ቀደምት ጽሑፎች

42/73

41—የክርስቶስ ትንሳኤ

የክብር ንጉሥ የሆነው የየሱስ በድን በመቃብር ውስጥ እንደተንጋለለ ደቀ መዛሙርቱ በጌታቸው ሞት እያዘኑ ሰንበትን አረፉ፡፡ በዚያ በዓይን የማይታዩ መላእክት ይሰፉ በነበረበት ቅዱሱ ባረፈበት ስፍራ ላይ፤ መሸትሸት ሲል ይህኑ ቦታ የሚጠብቁ ወታደሮች ተመድበው ነበር፡፡ ሌሊቱ ቀስ በቀስ ይገሰግስ ነበር ሆኖም ሳይነጋ ጨለማ እንደሆነ ጠባቂ መላእክት የከበረው የእግዚአብሔር ልጅና ተወዳጁ አዛዣቸው ከመቃብር የሚነሳበት ጊዜ መቃ ረቡን ተረዱ፡፡ መላእክቱ የድል አድራጊነቱን ሰዓት ጥልቅ በሆነ ስሜት እየተጠባበቁ ሳለ፤ መልኩ እንደ መብረቅ ብሩህ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ የሆነ አንድ ኃያል መልአክ ከሰማይ እየበረረ መጣ:፡፡ ብርሃኑ ጨለማውን ዳር እስከ ዳር በማብራት በአሸናፊነት የየሱስ አካል ይገባናል ብለው ሲጠባበቁ የነበሩትን ክፉ መላእክት ከፍካቱና ከክብሩ የተነሳ በፍርሃት እንዲበሩ አደ ረጋቸው የክርስቶስን ውርደትና የተቀበረበትን ስፍራ ሲመለከቱ ከነበሩት የመላእክት ሰራዊት አንዱ ይህን መልአክ ከሰማይ በመቀላቀል በአንድ ላይ ወደ መቃብሩ መጡ፡፡ በዚያም በተቃረቡ ጊዜ ምድር ተንቀጠቀጠች ታላቅም መናወጥ ሆነ፡፡ EWAmh 127.1

የሮም ወታደሮች በከፍተኛ ፍርሐት ላይ ወደቁ:: አሁን ያ ሁሉ ኃይላቸው ወዴ ሄደ? ከጸሐይ ይልቅ ያንጸባርቅ የነበረው የመላእክቱ ብርሃን ዙሪያውን ባበራ ጊዜ ወታደሮቹ ህሊናቸውን ስተው ወደቁ: ከመላእክቱ አንደኛው በመቃብሩ ደጃፍ ላይ የነበረውን ድንጋይ ካንከባለለው በኋላ በላዩ ላይ ቁጭ አለ፡፡ ሌላው ወደ መቃብሩ ውስጥ በማለፍ የየሱስ አናት የተጠቀለለበትን ጨርቅ ተረተረው፡፡ ከዚያም «አንተ የእግዚአብሔር ልጅ አባትህ ይጠራሃል ተነስ!» ብሉ ሲጮኽ ከድምጹ ብርታት የተነሳ ምድር ተናወጠች፡፡: ከዚህ በኋላ ሞት በእርሱ ላይ ሥልጣን ሊኖረው አልቻለም፡፡ የሱስ በድል አድራጊነት ከሞት ተነሳ፡፡ የመላእክት ሰራዊት በጽኑ አድናቆት ትዕይንቱን ይመለከቱ ነበር፡፡ የሱስ ከመቃብር በተነሳ ጊዜ እነዚያ ያበሩ የነበሩ መላእክት በአምልኮ አንገቶቻቸውን ወደ ምድር አጎንብሰው በድል አድራጊነትና በአሸናፊነት መዝሙር ምስጋና ያቀርቡለት ነበር የሰይጣን መላእክት በሰማይ መላእክት በፈነጠቀው አንጸባራቂና ብሩህ ብርሃን ከስፍራው እንዲወገዱ ሆነው ነበር፡፡ EWAmh 127.2

