ቀደምት ጽሑፎች
65—ታላቁ ጩኸት
የአንድ አስፈላጊ ክስተት እውን መሆንን ተከትሎ መላእክት ከሰማይ ወደ ምድር በፍጥነት ሲወርዱና ሲወጡ ተመልክቼ ነበር በመቀጠል አንድ ሌላ ታላቅ ሥልጣን የተሰጠው ኃያል መልአክ ድምጹን ከሦስተኛው መልአክ ጋር በማቀናጀት ለመልእክቱ ኃይልና ጉልበት ለመስጠት ወደ ምድር ሲወርድ አየሁ፡፡ ለመልአኩ ከተሰጠው ታላቅ ኃይልና ክብር የተነሳ ምድር አበራች:: መልአኩ በብርቱ ድምጽ ሲጮኽ በእርሱ ላይ ያንጸባረቀው ብርሃን ስፍራውን ሁሉ በብርሃን ሞላው «ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንት መኖሪያ የርኩሳን መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኩስና አጸያፊ ወፎች ሁሉ መጠለያ ሆነች፡፡” የባቢሎን ውድቀት መልእክት ቀደም ብሎ በሁለተኛው መልአክ በመሰጠቱ አሁን ከ1844 አንስቶ በቤተክርስቲያን የተከሰተውን ብልሹ አሠራር በማከል በድጋሚ ቀርቦአል፡፡ ይህ መልአክ ታላቁንና የመጨረሻውን የሦስተኛውን መልአክ መልእክት ለመደገፍ የመጣው በትክክለኛወ ጊዜ ነው፡፡ በዚህን ወቅትየእግዚአብሔር ሕዝቦች በቅርቡ እውን በሚሆነው ፈተና ላይ ለመቆም ተዘጋጅተው ነበር፡፡ በእነዚህ ህዝቦች ላይ ታላቅ ብርሃን ሲወርድና የሦስተኛውን መልአክ መልእክት ያለ ፍርሃት ለማወጅ ኀብረት ሲፈጥሩ ተመለከትከ EWAmh 204.2
ይህን ኃያል መልአክ ለመርዳት ሌሎች መላእክት ከሰማይ ተላኩ፡፡ ከዚያም በየስራው የሚሰሙ የሚመስሉ ድምጾችን አደመጥኩ «ሕዝቤ ሆይ በኃጢአቷ እንዳትተባበሩ፤ ከመቅሰፍቷም እንዳትካፈ ፤ ከእርሷ ውጡ ኃጢአትዋ እስከ ሰማይ ድረስ ተከምሮአልና፤ እግዚአብሔርም ዐመጻዋን አስታውሶአል” ይህ መልእክት 1844 ላይ ለሁለተኛው መልአክ መልእት በተጨማሪነት የዕኩለ ሌሊቱ ጩኸት ከመሰጠቱ በተመሳሳይ ለሦስተኛው መልአክ መልእክትታክሎ የተሰጠ ነው፡፡ በትዕግሥት ይጠባበቁ በነበሩት ቅዱሳን ላይ አምላካዊው ክብር አርፎ ነበር፡፡ ቅዱሳኑ የባቢሎንን ውድቀት በማወጅ የእግዚአብሔር ሐዝቦች በባቢሎን ላይ ከሚወርደው አስፈሪ ኩነኔ ይተርፉ ዘንድ ከውስጧ እንዲወጡ ያለ አንዳች ፍርሃት ይህን የመጨረሻውን ጽኑ ማስጠንቀቂያ ሰጡ፡፡ EWAmh 205.1
