የልጅ አመራር

53/85

ምዕራፍ 51—ለትምህርት ቤት ማዘጋጀት

የመጀመሪያዎቹ ስምንት ወይም አስር ዓመታት— ልጆች ለረጅም ጊዜ ቤት ውስጥ መታሰር የለባቸውም፣ እንዲሁም ለአካላዊ እድገት ጥሩ መሠረት እስኪጣል ድረስ በጥልቀት ማጥናት አይኖርባቸውም። ለልጆች የመጀመሪያዎቹ ስምንት ወይም አስር ዓመታት መስክ ወይም የአትክልት ስፍራ ምርጥ ትምህርት ቤት፣ እናት ምርጥ አስተማሪ፣ ተፈጥሮ ምርጥ የትምህርት መጽሐፍ ነው። ልጁ ትምህርት ቤት ለመማር ዕድሜው ሲደርስም እንኳን፣ ጤናው ከመጽሐፎች ዕውቀት ይልቅ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ተደርጎ መታየት አለበት፡፡ እርሱ ለአካላዊ እና ለአእምሮ እድገት በጣም ተስማሚ በሆኑ ሁኔታዎች ዙሪያ መከበብ አለበት፡፡ 580 CGAmh 283.1

በጣም ትናንሽ ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት መላክ የተለመደ ነው፡፡ የልጅነት አዕምሮአቸው ላይ ጫና የሚሆንባቸውን ነገሮች ከመጽሐፍ እንዲያጠኑ ይደረጋሉ…፡፡ ይህ ብልህ አካሄድ አይደለም፡፡ ብስጩ ልጅ በየትኛውም አቅጣጫ ከመጠን በላይ ጫና ሥር መውደቅ የለበትም፡፡ 581 CGAmh 283.2

በጨቅላነት ጊዜ የልጁ መርሃ ግብር— በልጁ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወይም ሰባት ዓመታት ውስጥ፣ እውቀት ይልቅ ለአካላዊ ሥልጠና ልዩ ትኩረት መሰጠት አለበት። ከዚህ ጊዜ በኋላ፣ አካላዊው አደረጃጀቱ ጥሩ ከሆነ ሁለቱም ትምህርቶች ላይ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል። ህፃንነት እስከ ስድስት ወይም ሰባት ዓመት ዕድሜ ድረስ ይዘልቃል፡፡ እስከዚህ ጊዜ ድረስ ልጆች ልክ እንደ ትናንሽ ጠቦቶች ከችግር እና ጭንቀት ነጻ ሆነው በቤት ዙሪያ እና በአጥር ግቢ ውስጥ፣ በደስታ ወዲያና ወዲህ መቦረቅ እና መዝለል አለባቸው፡፡ CGAmh 283.3

ወላጆች፣ በተለይም እናቶች እንደዚህ ላሉ የሕፃንነት አእምሮዎች ብቸኛ አስተማሪዎች መሆን አለባቸው፡፡ ከመጽሐፎች ማስተማር የለባቸውም። ልጆች በአጠቃላይ የተፈጥሮ ነገሮችን ለመማር ጠያቂዎች ይሆናሉ፡፡ እነርሱ ከሚያዩዋቸው እና ከሚሰሟቸው ነገሮች ጋር በተያያዘ ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ፣ እናም ወላጆች እነዚያን ትናንሽ ጥያቄዎች ለማስተማር እና በትዕግስት መልስ ለመስጠት እድላቸውን ማሻሻል አለባቸው፡፡ በዚህ መንገድ ጠላት ላይ ዕድል ፈንታን ማግኘት እና በልጆቻቸው ልብ ላይ መልካም ዘር በመዝራት የልጆቻቸውን አዕምሮ በመመሸግ ክፋት ሥር ለመስደድ ሥፍራ እንዳይኖረው ማድረግ አለባቸው፡፡ በልጅነታቸው ዕድሜ ላይ እናት የምትሰጣቸው ፍቅራዊ መመሪያ ባህሪያቸውን ለመቅረጽ ተፈላጊው ነገር ነው፡፡ 582 CGAmh 283.4