የሰይጣን መላእክት ግዳያችን ያሉት በኃይል ከእነርሱ በመወሰዱና ያ አብልጠው የጠሉት ከሞት በመነሳቱ በንጉሣቸው ላይ አማረሩ ሰይጣንና ሰራዊቱ በወደቀው ሰብዓዊ ፍጡር ላይ ባላቸው ኃይል የህይወት ጌታ በመቃብር እንዲውል በማድረጋቸው ከፍ ከፍ ቢሉም ነገር ግን ሰይጣናዊው ድል በእጅጉ አጭር ነበር የሱስ ከነበረበት የእስር ቤት ወጥቶ ወደ ንጉሣዊ ገዢነት መረማመዱ ሰይጣን ከተወሰኑ ጊዜ ያቶች በኋላ መሞት እንዳለበትና መንግሥቱም ወደ ትክክለኛው ባለ መብት እንደሚተላለፍ አወቀ፡፡ ሰይጣን የተቻለውን ሁሉ ቢያደርግም ነገር ግን የሱስ ሳይሸነፍ ለሰብዓዊው ፍጡር የደኅንነት መንገድ መክፈቱንና በዚህ ጎዳና የሚራመዱ ሁሉ እንደሚድኑ ሲመለከት አነባ---በቁጣም ነደደ፡፡ EWAmh 127.3

ክፉ መላእክትና አዛዣቸው አሁንም እንዴት በእግዚአብሔር መንግሥት በተቃራኒ መሥራት እንዳለባቸው ለመምከር ጉባዔ ተቀመጡ፡፡ ሰይጣን አገልጋዮቹ ወደ ቀሳውስት አለቆችና ሽማግሌዎች እንዲሄዱ በማድረግ የሠሩትን እንዲህ ሲል አቀረበ «ሰዎችን በማታለል፣ ዓይኖቻቸውን በማሳወርና ልቦቻቸውን በማደንደን ክንውን አግኝተናል፡፡ እርሱ አስመሳይ መሆኑን በመናገር እንዲያምኑ አድርገናቸዋል፡፡ ያ የሮማ ወታደር የክርስቶስን መነሳት የሚያፋልስ የጥላቻ ወሬ ይነዛል፡፡ ቀሳውስቱና ሽማግሌ ዎች የሱስን እንዲጠሉትና እንዲገድሉት አድርገናል፡፡ አሁን ወሬው ሊያዝ ይገባዋል፧ ያለበለዚያ የየሱስ ትንሳኤ ከታወቀ ንጹሁን ሰው በመግደላቸው ሕዝቡ በድንጋይ ይወግራቸዋል፡፡” EWAmh 128.1

የሰማይ መላእክት ሰራዊተየየሱስን የመቃብር ስፍራ ለቅቀው ሲሄዱ በአካባቢው የነበረው ብርሃንና ክብር ካለፈ በኋላ የሮማ ወታደሮች hወደቁበት አንገቶቻቸውን ቀና ለማድረግ በመሞከር በዙሪያቸው ያለውን ተመለከቱ፡፡ መቃብሩ ተዘግቶበት የነበረው ትልቅ ድንጋይ ተንከባሎና የየሱስ አካል ሄዶ ሲመለከቱ በአግራሞት ተሞሉ፡፡ ወዲያውም ያዩትን ለቀሳውስቱና ለሽማግሌ ዎች ለማውራት ተቻኩለው ወደ ከተማ ሄዱ የየሱስ ገዳዮች አስገራሚውን ዘገባ ሲሰሙ ፊታቸው ገረጣ፡፡ ባደረጉት ነገር ብርክ ያዛቸው፡፡ የቀረበው ዘገባ በእርግጥም ትክክለኛ ከሆነ ጠፍተዋል፡፡ ለጊዜው በመካከላቸው ጸጥታ ነገሠ፡፡ እናም ምን ማድረግ ወይም ምን ማለት እንዳለባቸው ባለማወቅ አንዱ የሌ ላውን ፊት ይመለከት ጀመር፡፡ የቀረበውን ዘገባ ከተቀበሉ እራሳቸውን በጥፋተኛነት ሊኮንኑ ነው:፡፡ በመሆኑም ምን መደረግ እንዳለበት አስመልክቶ ወደ መምከሩ አመሩ፡፡ ይህ በጠባቂዎቹ አማካኝነት የመጣው መረጃ ወደ ሕዝቡ ዘንድ ቢዛመት ክርስቶስን ለሞት ያበቁት እንደ ገዳዮቹ ተቆጥረው ይታረዳሉ፡፡ በመሆኑም ወታደሮቹን በገንዘብ በመግዛት ጉዳዩን በምስጢር ለማስቀረት ውሳኔ ላይ ደረሱ:: በዚህም ቀሳውስቱና ሽማግሌዎቹ ለወታደሮቹ በቂ ገንዘብ በመስጠት «ተኝተን ሳለን ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰረቁት በሉ» አሏቸው: ወታደሮቹ ተረኛ ዘብ ሆነው ለምን እንተኙ ከበላይ ኃላፊዎች ጥያቄ ቢመጣባቸው የአይሁድ የኃይማኖት መሪ ዎች ጉዳዩን ለገዢው በማስረዳትና በማሳመን ደኅንነታቸው የተጠበቀ እንደሚሆን ቃል ገበላቸው:፡፡ የሮማው ጠባቂ ያን የተመለከቱትን ክብር በገንዘብ በመሽጥ በቀሳውስቱና በሽማግሌዎችቹ ምክር ለመስማማት ወሰነ፡፡ EWAmh 128.2

የሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ «ተፈጸመ” ብሎ ሲጮኽ ዐለቶች ተሰነጣጠቁ እንዲሁ ም አንዳንድ መቃብሮች ተከፈቱ፡፡ እርሱ በሞትና በሲኦል ላይ ድል አድርጎ ሲነሳ የሰማይ ክብር ቅዱሱ በነበረበት ስፍራ ላይ አበራ;፡፡ ብዙዎች አንቀላፍተው የነበሩ ለጥሪው ታማኝ ቅዱሳን ለክርስቶስ ትንሳዔ ምስክር ሆነው ከመቃብር ተነሱ፡፡ እነዚህ ከብረው ከሙታን የተነሱ ምርጥ ቅዱሳን በተለያየ የዕድሜ ክልል የሚገኙና ከፍጥረት አንስቶ እስከ ክርስቶስ ጊዜ ድ ረስ በተለያዩ ዘመናት በምድር የኖሩ ናቸው:፡፡ በመሆኑም የአይሁድ መሪዎች የክርስቶስን ትንሳዔ ለመደበቅ እየሞከሩ ባሉበት ጊዜ ክብሩን ይናገሩና የየሱን ትንሳኤ ይመሰክሩ ዘንድ እግዚአብሔር አንቀላፍተው የነበሩትን ከመቃብር ለማስነሳት መረጠ፡፡ EWAmh 129.1

የእነዚያ ከመቃብር የተነሱ ሰዎች የሰውነት አቋምም ሆነ ቅርጽ ይበልጥ የከበረ ዓይነት ገጽታ ይታይበት ነበር፡፡ የምድር ነዋሪዎች ቁልቁል እየወረዱ፣ የነበራቸውን ጥንካሬና ውበት እያጡ መሄዳቸው ተነግሮኝ ነበር፡፡ ሰይጣን በሽታና ሞት የማምጣት ኃይል ያለው በመሆኑ የዚህ እርግማን ውጤት በእያንዳንዱ የዕድሜ ክልል በገሃድ የሚታይ ሆኖአል:: በኖህና በአብርሃም ዘመን የኖሩ ሐዝቦች በሰውነት ቀርጻቸው፣ በደም ግባታቸውም ሆነ በጥንካሬአቸው ከመላእክት ጋር መመሳሰል ነበራቸው:: ነገር ግን እያንዳንዱ ትውልዳቸው ደካማና ይበልጥ ለበሽታ ተገዢ በመሆን ህይወታቸው በአጭር ዕድሜ የተገደበ ሆነ፡፡ ሰይጣን ሰብዓዊውን ዘር እንዴት ማስከፋትና ማዳከም እንዳለበት ትምህርት ሲቀስም ኖሮአል፡፡ EWAmh 129.2

