት ጀምሮ ትምህርታቸው ላይ ዘብ የመቆምን አስፈላጊነት በበቂ ሁኔታ አያሳዩምን? ወጣቶች በእግዚአብሔር ዕውነት ግድየለሾች ከሚሆኑ ይልቅ አብዛኛውን ጊዜ እንደ ትምህርት ተቀባይነት ላለው ነገር በተወሰነ ደረጃ በድንቁርና ቢያድጉ አይሻልምን? 591 CGAmh 288.3

በሁሉም ቤተ ክርስቲያኖቻችን ውስጥ ትምህርት ቤቶች ያስፈልጋሉ— በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያሉ መምህራን ሚስዮናውያን የሆኑበት፣ በሁሉም ቤተክርስቲያኖቻችን ውስጥ ትምህርት ቤቶች መኖር አለባቸው፡፡ የሰንበትን ጠባቂዎች ልጆችን በሳይንስ ብቻ ሳይሆን በቅዱሳት መጻሕፍትም ጭምር በማስተማር ወሳኝ ሥራ ውስጥ አስተማሪዎች የበኩላቸውን እንዲወጡ ሥልጠና መስጠቱ አስፈላጊ ነው፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች የተቋቋሙ እና እግዚአብሔርን በሚፈሩ ወንዶች ወይም ሴቶች የሚመሩ እነዚህ ትምህርት ቤቶች እንዳስፈላጊቱ ልክ እንደ ነቢያት ትምህርት ቤቶች በተመሳሳይ መርሆዎች ላይ መገንባት አለባቸው፡፡ 592 CGAmh 289.1

በከተሞች ውስጥ የቤተክርስቲያን ትምህርት ቤቶች ያስፈልጋሉ— ልጆች ቤት ውስጥ እንዲማሩ የእግዚአብሔር ዕቅድ የሆነበትን ልጆች ወደ ትምህርት ቤት ተልከው እንደገና በእናቶቻቸው ቁጥጥር ሥር የሚሆኑበት እና ፋይዳ የመስጠትን የተግባር ትምህርት የማግኘት ምቹ አጋጣሚ እንዲኖራቸው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ቤት ማቋቋሙ እጅግ አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው…፡፡ CGAmh 289.2

በአሁኑ ጊዜ ከከተሞች መውጣት የማይችሉ ልጆችን ለማዳን እና ለማስተማር ብዙ መደረግ ይችላል፡፡ ይህ ከፍተኛ ጥረታችንን የሚሻ ጉዳይ ነው። ለልጆች በከተሞች ውስጥ የቤተክርስቲያን ትምህርት ቤቶች መመስረት አለባቸው፣ እንዲሁም እነዚህ አስፈላጊ ሆኖ በተገኙበት ከእነዚህ ትምህርት ቤቶች ጋር ተያያይዘው የከፍተኛ ትምህርቶችን ለማስተማር ዝግጅት መደረግ አለበት፡፡8 CGAmh 289.3

ለትናንሽ ቤተክርስቲያናት ትምህርት ቤቶችን አቋቁሙ— ልጆቻቸውን ለማስተማር ሲሉ ትልልቅ ትምህርት ቤቶቻችን ወደተቋቋሙባቸው አካባቢዎች የሚዛወሩ ብዙ ቤተሰቦች ባሉበት ሥፍራዎች በመቆየት ለጌታ የተሻለ አገልግሎት መስጠት ይችሉ ነበር፡፡ ልጆች በአከባቢያቸው ሁለ ገብ እና ተግባራዊ የክርስቲያን ትምህርት የሚያገኙበት የቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት እንዲመሰረት እነርሱ አባል የሆኑበትን ቤተክርስቲያን ማበረታታት አለባቸው፡፡ እነርሱ እዚያ አስፈላጊ ባለመሆናቸው ምክንያት በመንፈሳዊ ስራ ፈትነት የማያቋርጥ ፈተና ለውድቀት ወደሚዳረጉበት ትላልቅ ቤተ ክርስቲያናት ከሚሄዱ ይልቅ የእነርሱ እርዳታ የሚፈለግበት፣ ትናንሽ አብያተ-ክርስቲያናት ውስጥ ቢቆዩ ለልጆቻቸው፣ ለእራሳቸው እና ለእግዚአብሄር ሥራ እጅጉን የተሻለ ነው። CGAmh 290.1

