ቀደምት ጽሑፎች
21—የዊልያም ሚለር ህልም
በሕልሜ እግዚአብሔር በማይታይ እጅ አሥር ኢንች በስድስት ካሬ እርዝማኔ ያለውን ከጠንካራ ጥቁር እንጨት የተሠራና ፈርጦች ያሉትን የሬሳ ሣጥን ወደ እኔ እንደ ላከ ተመለከትኩ፡፡ ወዲያውኑ ቁልፍ አመጣሁና የሬሳ ሣጥኑን ከፈትኩት፡፡ በጣም በሚያስገርም መልኩ ሳጥኑ ሁሉም ዓይነት መጠን በነበራቸው ጌጣጌጦች እንቁዎች፣ የከበሩ ድንጋዮች፣ የወርቅና የብር ሣንቲሞች በሁሉም ቦታ ውብ ሆነው ተደርድረው ነበር:: እነዚህ የከበሩ ድንጋዮች ከውስጣቸው ያወጡ የነበረው የብርሃን ጨረር እና ክብር የሚስተካከሉት ከፀሐይ ጋር ብቻ ነው፡፡ EWAmh 60.1
ልቤ በደስታ ቢዘልም ነገር ግን ይህን ውብና የከበረ ዋጋ ያለውን ትዕ ይንት ብቻዬን እያየሁ መደሰት እንደሌለብኝ አሰብኩ፡፡ በክፍሌ አማካኝ ስፍራ ላይ በማስቀመጥ ሰው በህይወቱ ሙሉ አይቶት የማያውቀውን ይህን በእጅጉ አስደናቂ ትዕይንት ማንም መጥቶ መመልከት እንደሚችል ቃሌን ሰጠሁ: EWAmh 60.2
ሰዎች መምጣት ጀመሩ፡፡ በመጀመሪያ ላይ ቁጥራቸው አነስተኛ የነበ ረ ቢሆንም ነገር ግን ብዙ እስኪሆኑ ድረስ የጨመሩ ይሄዱ ነበር፡፡ ማንኛ ውም ሰው ገና በመጀመሪያ በሬሳ ሣጥኑ ውስጥ ያሉትን ከበሩ ነገሮች እንደተመለከተአግራሞት ይዞት በደስታ ይጮኽ ነበር ሆኖም ተመልካቾች በጨመሩ ቁጥር የከበሩትን ጌጣጌጦች ማተራመስና ከሬሳ ሣጥኑ ውስጥ እያወጡ ጠረጴዛ ላይ መበተን ጀመሩ፡፡ EWAmh 61.1
ባለቤቱ ይህን በእጄ ላይ ያለውን የሬሳ ሣጥንም ሆነ ጌጦቹን ሊጠይቀኝ ይችላል ብዬ ማስብ ጀመርኩ፡፡ ጌጦቹ እንዲበታተኑ የምፈቅድ ከሆነ በቀድሞ አቀማመጣቸው መልሼ ልደረድራቸው አልችልም፡፡ ስለዚሀ መጠነ ሰፊ ለሆነው ስህተት ተጠያቂ ሆኜ መቅረብ መቻል የለብኝም በማለት ሰዎች ጌጦቹን በእጃቸው መንካትም ሆነ ከሬሳ ሣጥኑ ውስጥ ማውጣት እንደሌ ለባቸው መለመኔን ቀጠልኩ፡፡ ነገር ግን አብልጬ በለመንኳቸው ቁጥር አብዝተው በመበተን ጭራሹኑ በየክፍሉና በየወለሉ ይዘሯቸው ጀመር፡፡ EWAmh 61.2
ሰዎቹ ከበተኗቸው ከእውነተኛ የከበሩ ጌጦችና ሣንቲሞች መካhል ሊቆጠሩ የማይችሉ ብዛት ያላቸውን ሐስተኛ ጌጦችና አስመስለው የተሠሩ ሣንቲሞችን ተመለከትኩ፡፡ በዚህ አጉል ባህሪያቸው በእጅጉ በመበሳጨት ወቀሳና ግሳጼ ሰነዘርኩባቸው፡፡ ነገር ግን አብልጬ በገጽኳቸው ቁጥር ሐሰተኞቹን ጌጦቻቸውንና ሳንቲሞቻቸውን በእውነተኛዎቹ መሃል አብዝተው ይበትኑ ነበር፡፡ EWAmh 61.3
