ቀደምት ጽሑፎች

1/73

ቀደምት ጽሑፎች

መግቢያ

በምንኖርባቸው ተለዋዋጭ ዘመናት ውስጥ ከምዕተ ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረ ነገር ግን ተፈላጊነቱ እየጨመረ የሚሄድ ወቅታዊ ጉዳዮችን የያዘ የሥነ ጽሑፍ ሥራ ማግኘት የሚቻለው በጣም አልፎ አልፎ ነው፡: ይህ በኤለን ጂ. ኋይት የተጻፈ መጽሐፍ ከእነዚህ ዕድለኛ ሥራዎች መካከል አንዱ ነው:: በዘመናት ይህ መጽሐፍ ለአያሌ ጊዜያቶች በተደጋጋሚ ሲታተም ኖሮአል: ይህ በመጀመሪያ እ...አ. 1851 ላይ የታተመ መጠነኛ ገጾች ያሉት ዝነኛ መጽሐፍ የክርስቲያኖችን ተሞክሮና የኤለን ጂ. ኋይት አመለካከቶችን ይዞአል፡፡ የኤለን ኋይት ቀደምት ሥራዎችን በብዙ አንባቢዎች ዘንድ ከፍተኛ ተፈላጊነት እንዲኖረው ያደረገው በመንፈሳዊ ስጦታዎች አማካኝነት ለቤተክርስቲያን ጠቃሚ ኢንፎርሜሽኖችንና ማበረታቻዎችን በመያዙ ነው:: EWAmh 3.1

The Trustees of the Ellen G. White Publications. Washington, D.C.