ከየሱስ ትንሳኤ በኋላ ከመቃብር የተነሱት ለብዙዎች በመታየት ለሰው ልጅ የተከፈለው መስዋዕትነት ፍጻሜ ማግኘቱን፣ አይሁድ የስቀሉት የሱስ ከሞት መነሳቱን «እኛም ከእርሱ ጋር ተነስተናል» በማለት በተጨባጭ ማስ ረጃ በመናገር፧ በእርሱ ኃያልነት ከሙታን መነሳታቸውን መሰከሩላቸው፡፡ ምንም እንኳ የሐሰት ወሬ እንዲነዛ ቢደረግም የክርስቶስ ትንሳኤ በሰይጣን በመላእክቱ ወይም በቀሳውስት አለቆች ተሸፋፍኖ መቅረት አልቻለም: እነዚህ ቅዱሳን ሰዎች ከመቃብር በመነሳት አስደናቂና አስደሳች የሆነውን የምስራች አሰራጩ፡፡ እንዲሁም የሱስ አዝነውና ልባቸው ተስብሮ የነበሩ ደቀ መዛሙርቱን ኃዘን በማስወገድ ልባቸውን በደስታ ሞላው፡፡ EWAmh 129.3

ወሬው ከከተማ ወደ ከተማ እንዲሁም ከመንደር ወደ መንደር እየተስራጨሲሄድ አይሁድ በተራቸው ለህይወታቸው በመፍራት ወደ ደቀ EWAmh 129.4

ሙዛሙርቱ ለማዛመት አስበውት የነበረውን ጥላቻ በድብቅ ያዙት የእነርሱ ብቸኛ ተስፋ የሐሰት ወሬአቸውን ማዛመት ነበር፡፡ ደግሞም ይህ ሐስት እውነት እንዲሆን የተመኙ ተቀብለውታል፡፡ ጲላጦስ የክርስቶስን ትንሳኤ በሰማ ጊዜ ተርበደበደ፡፡ የሰማውን ምስክርነት መጠራጠር ያልተቻለውን ጲላጦስ---ሰላም ከዚያን ጊዜ አንስቶ ለዘላለም ተለይቶት ሄደ፡፡ ጲላጦስ ለምድራዊው ክብርና ዝና፣ ለሥልጣኑና ለህይወቱ ፍርሃት ስላደረበት የሱስን ለሞት አሳልፎ ሰጠው፡፡ ከዚህ በኋላ እርሱ ወንጀለኛ ሆኖ የተገኘው በአንድ ንጹህ, ሰው ደም ሳይሆን ነገር ግን በእግዚአብሔር ልጅ ደም መሆኑን ሙሉ በሙሉ አምኖ ተቀብሏል፡፡ የጲላጦስ ህይወት የመጨረሻዎቹ ምዕራፎች በእጅጉ በሐዘን የተሞሉ ነበሩ፡፡ እያንዳንዱን ተስፋውንና የነበረውን የደስታ ስሜት ሥቃይና ተስፋ ማጣት አደቀቀው፡፡ ጲላጦስ ለመጽናናት እምቢ በማለቱ በእጅጉ አሳዛኝ ሞት ደረሰበት፡፡ የሔሮድስ ልብ (ሔሮድስ አንቲጳስ በክርስቶስ ፍርድ ወቅት እጁ የነበረ ገዢ ሲሆን ሔሮድስ አግሪጳ ቀዳማዊ ደግሞ ያዕቆብ እንዲገደል ያደረገ ነው፡፡ አግሪጳ ለአንቲጳስ የወንድም ልጅና የሚስቱ ወንድም ነበር፡፡ እርሱ ሴራ በማሴር የአንቲጳስን መንግሥት ወረሰ፡፡ ወደ ሥልጣን በመጣ ጊዜ አንቲጳስ በክርስቲያኖች ላይ ይከተል የነበረውን ተመሳሳይ አቋም ያንጸባርቅ ነበር በሔሮድያውያን ሥርወ ንግሥት ስድስት ሰዎች ሔሮድስ በተሰኘው ስያሜ ተጠርተዋል፡፡ ምንም እንኳ እንደ አንቲጳስ፣ ፊሊፕ፣ አግሪጳ በመሳሰሉት ሌሎች ስያሜዎች የተጠሩ ግለሰቦች ቢኖሩም ነገር ግን ሔሮድስ የተስኘው ስያሜ እንደ ጥቅል መጠሪያ አገልግሎአል፡፡ ይህ ስያሜ ዛር ኒኮላስ፣ ዛር አሌክሳንደር ወዘተእንደማለተነው:) በእጅጉ ደንድኖ ነበር፡፡ እርሱ ስለ ክርስቶስ ትንሳኤ በሰማ ጊዜ እምብዛም አልተሸበረም ነበር፡፡ ሔሮድስ የያዕቆብን ህይወት መቅጠፉ አይሁድን እንዳስደሰታቸው በተመለከተ ጊዜ ጴጥሮስንም እንዲሁ ለመግደል አስያዘው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በጴጥሮስ የሚሠራው ሥራ ስለነበረው ከእርሱ ያድነው ዘንድ መልአኩን ላከ፡፡ ሔሮድስ በአምላካዊው ፍርድ ተጎብኝቷል፡፡ ሔሮድስ ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት ለእግዚአብሔር የሚሰጠውን ክብር ለራሱ በመወሰዱ የጌታ መልአክ መታውና ዘግናኝ ሞት ደረሰበት፡፡ EWAmh 130.1

በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ማለዳ ላይ ገና ብርሃን ከመፈንጠቁ አስቀድሞ ቅዱሳን ሴቶች የየሱስን አካል ሽቶ ለመቀባት ወደ መቃብሩ መጡ፡፡ በስፍራው እንደ ደረሱ ግዙፉ የመቃብሩ ድንጋይ ተንከባሎ የነበረ ሲሆን፧ የየሱስም አካል በስፍራው hልነበረም:፡፡ ልባቸው በማዘኑ ጠላቶቻቸው አካሉን ወስደውት ይሆናል የሚል ፍራቻ አደረባቸው፡፡ ሳይታሰብ ነጭ ልብስ የለበሱ፣ ፊታቸው የሚያበራ ሁለት መላእክት ተመለከቱ፡፡ እነዚህ ስማያዊ ፍጡራን ሴቶቹ ይሹ የነበረውን በማስተዋል የሰ ስ በዚያ እንደሌለ፤ ነገር ግን እንደተነሳና ፍላጎታ ው ከሆነ ተኝቶ የነበረበትን ቦታ እንያዩ ነገሯቸው፡፡ ሴቶቹ ፈጥነው ወደ ደቀ መዛሙርቱ በመሄድ የሱስ ከሙታን እንደተነሳና ቀድሞአቸው ወደ ገሊላ እንደሚሄድ ንገሯቸው አሏቸው፡፡ ሴቶቹም በፍርሃትና በደስታ ተሞልተው አዝነው ወደነበሩት ደቀ መዛሙርቱ በፍጥነት በማምራት ያዩአቸውንና የሰሟቸውን ነገሮች ነገሯቸው፡፡ EWAmh 130.2