ጥቂት የሰንበት ጠባቂዎች ባሉበት ቦታ ሁሉ ወላጆች ልጆቻቸው እና ወጣቶቻቸው የሚማሩበት የመደበኛ ትምህርት ቤት ቦታን በማመቻቸት መተባበር አለባቸው። እንደ ቅዱስ ሚስዮናዊ፣ ልጆችን ሚስዮናውያን እንዲሆኑ በሚመራ አይነት መንገድ የሚያስተምር የክርስቲያን መምህር መቅጠር አለባቸው። በጋራ ጥናት ቅርንጫፎች፣ መጽሐፍ ቅዱስ የሁሉም ጥናቶች መሠረት እና ሕይወት ሆኖ በተለመዱ ዘርፎችን ጥልቅ ትምህርት የሚሰጡ መምህራን ይቀጠሩ፡፡ 593 CGAmh 290.2

አማኞች ጥቂት በሆኑባቸው አካባቢዎች፣ ሁለት ወይም ሦስት አብያተ ክርስቲያናት መጠነኛ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ቤትን ለማቋቋም አንድነት ይፍጠሩ፡፡10 CGAmh 290.3

በዚህ ጊዜ ጌታ እንዲሠራ የሚሻውን ሥራ ለመሥራት በመተባበር ወላጆች የእነዚህን አነስተኛ የማስተማሪያ ማዕከላት አስፈላጊነት ቢገነዘቡ ጠላት ለልጆቻችን ያቀዳቸው እቅዶች ይፈርስ ነበር።11 CGAmh 290.4

የቤት ውስጥ ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤቶች — በተቻለ መጠን ሁሉም ልጆቻችን የክርስትና ትምህርት የማግኘት ዕድል ሊኖራቸው ይገባል፡፡ CGAmh 291.1

ይህንን ለመስጠት አንዳንድ ጊዜ የቤት ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤቶችን መመስረት አለብን፡፡ ጎረቤት ያሉ ብዙ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን በማስተማር ረገድ ወላጆች የሚፈልጉትን ያን ዕርዳታ የሚሰጥ ትሑት እና ፈሪሃ አምላክ ያለው አስተማሪ ቢቀጠሩ ጥሩ ነው። ይህ በገለልተኛ ሥፍራ ለሚኖሩ ለአያሌ የሰንበት ጠባቂ ቡድኖች ታላቅ በረከት እና አንዳንድ ጊዜ ከምትከተሏቸው ትላልቅ ትምህርት ቤቶቻችንን እንዲከታተሉ ትናንሽ ልጆቻችሁን ከቤት አውጥቶ የመላክ ዕቅድ የበለጠ ጌታን የሚያስደስት ዕቅድ ነው፡፡ CGAmh 291.2

የሰንበት ጠባቂች ትናንሽ ቡድኖቻችን በጎረቤቶቻቸው ፊት ብርሃንን ከፍ አድርገው መያዝ አስፈላጊ ናቸው፤ እና የጥናት ሰዓት ሲያጠናቀቅ ለወላጆቻቸው ድጋፍ የሚሆኑ ልጆች በቤታቸው ውስጥ ይፈለጋሉ። ትናንሽ ልጆች በጌታ ትእዛዝን የተከተለ የወላጅን ተግሣጽ ሊያገኙ የሚችሉበት በሥርዓት የተያዘ የክርስቲያን ቤት፣ ለእነርሱ ምርጥ ቦታ ነው። 594 CGAmh 291.3

በገለልተኛ ሥፍራ የሚኖሩ አባላት ችግር — አንዳንድ የሰንበት ጠባቂ ቤተሰቦች ብቻቸውን ወይም ተመሳሳይ እምነት ካለቸው ከሌሎች ተለይተው የሚኖሩ ናቸው። እነዚህ አንዳንድ ጊዜ ልጆቻቸውን እርዳታ አግኝተው ለገዛ ቤታቸው በረከት ወደሚሆኑበት አዳሪ ትምህርት ቤቶታችን ይልካሉ፡፡ ነገር ግን አንዳንዶች ልጆቻቸውን እንዲማሩ ከቤት ወደ ውጭ መላክ አይችሉም፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ወላጆች ባላቸው ችሎታ ለጌታ በመስራታቸው የሚደሰቱ እና የትኛውንም የወይን እርሻ ክፍል ለማልማት ፈቃደኛ የሆነ አርአያ የሚሆን የኃይማኖት መምህር ለመቅጠር መጣር አለባቸው። አባቶችና እናቶች ለልጆቻቸው መለወጥ በትጋት በመስራት ከመምህሩ ጋር መተባበር አለባቸው፡፡13 CGAmh 291.4