በሽግግሩ ወቅት የሚያስፈልጉ ትምህርቶች— እናት አስተማሪ፣ ቤት እያንዳንዱ ልጅ የመጀመሪያ ትምህርቱን የሚቀበልበትን ትምህርት ቤት መሆን አለበት፤ እና እነዚህ ትምህርቶች የታታሪትን ልማዶችን ማካተት አለባቸው። እናቶች፣ ትናንሽ ልጆች ከቤት ውጭ አየር ማግኘት የሚችሉበት ቦታ ላይ ይጫወቱ፤ ወፎችን እያዳመጡ በሚያማምሩ ሥራዎቹ ውስጥ የተገለፀውን የእግዚአብሔር ፍቅርን ይማሩ፡፡ ከተፈጥሮ መጽሐፍ ስለ እነርሱ ከተቀመጡ ነገሮች ቀላል ትምህርቶችን አስተምሯቸው፤ እናም አእምሯቸው እየሰፋ ሲሄድ፣ ከመጽሐፎች ውስጥ ትምህርቶችን በመጨመር አዕምሮአቸው ላይ በጥብቅ ይቀረጽ። ነገር ግን ገና በልጅነታቸው ዓመታትም ፈይዳ መስጠትንም ጭምር ይማሩ፡፡ የቤተሰቡ አባላት እንደመሆናቸው መጠን ገና ከልጅነት ዓመታቸውም ጀምሮ እንኳ የቤት ውስጥ ሸክሞችን በመጋራት ረገድ አጋዥ እንዲሆኑ እና አስፈላጊ የሆኑ የቤት ውስጥ ሥራዎችን በሚያከናውንበት ጊዜ ጤናማ ሥራ መስራትን ለመሻት ፍላጎት እንዲኖራቸው አሠልጥኗቸው፡፡ 583 CGAmh 284.1

አሰቃቂ ሂደት መሆን የለበትም — እንዲህ ዓይነቱ ሥልጠና ለልጅ የልተነገረለት ዋጋ አለው፣ እና ይህ ስልጠና አሰቃቂ ሂደት መሆን የለበትም። ልጅ እንዴት መርዳት እንዳለበት እየተማረ ደስታን በሚያገኝበት መልኩ መስጠት ይቻላል። እናቶች ትናንሽ የፍቅር የኃላፊት ቦታዎችን እንዲወጡ እና የቤት ውስጥ ስራዎችን እንዲያከናውኑ በማስተማር ልጆቻቸውን ማስደሰት ይችላሉ፡፡ ትዕዛዝ በትዕዛዝ፣ ሥርዓት በሥርዓት፣ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ በማድረግ ልጆቿን በትዕግስት ማስተማር የእናት ስራዋ ነው። እናም ይህንን ሥራ ስትሠራ እናት እራሷ እጅግ ጠቃሚ ስልጠና እና ትምህርትን ታገኛለች፡፡ 584 CGAmh 284.2

በትምህርት ቤት ባልደረባዎች አደጋ ላይ የወደቀው ግብረ ገብ— ትናንሽ ልጆቻችሁን ገና በልጅነታቸው ወደ ትምህርት ቤት አትላኩ። እናት የልጅነት አእምሮን መቅረጽን ለሌሎች በአደራ እንዴት መስጠት እንዳለባት ጥንቃቄ ማድረግ አለባት፡፡ 585 CGAmh 285.1

ብዙ እናቶች ልጆቻቸውን ለማስተማር ጊዜ እንደሌላቸው ይሰማቸዋል፣ እርሱንም ከመንገድ ዞር ለማድረግ እና ጫጫታ እና ችግርን ለማስወገድ ወደ ትምህርት ቤት ይልኳቸዋል…፡፡ CGAmh 285.2

ልጆችን በልጅነታቸው ወደ ትምህርት ቤት መላክ አካላዊ እና አእምሯዊ ጤንነት ላይ አደጋ የሚጥል ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን ከግብረ ገብ አንጻርም የተዋረዱ ናቸው። በባህሪያቸው ካላደጉ ልጆች ጋር ለመተዋወቅ እድል አግኝተዋል፡፡ ክፉ፣ ባለጌ፣ የሚዋሹ፣ የሚምሉ፣ የሚያታልሉ እና ከእነርሱ በዕድሜ ለሚያንሱት የብልግናን ዕውቀት በማስተማር የሚደሰቱ ማህበረሰብ ውስጥ ይወረወራሉ፡፡ ትናንሽ ልጆች ለእራሳቸው ከተተዉ፣ ከመልካም የበለጠ ክፉውን በፍጥነት ይማራሉ። መጥፎ ልማዶች ከተፈጥሮ ልብ ጋር በተሻለ ሁኔታ ይስማማሉ፣ እናም በልጅነታቸው የሚያዩት እና የሚሰሟቸው ነገሮች በአዕምሮአቸው ውስጥ በጥልቀት ይቀረጻሉ፤ በልጅነታቸው ልብ ውስጥ የተዘራው መጥፎ ዘር ሥር ይሰድድ እና የወላጆቻቸውን ልብ የሚያቆስል የሾለ እሾህ ይሆናል።7 CGAmh 285.3