ደቀ መዛሙርቱ የክርስቶስን ትንሳኤ ማመን አልቻሉም ነበር፡፡ በመሆኑም ዜናውን ይዘው ከመጡት ሴቶች ጋር በመሆን ወደ መቃብሩ ስፍራ በፍጥነት እየገሰገሱ ሄዱ፡፡ በስፍራው እንደ ደረሱ የሱስ በዚያ አልነበ ረም፡፡ ምንም እንኳ ከተልባ እግር የተሠራውን የከፈን ጨርቁን ቢመለከቱም ነገር ግን ከሙታን የመነሳቱን የምስራች ማመን አልቻሉም ነበር፡፡ ደቀ መዛሙርቱ በተመለከቱት ነገርና ሴቶቹ ይዘውት በመጡት የምስራች በመደመም ወደቤታቸው ተመለሱ፡፡ ማርያም ግን የተመለከተችውን ነገር እያሰበችና ምናልባትም ተታልላ እንዳይሆን ተስፋ በቆረጠ ስሜት መቃብሩ አካባቢ መቅረት መረጠች፡፡: አዳዲስ ፈተናዎች ሊጠብቋት እንደሚችሉ ተስምቷታል ሐዘኗ ታደሰና ዳግመኛ አምርራ ማንባቷን ቀጠለች፡፡ ማርያም እያለቀሰች እንደገና ወደ መቃብሩ ለመመልከት ጎንበስ ስትል የየሱስ ሥጋ በነበረበት ቦታ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት መላእክት አንዱ በራስጌ ሌላው በግርጌ ተቀምጠው አየች:፡፡ መላእክቱ በጣም በተለሳለሰ አነጋገር ለምን እንደምታለቅስ ጠየቋት፡፡ እርሷም «ጌታዬን ወስደውታል የት እንዳኖሩትም አላውቅም” በማለት መለሰችላቸው፡፡ EWAmh 131.1

ይህን ብላ ከመቃብሩ ዘወር ስትል የሱስን በዚያው ቆሞ አየችው፧ ነገር ግን አላወቀችውም ነበር የሱስም ትህትና በተሞላው አነጋገር ለምን እንደምታዝንና የምትፈልገው ማንን እንደሆነ ጠየቃት፡፡ እርሷም የኣትክልቱ ቦታ ጠባቂ መስሏት የጌታዋን ሥጋ ለመውሰድ እንደምትፈልግ በመናገር የት እንዳኖረው ይነግራት ዘንድ ለመነችው፡፡ በዚህን ጊዜ የሱስ በሰማያዊው ድምጹ ‹ማርያም!» አላት፡፡ ማርያም ይሀን የከበረ ድምጽ ታውቀው ስለነበር ወዲያውኑ «መምህር ሆይ!” በማለት መለሰችለት፡፡ ማርያም ከደስታዋ ብዛት ልትጠመጠምበት ብትልም የሱስ ግን «ገና ወደ አብ ስላላረግኩ አትንኪኝ፧ ይልቁንስ ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፤ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዐርጋለሁ ብሎአል ብለሽ ንገሪያቸው አላት»፡፡ እርሷም የምስራቹን ይዛ በፍጥነት ወደ ደቀ መዛሙርቱ አመራች የሱስ አባቱ መስዋዕቱን መቀበሉን ከአፉ ለመስማትና በሰማይና በምድር ያለውን ኃይል ሁሉ ለመቀበል ወዲያውኑ ወደ አባቱ አረገ፡፡ EWAmh 131.2

መላእክት ልክ እንደ ደመና የእግዚአብሔርን ልጅ ከከበቡት በኋላ የክብር ንጉሥ ይግባ ሰማያዊ ደጆችም ይከፈቱ ሲሉ ተናገሩ፡፡ የሱስ ብሩህ ከሆኑ የሰማይ ሠዊት ጋር በመሆን እግዚአብሔር ባለበ ስፍራ ላይ በአብ ክብር ተከብቦ ተመለከትኩ፡፡ የሱስ ከአባቱ ኃይል ከተቀበለ በኋላ በምድር ወዳሉት ደቀ መዛሙርቱ በመመለስ ኃይል ይሰጣቸዋል እንጂ አልረሳቸውም ነበር፡፡ የሱስ የዚያኑ ቀን ወደ ምድር በመመለስ እራሱን ለደቀ መዛሙርቱ አሳያቸው፡፡ እርሱ ወደ አብ ዘንድ በመሄድ ኃይል ተቀብሎ ስለመጣ ይነኩት ዘንድ ነገራቸው፡፡ EWAmh 131.3