ልጆችን ለማዳን የራሳችሁን ነፍስ ለማዳን እንደምትሰሩ ሥሩ — በአንዳንድ አገሮች ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ በሕግ ይገደዳሉ፡፡ በእነዚህ አገራት ውስጥ ቤተ ክርስቲያን በሚገኝባቸው አካባቢዎች ትምህርቱን ለመከታተል ከስድስት የሚበልጡ ልጆች ከሌሉ ትምህርት ቤቶች መመስረት አለባቸው፡፡ በዓለም ብክለት እና ብልሹ ተጽዕኖዎች እንዳይሰምጡ ልጆቻችሁን ለመታደግ ለህይወታችሁ እንደምትሰሩ ያህል ሥሩ። CGAmh 291.5

በዚህ አስፈላጊ ጉዳይ አንጻር ከኃላፊነታችንን ከመወጣት እጅግ ወደ ኋላ ቀርተናል፡፡ በብዙ ቦታዎች ትምህርት ቤቶች ከዓመታት በፊት መሆን ሥራ መጀመር ነበረባቸው፡፡ አያሌ አከባቢዎች ለጌታ ሥራ ልዩ መለያ የሚሰጡ የእውነት ተወካዮች መሆን ይችሉ ነበር። በውስን ቦታዎች ብዙ ትላልቅ ሕንፃዎችን ከመገንባት ይልቅ ትምህርት ቤቶች በብዙ አካባቢዎች መመስረት ነበረባቸው። CGAmh 292.1

ልጆች እና ወጣቶች በየራሳቸው ቤተክርስቲያናት እንዲማሩ እነዚህ ትምህርት ቤቶች አሁን በጥበብ ምሪት ይጀመሩ፡፡ እግዚአብሔር የምንሰራባቸውን መገልገያ መሰሪዎችን በብዛት ሰጥቶን እያለ በዚህ መስመር ከፍተኛ ቸልተኝነት መኖሩ ለእግዚአብሔር ከባድ ኃጢአት መስራት ነው፡፡ 595 CGAmh 292.2

ሊተው የማይገባ የተመሰረተ ትምህርት ቤት— ይህ መከናወን እንዳለበት እግዚአብሔር በግልጽ ካልተናገረ በቀር የቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት በተቋቋመበት ሥፍራ የትምህርት ቤት ሥራ ፈጽሞ መተው የለበትም። ጎጂ ተጽዕኖዎች ትምህርት ቤቱ ላይ የሚያሴሩ ሊመስሉ ይችላሉ፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር እርዳታ መምህሩ የነገሮችን ቅደም ተከተል በመለወጥ ታላቅ እና የመታደግን ስራ መስራት ይችላል፡፡ 596 CGAmh 292.3

የማይታዘዙ እና ሥርዓት አልባ የሆኑ ልጆችን ማነቃቃት — አንዳንድ ጊዜ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ስራውን እጅግ ከባድ የሚያደርግ ምስቅልቅል ሁኔታ አለ፡፡ ትክክለኛውን ትምህርት ያላገኙ ልጆች ብዙ ችግር ይፈጥራሉ፣ በጠማማነታቸውም የመምህሩን ልብ ያሳዝናሉ፡፡ ነገር ግን ተስፋ አይቁረጥ፡፡ ፈተና እና መከራ ተሞክሮን ያመጣሉ፡፡ ልጆቹ የማይታዘዙ እና ሥርዓት አልባ ከሆኑ፣ ይበልጥ ጽኑ ጥረት ያስፈልጋል፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ባህሪይ ያላቸው ልጆች መኖራቸው የቤተ-ክርስቲያን ትምህርት ቤቶች መመስረት ካለባቸው ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡ ወላጆች ከማስተማር እና ከመገሰጽ ችላ ያሏቸው ልጆች ከተቻለ መዳን አለባቸው። 597 CGAmh 292.4