በዳግም ምጽአቱ ተጠባባቂዎች ላይ አብርቶ የነበረው ብርሃን በየስፍራው በመሰራጨቱ በየአብያተክርስቲያናቱ ብርሃን የነበራቸው፤ የሦስተኛውን መልአክ መልእክት ያልሰሙና ያልተቃወሙ በመታዘዝ የወደቀችውን ቤተክርስቲያን እየተዉ ወጡ፡፡ እነዚህ መልእክቶች ከተሰጡበት ጊዜ አንስቶ ብዙዎች ተጠያቂ ሲሆኑበት፣ ብርሃን በላያቸው ሲያንጸባርቅና ህይወት ወይም ሞት የሚመርጡበትን ዕድል ሲያገኙበት ኖ ረዋል አንዳንዶች ህይወትን በመምረጥ ጌታቸውን ከሚጠባበቁና የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ከሚጠብቁ ጋር አቋማቸውን አንድ አድርገዋል፡፡ በሦስተኛው መልእክት ሁሉም በመፈተን---መልአክቱ የከበሩት ነፍሳት ከየኃይማኖታዊ ተቋማቱ ተጠርተው እንዲወጡ በማድረግ የታለመለትን ሥራ መሥራት ነበረበት፡፡ አምላካዊው ኃይል የእግዚአብሔርን ሥራ መሥራት እንዳለባቸው የተሰማቸውን ታማኞቹን ወደፊት በመግፋት ብርቱ ልበት ሲሆናቸው ነገር ግን አማኝ ያልሆነ ት ዘመዶቻቸውና ጓደኞቻቸው በእነርሱ ላይ አጉል ተጽእኖ በማሳረፍ ሥራው ላይ መስናክል እንዳይሆኑ የሚያደርግ ፍርሃት ጉበቷቸው ነበር የመጨረሻው ጥሪ ምስኪን የነበሩትን ኃይማኖተኛ ባሮችንም ጭምር የሚያካትት ነበር እነዚህ ወገኖች ስለ ነጻነታቸው የሚያወሱ ልብ መጭ መዝሙሮችን በደስታ መንፈስ ያሙ ነበር: ጌቶቻቸው ፍርሃትና መደመም ስለያዛቸው ሁናቴውን በጸጥታ ከመከታተል ውጪ አፋቸውን ከፍተው ሊያስቆሟቸው አልቻሉም ነበር፡፡ አማኞችን ምልክቶችና ድንቃድንቆች ይከተሏቸው ስለ ነበር ታላላቅ ተአምራቶች ተደ ረጉ፣ የታመመ ም ተፈወሱ፡፡ እግዚአብሔር በሥራው ውስጥ ስለነበር እያንዳንዱ የእርሱ ቅዱስ ሊመጣበት የሚችለውን ነገር : ባለመፍራት በመንፈስ ቅዱስ የተነካውን ህሊናውን ተከትሎ ሁሉንም የአግዚአብሔር ትእዛዛት ከሚጠብቁ ወገኖች ጋር ህብረት በመፍጠር በአንድነት የሦስተኛውን መልአክ መልእክት አስተጋቡ፡፡ ይህ መልእክት ከእኩለ ሌሊቱ ጩኸት በላቀ በኃይልና በብርታት እንደሚዘጋ ተመልክቼ ነበር EWAmh 205.2
የእግዚአብሔር አገልጋዮች ከላይ በወረደ በኃይል ተሞልተው፣ ፊታቸው አብርቶና ተቀድሰው ሰማያዊውን መልእክት ለማወጅ ተንቀሳቀሱ፡፡ ተበታትነው የነበሩ የከበሩ ነፍሳት ለጥሪው ከየነበሩባቸው ኃይማኖታዊ ተቋማት ምላሽ በመስጠት ሰዶም ሊጠፋ ሲል ሉጥ በፍጥነት ለቅቆ እንደወጣ ሁሉ እነዚህም ወገኖች ከወደቁት አብያተክርስቲያናት እየተጣደፉ ይወጡ ነበር የእግዚአብሔር ሕዝቦች በላያቸው ተትረፍርፎ ያረፈው ግሩም ክብር እንዲÁረታቱ በማድረግ የፈተናውን ሰዓት እንዲያልፉ አዘጋጅቶአቸው ነበር በየስፍራው እንዲህ የሚል የብዙ ህዝብ ድምጽ ሰማሁ ‹‹የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁና ለየሱስም ታማኝ ሆነው በትዕግሥት የሚጸኑ ቅዱሳን የሚታወቁት በዚህ ነው፡፡» EWAmh 206.1