በወቅቱ ቶማስ በስፍራው አልነበረም: በደቀ መዛሙርቱ የቀረበውን ዘገባ በትህትና ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆነው ቶማስ በምስማር የተቸነከሩትን የእጆቹን ምልክቶች ካላየ፣ ምስማሮቹ በነበሩበት ቦታ ጣቱን ካላደረገ በጎም እጁን ካላስገባ እንደማያምን ተናገረ፡፡ ቶማስ በዚህ አነጋገሩ በወንድሞች ላይ የነበረውን ኣለመተማመን አሳየ:: ሁሉም እንደ ቶማስ ማስረጃ እንዲቀርብላቸው ቢጠይቁ ኖሮ ከመካከላቸው አንዳቸውም አሁን የሱስን ባልተቀበሉና በትንሳኤውም ባላመኑ ነበር ነገር ግን አምላካዊው ፈቃድ ሆነና ከሙታን የተነሳውን ጌታ በዐይኖቻቸው ማየትም ሆነ በጆሮዎቻቸው መስማት ያልቻሉት ወገኖች የደቀ መዛሙርቱን ዘገባ ተቀበሉ፡፡ አግዚአብሔ ር በቶማስ አለማመን ደስተኛ አልነበረም፡፡ የሱስ እንደገና ደቀ መዛሙርቱን በተገናኛቸው ጊዜ ቶማስ ከእነርሱ ጋር ስለ ነበር የሱስን ሲመለከተው አመነ፡፡ ነገር ግን ይህ ደቀ መዝሙር ካላየው በቀር በተነገረው ነገር ሊረካ እንደማይችል በይፋ ተናግሮ የነበረ ሲሆን የሱስም የተመኘውን ተጨባጭ መረጃ ሰጠው:: ቶማስ የሱስን በተመለከተጊዜ «ጌታዬ፧አምላኬም!” በማለት ጮኸ፡፡ ነገር ግን የሱስ ጥርጣሬውን በመገሰጽ «አንተስላየኸኝ አምነሃል ሳያዩ የሚያምኑ ግን ብጹአን ናቸው” አለው፡፡ EWAmh 132.1

ከዚህ በተመሳሳይ በመጀመሪያውና በሁለተኛው መልአክ መልእክት ላይ አንዳችም ተሞክሮ ያልነበራቸው ሰዎች ከሌሎች ልምዱ ካላቸውና መልአክቶቹን ከተቀበሉ ሊቀበሉ የግድ ነው፡፡ የሱስ ነቀፋ አንደ ደረሰበት ሁሉ እነዚህም መልአከቶች ሲነቀፉ ተመልክቻለሁ፡፡ ደኅንነት በሌላ በማንም እንደማይገኝ፧ እንድንበት ዘንድ ለሰዎች የተሰጠ ከዚህ ስም በስተቀር ሌላ ስም ከሰማይ በታች እንደሌለ ደቀ መዛሙርቱ በይፋ እንደተናገሩ ሁሉ፤ ሰዎች ከሦስተኛው መልአክ መልእክት ጋር ቁርኝት ያለውን የተወሰነውን የእውነት ክፍል ብቻ መያዝ ሳይሆን ነገር ግን .ሁሉንም መልእክቶች እግዚአብሔር እንደሰጣቸው በማመን በደስታ ሊቀበሏቸው እንደሚገባ ወይም ከጉዳዩ ገሸሽ እንዲሉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች በታማኝነትና እርሱን በመፍራት ሊነግሯቸው ይገባል፡፡ EWAmh 132.2

ቅዱሳን ሴቶች የየሱስን ትንሳኤ የምስራች ይዘው ሲሄዱ የሮም ወታደሮች ግን በቀሳውስት አለቆችና ሽማግሌዎች የተነገራቸውን ይዘው እነርሱ እንደተኙ ደቀ መዛሙርቱ በሊት መጥተው በማለት ሐሰት አዛመቱ፡፡ ሰይጣን ይህን ሐሰት በቀሳውስት አለቆችና በሽማግሌዎቹ ልብና አፍ ላይ አስቀምጦ የነበረ ሲሆን ሕዝቡም ቃላቸውን ለመቀበል ዝግጁ ሆኖ ይጠባበቅ ነበር:: እግዚአብሔር ግን ጉዳዩን የተረጋገጠ በማድረግ ይህንን የደኅንነታችንን መሰረት ቀሳውስትና ሽማግሌዎች ሊሸፋፍኑ በማይችሉት ከማንኛውም ጥርጣሬ በጸዳ መልኩ እርግጠኛ አድረጎ አስቀመጠው: በመቃብር የነበሩ ከሞት በመነሳት ለክርስቶስ ትንሳኤ ምስክር ሆኑ፡፡ EWAmh 132.3