ዓለማዊ ወጣቶችን ለመለወጥ— ከዓመታት በፊት ትልልቅ ሕንፃዎች ሳይሆኑ የልጆች እና ወጣቶች እውነተኛ ትምህርት ማግኘት የሚችሉባቸው ለቤተክርስቲያን ትምህርት ቤቶች ተስማሚ የሚሆኑ የትምህርት ቤት ህንፃዎች ከ-- በተጨማሪ በሌሎች ቦታዎች መገንባት ነበረባቸው። ጥቅም ላይ የሚውሉ የመማሪያ መጻሕፍት የእግዚአብሔርን ሕግ ወደ ትኩረት የማምጣት ባህሪይ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የትምህርት መሠረት መደረግ አለበት። በዚህ ሥራ የእውነት ብርሃን፣ ጥንካሬ እና ኃይል ደምቆ ይታያል። ስሜታቸውን በማርካት አእምሮአቸው ያልተበላሸባቸው ከዓለም የመጡ ወጣቶች፣ ከእነዚህ ትምህርት ቤቶች ጋር በመገናኘት እዚያም ይለወጣሉ…፡፡ እንዲህ ዓይነት የሚስዮናዊነት የእውነትን ብርሃን እና ዕውቀት በማስፋፋት ረገድ እጅግ በጣም ኃይለኛ ተጽዕኖ ይኖረዋል፡፡17 CGAmh 293.1

ከፍተኛ ደረጃን ጠብቆ ማቆየት — በቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚሠራው ሥራ ባህርይ እጅግ ከፍተኛ ደረጃ ያለው መሆን አለበት፡፡ ለተሳሳተ ትምህርት ብቸኛው መፍትሄ ሰጪ፣ አዳሹ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ እናም ቃሉ የሚያስተምራቸው ትምህርቶች እጅግ ባማረ መልኩ በወጣቶች ፊት መቅረብ አለባቸው። የትምህርት ቤት ሥነ-ሥርዓቱ የቤት ውስጥ ሥልጠናን ማገዝ አለበት፣ በቤትም ሆነ በትምህርት ቤት ቀላል ያለ የአኗኗር ዘይቤ እና እግዚአብሔርን መምሰልን ጠብቆ ማቆየት ተገቢ ነው፡፡ 598 CGAmh 293.2

ለላይኛው ከፍተኛ ክፍል ለመዘጋጀት— ልጆቻችሁን ወደ ቤታችሁ ሰብስቧቸው፣ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ከሚጥሱ፣ ክፉን ከሚያስተምሩ እና ከሚያደርጉ ለይታችሁ ሰብስቧቸው ሲል እርሱ ለወላጆች የማስጠንቀቂያ ጩኸት ይልካል፡፡ በተቻላችሁ ፍጥነት ከትላልቅ ከተሞች ውጡ። የቤተክርስቲያን ትምህርት ቤቶችን መስርቱ፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል የትምህርት ሁሉ መሠረት አድርጋችሁ ለልጆቻችሁ ስጧቸው፡፡ ይህ በሚያማምሩ ትምህርቶች የተሞላ ነው፣ እንዲሁም ተማሪዎች በታችኛው የመጀመሪያ ደረጃ ይህን ጥናታቸውን ካደረጉ ለላይኛው ከፍተኛ ደረጃ ይዘጋጃሉ፡፡ 599 CGAmh 293.3

እግዚአብሔር አዘጋጅቷል— ትምህርት ቤቶቻችን ልጆችን እና ወጣቶችን ለሚስዮናዊነት ሥራ ገጣሚ የሚያደርግ የጌታ ልዩ መሳሪያ ነው። ወላጆች ኃላፊነቶቻቸውን መረዳትና ልጆቻቸው በትምህርት አጋጣሚዎች ውስጥ እግዚአብሔር ያዘጋጀላቸውን ታላላቅ ዕድሎች እና በረከቶችን ማድነቅ ይችሉ ዘንድ መርዳት አለባቸው፡፡ 600 CGAmh 294.1