ቀደምት ጽሑፎች
64—የባቢሎን ኃጢአት
ሁለተኛው መልአክ የአብያተክርስቲያነትን ውድቀት ካወጀበት ጊዜ አንስቶ ከቀድሞው ይበልጥ እየከፉ መሄድ መጀመራቸውን ተመልክቻለሁ፡፡: አባላቶቻቸው የየሱስን ስም ተሸክመናል ቢሉም ነገር ግን እነርሱን ከዓለም ለይቶ ማየት አዳጋች ነው፡፡ አገልጋዮች ጥቅሶችን የሚወስዱት ከአምላካዊው ቃል ቢሆንም ነገር ግን ስብከቶቻቸው ለስላሳ ናቸው፡፡ በመሆኑም ተፈጥሮአዊው ልብ በመልክቶቻቸው ላይ የሚያሰማው ተቃውሞ የለም፡፡ በሥጋዊው ልብ ዘንድ የሚጠሉት---የእውነት ኃይልና መንፈስ እንዲሁም የክርስቶስ ደኅንነት ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህ ውጪ በዝነኛው አገልግሎት የሰይጣንን ቁጣ በማጫር ኃጢአተኛውን እንዲንቀጠቀጥ የሚያደርግ ወይም በቅርብ የሚመጣውን ፍርድ አስፈሪ ተጨባጭ ገጽታ በልብና በህሊና ላይ የሚያሳርፍ አንዳችም ነገር የለም፡፡ ኃጢአተኛ ሰዎች በእውነት የተለወጠ ህይወት በሌለው በጎነት ደስተኞች በመሆናቸው ለእንዲህ ያለው ኃይማኖት ድጋፋቸውን ይሰጣሉ፡፡ EWAmh 202.1
መልአኩ አንዲህ አለ «ከጽድቅ የጦር ትጥቅ ባነሰ ያለ ዝግጅት ሰብዓዊው ፍጡር በጨለማው ኃይላት ላይ ድል እንዲቀዳጅ አያስችለውም:: ሰይጣን አብያተክርስቲያናትን እንደ አንድ አካል በመቆጣጠሩ የሰዎች አባባልና ድርጊት የተባ ስለት ካለው ግልጽ አምላካዊ ቃል በላይ ሆነ፡፡ የዓለም መንፈስና ወዳጅነት ከእግዚአብሔር ጋር ባላንጣ ነው፡፡ እውነት በየሱስ ላይ እንደታየው ግልጽና ኃይል ሲኖረው ከዓለም በተቃራኒ በመሆን ፍሬ ያፈራል---ስደት እንዲመጣም መንስዔ ይሆናል፡፡ ክርስቲያን ነን የሚሉ ብዙዎች እግዚአበሔርን አላወቁትም፡፡ ተፈጥሮአዊው ልብ ባለመለወጡ ሥጋዊው አእምሮ ከእግዚአብሔር ጋር ጠላት እንደሆነ ይኖራል፡፡ ምንም እንኳ እነዚህ ሰዎች መጠሪያቸው ሌላ ቢሆንም እነርሱ ግን የሰይጣን ታማኝ አገልጋዮች ናቸው፡፡” EWAmh 202.2
የሱስ የሰማያዊውን መቅደስ ቅዱሱን ክፍል በመልቀቅ ወደ ሁለተኛው መጋረጃ ከገባበት ጊዜ አንስቶ ቤተክርስቲያናት በረከሱና በሚጠሉ አዕዋፋት እንደተሞሉ አይቻለሁ:: አባላት እራሳቸውን ክርስቲያን ብለው ቢጠሩም ነገር ግን በቤተክርስቲያናት ውስጥ ታላቅ እርክስናና ብልግና ተመልክቻለሁ፡፡ ተግባራቸውና ጸሎታቸው በእግዚአብሔር ዐይን አሰቃቂና አስፈሪ ናቸው፡፡ መልአኩ እንዲህ አለኝ «እግዚአብሔር በጉባዔዎቻቸው አይኖርም፡፡ እራስ ወዳድነትን፣ ማጭበርበርና ማታለልን በመገሰጽ ፋንታ እየተለማመዷቸው የሚገኙ ሲሆን፤ በእነዚህ ባህሪያት ላይ ኃይማኖታዊውን ካባ ደርበዋል፡፡” የየሱስን ስም ተሸክመናል የሚሉ አብያተክርስቲያናትን ኩራት ተመልክቼ ነበር፡፡ እግዚኣብሔር በአስተሳሰባቸው ውስጥ የለም በምትኩ ከእነርሱ ጋር ያለው ሥጋዊው አስተሳሰባቸው ነው፡፡ ምስኪንና ሟች የሆነውን አካላቸውን በማጋጌጥ እራሳቸውን በእርካታና በደስታ ይመለከታሉ፡፡ የሱስና መላእክቱ እነዚህን ሰዎች በብስጭት ይመለከቷቸዋል፡፡ መልአኩ እንዲህ አለኝ «የእነርሱ ኃጢአትና መታበይ ሰማይ ደርሶአል፡፡ ድርሻቸው ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ፍርድና ፍትሕ ለረጅም ጊዜ ቢያንቀላፉም ነገር ግን በቅርቡ ይነቃሉ በቀል የእኔ ነው ዋጋቸውን እከፍላለሁ ይላል ጌታ»፡፡ የሦስተኛው መልአክ አስፈሪ ማስጠንቀቂያዎች ልብ ሊባሉ ይገባል፡፡ ኃጥአን ሁሉ ከእግዚአብሔር ቁጣ መጠጣታቸው እሙን ነው፡፡ ለቁጥር የሚያታክቱ የክፉ መላእክት ሰራዊተበመላው ምድሪቱ ላይ በመሰራጨት አብያተክርስቲያናትን እያጣበቡ ይገኛሉ፡፡ ኃይማኖታዊው ካባ ታላላቅ ወንጀሎችንና ማጭበርበሮችን ስለሚሸፍን እነዚህ የሰይጣን ወኪሎች መንፈሳዊ አካላትን በፈንጠዝያ ዐይን ይመለከቷቸዋል፡፡ EWAmh 202.3