የሱስ ደቀ መዛሙርቱን ደስ ያሰኛቸውንና ልባቸውን በሐሌት የሞላውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ተጨባጭ ውነታ ምንነተሙሉ ለሙሉ እየገለጠላቸው አብሮአቸው ለአርባ ቀናት ቆየ: ደቀ መርቱ የሱስ ስለ ደረሰበተሥቃይ፣ ስለ ሞቱና ትንሳኤው፣ ለኃጢአት መስዋዕተስለመነና ወደ እርሱ የሚመጡ ሁሉ ህይወት እንደሚያገኙ ባዩአቸውና በሰሟቸው ነገሮች ምስክር ይሆኑት ዘንድ ሾማቸው: ደቀ መዛሙርቱ ስደትና ሥቃይ እንደሚደርስባቸው፤ ይህም ቢሆን ግን የቀድሞ ተሞክሮአቸውንና እርሱ የራቸውን ቃት በማስታወስ እፎይታ እንደሚያኙ በትህትና አስታውቆአቸዋል:: እርሱ የሰይጣንን ፈተናዎች በማሸነፍ በአስቸጋሪ ሁናቴዎችና ቢሥቃይ ላይ ድል መቀዳጀቱን በመንገር ከዚህ በኋላ ሰይጣን በእርሱ ላይ ኃይል ሊኖ ረው እንደማይችል፤ ነገር ግን ፈተናዎቹን በቀጥታ በእነርሱና በስሙ በሚያምኑ ላይ እንደሚያመጣና እነርሱም ልክ እንደርሱ ሊያንፉት እንደሚችሉ ገለጸላቸው: የሱስ ደቀ መዛሙርቱ ተአምራት የሚያደርበትን ኃይል በመስጠት ምንም እንኳ በክፉዎች ስደት ለደርስባቸው ቢችልም ነገር ግን ያድኗቸው ዘንድ ከጊዜ ወደ ዜ መልአክቶቹን እንደሚልክላቸው በመንገር ተልእኮአቸውን ወደ ፍጻሜ እስኪያመጡ ድረስ ህይወታቸው ላይ አደጋ እንደማይደርሰ፤ ከዚያም ምስክርነታቸውን በደማቸው ያትሙ ዘንድ እንደሚጠየቁ ነገራቸው:: EWAmh 133.1

ቅዱስ ከሆነው ከየሱስ አንደበት ይወጡ በነበሩት ቃላት በእጅጉ ደስ በመሰኘት ደቀ መዛሙርቱ አስተምህሮውን በደስታና በጉጉት ያደምጡ ነበር፡፡ አሁን እርሱ: በእርግጥም የዓለም አዳኝ እንደነበር አውቀዋል ሰማያዊው መምህር በቅርቡ እንደሚለያቸው የተረዱት ደቀ መዛሙርት ከዚህ በኋላ ከአንደበቱ ይወጡ የነበሩትን አጽናኝ ደግ፣ ቸርና መሃሪ ቃላት የማይሰሙ መሆናቸውን ሲረዱ ሐዘን ተሰማቸው፡፡ ነገር ግን የሱስ ወደ ሰማይ የሚሄደው ስፍራ ሊያዘጋጅላቸው መሆኑንና ሄዶም ስፍራ ካዘጋጀ በኋላ እርሱ ባለበት እነርሱም ይሆኑ ዘንድ ሊወስዳቸው ዳግመኛ እንደሚመጣ፣ ከዚያም ለዘላለም ከእርሱ ጋር እንደሚሆኑ ሲነግራቸው ልባቸው በፍቅር ሞቀ፤ በደስታም ተሞላ፡፡ በተጨማሪም ወደ እውነት ሁሉ ይመራቸው ዘንድ አጽናኙን እንደሚልክላቸው ቃል ገባላቸው «እጆቹንም አንስቶ ባረካቸው»፡፡ EWAmh 133.2