ቀደምት ጽሑፎች
20—የሚስስ ኋይት ህልሞች
ብዙ ሰዎች ወደ ውስጥ ይጎርፉበት የነበረን ቤተመቅደስ በሕልሜ አየሁ፡፡ ጊዜው ፍጻሜ ባገኘ ጊዜ በዚያ ቤተመቅደስ መሸሸጊያ ያገኙ ብቻ ሲድኑ ነገር ግን ከቤተመቅደሱ ውጪ ያሉ ሁሉ ለዘላለም ይጠፉ ነበር፡፡ የራሳቸውን የተለያዩ መንገዶች ይጓዙ የነበሩና መሸሸጊያ ያልነበራቸው አያሌ ሕዝቦች ወደ መቅደሱ የሚገቡትን---ይህ የደህንነት እቅዳቸው ማጭበርበር EWAmh 58.1
እንጂ በእርግጥ የሚመጣ አንዳችም አደጋ እንደሌለ እያሾፉ ይነግሯቸው ነበር እነዚህ ስዎች ከዚህም አልፈው አንዳንዶች በፍጥነት ወደ ቤተመቅደሱ እንዳይገቡ ገትተዋቸው ነበር እነዚህ ሰዎች እንዳይሳለቁብኝ ስለፈራሁ ወደ ቤተመቅደሱ ለመግባት የተሻለው መንገድ ሰዎቹ እስኪበተኑ መጠበቅ ወይም ሳያዩኝ ሹልክ ብዬ መግባት እንደሆነ አሰብኩ፡፡ ሆኖም እነዚህ ሕዝቦች ከመበተን ይልቅ እየጨመሩ ይሄዱ ነበር እኔም በጣም በመዘግየቴ ፍርሃት ገባኝ፡፡ ከዚያም ቤቴን በፍጥነት ትቼ በሕዝቡ መሃል ስንጥቄ ተጓዝኩ፡፡ ወደ መቅደሱ ለመድ ረስ በነበረኝ ጭንቀት ከብቦኝ የነበረውን ሕዝብ ልብ አላልኩም ወይም ለእነርሱ ግድ አልነበረኝም:: በሕንጻው መግቢያ ላይ የተንጣለለ መቅደስ ተመለከትኩ፡፡ መቅደሱ በአንድ ግዙፍ ምሰሶ ተደግፎ ነበር የቆመው:: በምሰሶው ላይ ጠቦት በግ ታስሮ የነበረ ሲሆን ጠቦቱ ተወግቶ እየደማ ነበር፡፡ እኛ በዚያ ቦታ የነበርነው ይህ ጠቦት ለእኛ ሲል እንደተመታና እንደቆስለ የምናውቅ ዓይነት ነበርን፡፡ ወደ መቅደሱ የሚገቡ ሁሉ ወደ ፊቱ በመምጣት ኃጢአታቸውን መናዘዝ ነበረባቸው፡፡ EWAmh 58.2
ጠቦቱ ወደ ላይ ከፍ ከፍ ሊል ሲል ሕዝቡ በተቀመጡባቸው መቀመጫ ዎች ላይ እንዳሉ ከፍተኛ ደስታ ይታይባቸው ነበር፡፡ ሰማያዊው ብርሃን በፊቶቻቸው ላይ የሚያንጸባርቅባቸው ይመስል ነበር እነርሱም እግዚኣብሔ ርን እያመሰገኑ የመላእክት ዓይነት የደስታ ዝማሬ ያስሙ ነበር፡፡ እነዚህ ሕዝቦች ወደ ጠቦቱ የመጡ፣ ኃጢአቶቻቸውን የተናዘዙና ይቅር ተብለው አሁን አስደሳች የሆነውን ጊዜ የሚጠባበቁ ናቸው፡፡ EWAmh 58.3
ወደ ህንጻው ውስጥ ከገባሁ በኋላም እንኳፍርሃት ተሰምቶኝ ነበር፡፡ ደግሞም በእነዚህ ሕዝቦች መሃል እራሴን ማዋረዱ የሚያሳፍር ሆኖብኝ ነበር ነገር ግን ወደፊት እንድንቀሳቀስ ግፊት እንደተደረገብኝ ሆኖ ተሰማኝ፡፡ ከዚያም ጠቦቱን ለመጋፈጥ በዝግታ ወደ መሰሶው አመራሁ፡፡ የመለከት ድምፅ በተሰማ ጊዜ መቅደሱ ተንቀጠቀጠ---የድል አድራጊነት ጩኸትም ከተሰበሰቡት ቅዱሳን ተደመጠa አስፈሪ ብርሃን በሕንጻው ላይ ፈነጠቀና ሌ ላው አካባቢ ግን በጽልመት ተዋጠ፡፡ ደስተኞቹ ሕዝቦች በሙሉ አንጸባራዊ ሆነው ከዐይን ተሰወሩ፡፡ እኔም በዚያ ረጭ ባለና በጽልመት በተዋጠ አስፈሪ ምሽት ብቻዬን ቀረሁ EWAmh 58.4
በከፍተኛ ሁኔታ ጭንቅላቴን ከብዶኝና አሞኝ ስነቃ በሕልም ላይ እንደነበርኩ እራሴን ለማሳመን ተቸግሬ ነበር፡፡ በዚህን ጊዜ የጌታ መንፈስ ዳግም ላይመለስ ትቶኝ እንደሄደና የመጥፋቴ ነገር ያበቃለት እንደሆነ አሰብኩ፡፡ ጥልቅ ተስፋ መቁረጥ ተሰማኝ፡፡ EWAmh 59.1