ከዚህ በኋላ በእጅጉ በመናደድ ከክፍሉ እየገፈታተርኩ ለማስወጣት ኃይል መጠቀም ጀመርኩ፡፡ ሆኖም አንዱን ሳስወጣ ሌሎች ሦስት ተጨማሪ ሰዎች እውነተኛዎቹን ጌጦች፣ እንቁዎችና ሣንቲሞች እስኪሸፍኑና ከዕይታ እሰኪያጠፏቸው ድረስ አፈር ልጣጭ፣ አሸዋና ሁሉንም ዓይነት ቆሻሻዎች ይዘው ይገቡ ነበር፡፡ በተጨማሪ የሬሳ ሣጥኑንም ሰባብረው ከቆሻሻው ጋር በትነውት ነበር ማንም ሃዘኔንም ሆነ ቁጣዬን እንዳላየልኝ በማሰብ በእጅጉ ተስፋ በመቁረጥ ቁጭ ብዬ አነባሁ፡፡ EWAmh 61.4
ለደረሰብኝ ታላቅ እጦትና ተጠያቂነት እግዚአብሔርን አስታወስኩና አርዳታውን ጠየቅኩት፡፡ እያለቀስኩና እያነባሁ እያለ ይልክልኝ ዘንድ በጽናት EWAmh 61.5
ወዲያውኑ በራፉ ተከፈተና አንድ ሰው ጠራርገው ከክፍሉ ወጡ፡፡ ሰውየው የቆሻሻ መስኮቶቹን ከፈተና ቆሻሻዎቹን እየጠረገ ከክፍሉ ማውጣት ጀመረ: ወደ ክፍሉ ገባ፡፡ ሰዎቹ ተመጥረጊያ በእጁ የያዘ ሲሆን EWAmh 61.6
ከቆሻሻው መሃል የተበተኑ የከበሩ ጌጦች ስለሚኖሩ መጥረጉን እንዲያቆም እያለቀስኩ ለመንኩት፡፡ EWAmh 61.7
ሰውየውም አትፍራ እርሱ ይጠነቀቅላቸዋል” አለኝ፡፡ ከዚያም ቆሻሻውን እየጠረገና እያጸዳ እያለ ሐስተኛ ጌጦችና ተመሳሳይ ሣንቲሞቹ ሁሉም ብድግ ብለው በመስኮቱ እንደ ደመና ብን ብለው ሄዱ፡፡ ነፋስም ጠራርጎ ወሰዳቸው፡፡ በጥድፊያው መሃል ለጊዜው ዐይኖቼን ጨፍኜ ነበር፡፡ ነገር ግን በገለጥኳቸው ጊዜ ቆሻሻው ሁሉ ተወግዶ ሁሉም የከበሩ ጌጦች፣ እንቁዎች የወርቅና የብር ሣንቲሞች በየክፍሉ ውስጥ ሞልተውና ተበታትነው ይገኙ ነበር: EWAmh 61.8
ከዚያም የሬሳ ሣጥኑን በጠረጴዛው ላይ በማስቀመጥ ከቀድሞዎቹ የላቀ ብዛት ያላቸውና ይበልጥ ውብ የሆኑ ጌጦችን፣ እንቁዎችንና ሣንቲሞችን እያፈሰ አንድም ሳይቀር ሣጥኑ ውስጥ ከተታቸው፡፡ ምንም እንኳ አንዳንዶቹ እንቁዎች የመርፌ ጫፍ ያህል መጠን ቢኖራቸውም ነገር ግን ሁሉም ተሰብስበው ተከትተው ነበር፡፡ ከዚያም ጠራኝና «ና ተመልከት” አለኝ፡፡ ወደ ሬሳ ሣጥኑ ውስጥ ስመለከት በትዕይንቱ ዐይኖቼ ተብረቀረቁ:፡፡ ከመጀመሪያው አሥር ጊዜ እጥፍ የከበሩ ሆነው ነበር፡፡ በእነዚያ ክፉ ሰዎች አማካኝነት ከአሸዋውና ቆሻሻው ጋር ተደባልቀው የጠፉ መስሎኝ የነበረ ቢሆንም እርሱ ግን በሚያምር አቀማመጥ በሣጥኑ ውስጥ ሁሉንም በየቦታቸው ደርድሯቸው ነበር፡፡ ጌጦቹን ደርድሮ ባስቀመጣቸው ሰው ላይ አንዳችም ጉዳት ወይም ህመም አይታይበትም ነበር፡፡ በዚህን ጊዜ ታላቅ የደስታ ጩኸት ጮኽኩ፡፡ ጩኸቱ ከእንቅልፌ አነቃኝ፡፡ EWAmh 62.1