የእግዚአብሔርን ሥራ ውጤት እጅግ በዘቀጠ መልኩ አውርዶ ሰብዓዊውን ፍጠር እንደ እንስሳ የመቁጠሩን ተግባር መላው ሰማይ በቅዱስ ቁጣ ይመለከተዋል፡፡ ለሰው ልጅ የተለየ ርኅራኄ የነበረው አዳኝ ተከታዮች ነን የሚሉ በከፋው የባሪያ ፍንገላ ኃጢአት ውስጥ እጆቻቸውን በማስገባት ከልባቸው ገፍተውበታል፡፡ ሰብዓዊው ህመምና ሥቃይ ከስፍራ ስፍራ እንዲጋዝና እንዲሸጥ ሆኗል፡፡ ይህን ደግሞ የሰማይ መላእክት መዝግበው በመያዛቸው በመጽሐፉ ላይ ተጽፎአል፡፡ በግዞት ውስጥ ያሉ ቅዱሳን ወንዶች፣ ሴቶች፣ አባቶች፣ እናቶች፣ ህጻናት፣ ወንድሞችና እህቶች እንባ በሰማያዊው ዕቃ ተሰፍሮ ተቀምጦአል፡፡ እግዚኣብሔር ቁጣውን የሚይዘው ለአጭር ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ቁጣው በዚህ ህዝብ በተለይም የሰብዓዊውን ፍጡር የባርነት ዝውውር በደገፉ ኃይማኖታዊ አካላት ላይ ይወርዳል፡፡ እንዲህ ያለው ኢፍትሐዊነት፣ ጭቆናና ሥቃይ ኃዘኔታና ርኅራኄ በሌላቸው ቅን የሆነው የየሱስ ተከታዮች ነን ባዮች ዘንድ የሚታይ ነው፡፡ ከእነዚህ ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በጥላቻ ተሞልተው በእነዚህ ወገኖች ላይ ለመግለጽ አዳጋች ሥቃዮችን, እያደረሱ እግዚአብሔርን እናመልካለን ብለው በድፍረት ይናገራሉ፡፡ ይህ በእርሱ ላይ መሳለቅ ነው፡፡ በዚህ ተግባራቸው የሚከብረው ሰይጣን ‹እነሆ የክርስቶስ ተከታዮች!» እያለ የሱስና መላእክቱን ያለማቋረጥ ይተቻል:: EWAmh 203.1
እነዚህ ክርስቲያኖች ነን የሚሉ ሰዎች በሰማዕታት ላይ የደረሰውን ሥቃይና በጉንጮቻቸው ቁልቁል ስለ ወረደው የዕንባ ዘለላ በማንበብ እንዴት ሰው በሰው ላይ እንዲህ ያለውን የጭካኔ ድርጊት ይፈጽማል? ብለው ተገርመዋል፡፡ ነገር ግን እንዲህ የሚያስቡትና የሚናገሩት እነርሱ እራሳቸው ሰብዓዊውን ፍጡር በባርነት እየገዙ ነው:፡፡ በዚህ ብቻ ሳያበቁ በመካከላቸው ያለውን ተፈጥሮአዊ ትስስር በመበጠስ ወገናቸው የሆነውን የሰው ልጅ ላይ አሰቃቂ ጭቆና አድርሰዋል፡፡ እንዲሁም ቀደም ባለው ጊዜ በጳጳሳዊው ሥርዓትና በአረማውያን አማካኝነት በክርስቲያኖች ላይ ይፈጸም የነበረው ሥቃይና ግፍ በተመሳሳይ ጭካኔ ተፈጽሞባቸዋል፡፡ መልአኩ «በእግዚአብሔር ፍርድ ወቅት ከእነዚህ ሕዝቦች ይልቅ ለጳጳሳቱና ለአረማውያኑ ይቀላል» አለኝ፡፡ ጭቆና የደረሰባቸው ሰዎች ለቅሶ ሰማይ በመድረሱ በአምላካዊው አምሳያ በተፈጠረው ሰብዓዊ ፍጡር ላይ እንዲህ ያለውን ከዚህ ቀደም ታይቶ የማያውቅ ሥቃይ መላእክት በአግራሞት ይመለከቱ ነበር፡፡ መልአኩ «የሚጨቁኑና የሥቃይ ዕንባ እንዲስ የሚያደርጉ ሰዎች ስም በደም ተጽፎአል፡፡ ይህ ምድር የቁጣውን ጽዋ እስኪጎነጭ ድረስ አምላካዊው ቁጣ አያባራም፡፡” አለኝ፡፡ EWAmh 203.2
የባሪያ አሳዳሪው ያለ ዕውቀት ላጎረው ነፍስ መልስ መስጠት እንዳለበትና ለባሪው ኃጢኣት ተጠያቂው እርሱ እንደሚሆን ተመልክቻለሁ፡፡: ስለ እግዚአብሔር ወይም ስለ መጽሐፍ ቅዱስ አንዳችም ዕውቀት ሳይኖረው ከጌታው ዱላ በቀር ፈሪሃ እግዚአብሔር ሳይኖረው ተጨቁኖ የኖረው ባሪያ ወደ ሰማይ ለመሄድ ይቸገራል፡፡ EWAmh 204.1