ቀደምት ጽሑፎች

43/73

42—የክርስቶስ ዕርገት

መላው ሰማይ የሱስ ወደ አባቱ ማረግ ያለበትን የድል አድራጊነቱን ሰዓት ይጠባበቅ ነበር፡፡ መላእክት የክብር ንጉሥን በመቀበል በድል አድራጊነት ወደ ሰማይ አጅበውት ሊወስዱት መጡ፡፡ የሱስ ደቀ መዛሙርቱን ከባረካቸው በኋላ ከእነርሱ ተለይቶ አረ7፡፡ እርሱ ወደ ሰማይ ሲያርግ በትንሳኤው ወቅት ከእርሱ ጋር ከሙታን የተነሱ ምርኮዎችን አስከትሎ ወጣ:: ትዕይንቱን መላው የሰማይ ሠራዊት ይመለከት የነበ ረ ሲሆን በሰማይ ደግሞ ሊቆጠሩ የማይችሉ መላእክት ይጠባበቁት ነበር፡፡ የሱስ ወደ ቅድስት ከተማ ሲያርግ እርሱን እያጀቡ የነበሩ መላእክት ድምጻቸውን ከፍ አድርገው «እናንተደጆች፤ ቀና በሉ፤ እናንተየዘላለም በሮች፤ የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ!” በማለት ጮኹ፡፡ በዚህን ጊዜ በከተማዋ ውስጥ የነበሩ መላእክት በደስታ ተውጠው «ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው?” በማለት ጠየቁ:: የሱስን አጅበው የነበሩ መላእክት «እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኃያል፤ እግዚአብሔር ነው በውጊያ ኃያል፤ እናንተደጆች ፧ ቀና በሉ፧ እናንተየዘላለም በሮች፧ የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ!” ሲሉ በድል አድርጊነት መለሱላቸው፡፡ ሲጠባበቁ የነበሩት መላእክት «ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው?” በማለት በድጋሚ ጠየቋቸው፡፡ የሱስን ያጀቡት መላእክት ቅላጼያዊ በሆነ አነጋገር «የሰራዊት አምላክ እርሱ የክብር ንጉሥ ነው» በማለት መለሱላቸው፡፡ ከዚያም ወደ እግዚአብሔር ከተማ አልፈው ገቡ፡፡ በዚህን ወቅት መላው የሰማይ ሰራዊት ታላቁን አዛዣቸውን ከብበው በፊቱ በማጎንበስ ከልብ በመነጨፍቅር አብረቅራቂ አክሊሎቻቸውን ከአናታቸው እያወለቁ በአግሩ ስር አኖሩ፡፡ ወርቃማ በገናዎ ቻቸውን በመንካት ታርዶ ለነበረው፣ ዳግም በንጉሥነት በክብር ለሚኖረው ለበጉ ጣፋጭና ውብ የሆኑ ዜማዎችን በማሰማት መላውን ሰማይ በጥልቅ ሙዚቃና ዝማሬ ሞሉት፡፡ EWAmh 134.1

ደቀ መዛሙርቱ በሐዘን ስሜት ሆነው ወደ ሰማይ እያረገ የነበረውን የሱስ ትኩር ብለው እየተመከቱ እያለ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት መላእክት ድንገት አጠገባቸው ቆሙና እንዲህ አሏቸው «እናንት የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ እዚህ የቆማችሁት ለምንድን ነው? ይህ ከእናንተዘንድ ወደ ሰማይ ሲያርግ ያያችሁት የሱስ ልክ ወደ ሰማይ ሲወጣ እንዳያችሁት በዚሁ ሁኔታ ይመለሳል፡፡” ደቀ መዛሙርቱና ከእነርሱ ጋር የእግዚአብሔርን ልጅ እርገተየተመለከተችው እናቱ ቀጣዩን ምሽት በአነዚያ አጭር ጊዜያት ውስጥ ስለ ሠራቸው አስደናቂ› እንግዳና በክብር የተሞሉ ክስተቶች እያወሩ አሳለፉ፡፡ EWAmh 134.2

ሰይጣን በድጋሚ ከመላእክቱ ጋር በመምከር እርሱ በምድር ላይ ያለውን ኃይሉንና ሥልጣኑን ጠብቆ በመያዝ በየሱስ ተከታዮች ላይ አስር እጥፍ የበረታ ሥራ መሥራት እንዳለባቸው በእግዚአብሔር መንግሥት ላይ የመረረ ጥላቻ በማሳየት ነገራቸው፡፡ እነርሱ በክርስቶስ ላይ አንዳችም ድል ባለመቀዳጀታቸው የሚቻል ከሆነ ተከታዮቹን ማሽነፍ አለባቸው፡፡: በማንኛ ውም ትውልድ የሚገኙ የየሱስን አማኞች ወጥመዳቸው ውስጥ መክተት አለባቸው:: የየሱስ ደቀ መዛሙርት እነርሱን እንዲገስጽዋቸው፣ ከሰለባዎቻ ቸው ውስጥ እንዲያወጧቸውና በሽታ ላይ የጣሏቸውን እንዲፈውሱ የሱስ ኃይል እንደሰጣቸው ለመላእክቱ ነገራቸው፡፡ ከዚህ በኋላ የሰይጣን መላእክት የየሱስን ተከታዮች ለማጥፋት በመሻት እንደሚያገሣ አንበሳ ሆነው ወደፊት ማምራታቸውን ቀጠሉ፡፡ EWAmh 135.1