ይህ በሆነ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ሌላ ህልም hለምኩ: በተስፋ መቁ ረጥ ስሜት እጆቼን ፊቴ ላይ አድርጌ እንዲህ አልኩ: የሱስ ምድር ላይ ቢሆን ኖሮ ወደ እርሱ በመሄድ እኔነቴን በእግሮቹ ስር ጥዬ ሥቃዬን ሁሉ እነግረው ነበር፡፡ እርሱ ፊቱን አያዞርብኝም ምህረት ያደርግልኛል እኔም አፈቅረዋለሁ ሁልጊዜም አገለግለዋለሁ፡፡ በዚህን ወቅት በር ተከፈተና ውብ አቋምና ገጽታ ያለው ሰው ገባ፡፡ ከዚያም በኃዘኔታ ወደ እኔ ተመለከተና እንዲህ አለኝ «የሱስን ለማየት ትመኛለሽ? እርሱ ያለው እዚሁ በመሆኑ የተመኘሽውን ልታይ ትችያለሽ፡፡ ያለሽን ያዢና ተከተይኝ››፡፡ EWAmh 59.2
ይህን በአንደበት ሊገለጽ የማይችል ደስታ ከሰማሁ በኋላ ያሉኝን ጥቂት ንብረቶችና ጥቃቅን ጌጣ ጌጦች በሙሉ ሰብስቤ መሪዬን ተከተልኩ፡፡ እርሱም ቀጥ ባለና አደጋ የማይችል በሚመስል ደረጃ ላይ የመራኝ ነበር፡፡ ደረጃዎቹን ወደ ላይ መውጣት ስጀምር ምናልባት አዳልጦኝ እንዳልወድቅ ወደ ላይ ብቻ እንድመለከት ነገረኝ፡፡ ደረጃውን ከሚወጡት መሃል ጫፍ ላይ ሳይደርሱ የሚወድቁ ብዙዎች ነበሩ፡፡ EWAmh 59.3
በመጨረሻ ጫፍ ላይ ያለው ደረጃ ላይ በመድረስ በራፉ ላይ ቆምን፡፡ መሪዬ ይዤ የመጣሁትን ሁሉንም ነገር እዚሁ እንድተወው ነገረኝ፡፡ እኔም በደስታ ካስቀመጥኳቸው በኋላ በሩን ከፍቶ አስገባኝ፡፡ ወዲያው ከየሱስ ፊት ቆሜ ነበር ያ ውብ ገጽታ የእርሱ መሆኑ ያለ ምነም ስህተት ተለይቶ ይታወቃል: ምክንያቱም እንደዚያ ግርማ የተላበስ ደስታና ፍቅር የማንም ሊሆን አይችልም፡፡ ወደ እኔ መልከት ሲያደርግ ከእያንዳንዱ የህይወቴ ክፍል ጥልቅ አስተሳሰቤንም ሆነ ስሜቴን አብጠርጥሮ እንደሚያውቅ ኣሰተዋልኩ፡፡ EWAmh 59.4
ሰርስረው የሚፈትሹትን ዐይኖቹን መቋቋም ባለመቻሌ እራሴን ከምልከታው ለመጋረድ ሙከራ ባደርም ነገር ግን ፈገግ ብሎ ወደ እኔ ቀረበና እጁን በአናቴ ላይ አሳርፎ «አትፍሪ” አለኝ፡፡ ጣፋጭ ድምጹ ከዚያ በፊት ልቤን ተሰምቶት በማያውቀው ደስታ ሞላው፡፡ ከደስታ ብዛት አንዳች ነገር ለመናገር ፈልጌ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን እጅግ ከፍ ባለ ሐሴት በመሸነፌ እግሮቹ ላይ ፊቴን እንደደፋሁ ስምጬ ቀረሁ:፡፡ እራሴን መቆጣጠር አቅቶኝ በዚያ ቦታ ላይ እንደተዘረርኩ ውበትና ግርማ የተላበሰ ትዕይንት በፊቴ ኣለፈ፡፡ እኔም የሰማይ ሰላምና ደህንነት ላይ እንደ ደረስኩ ተሰማኝ፡፡ ቀስ እያለ ብርታቴ ተመለሰልኝና ተነሳሁ፡፡ አፍቃሪዎቹ የየሱስ ዐይኖች አሁንም በእኔ ላይ ነበሩ፡፡ ፈገግታው ነፍሴን ደስ አሰኛት፡፡ የርሱ መገኘት በተቀደሰ አክብሮትና ሊገለጽ በማይችል ፍቅር ሞላኝ፡፡ አሁን ያ የሚመራኝ በሩን ከፈተና ሁለታችንም ወጥተን ሄድን፡፡ ከዚያም በራፉ ላይ የተውኳቸውን መልሼ እንድወስድ ከነገረኝ በኋላ አረንጓዴ ጥቅል ሲባጎ ሰጠኝና ከልቤ አጠገብ በእቅፌ እንድይዘው ነገረኝ፡፡ የሱስን ማየት በምፈልግ ጊዜ ሲባጎውን ከእቅፌ አውጥቼ እስከ መጨረሻው እዘረጋዋለሁ፡፡ ሲባጎው ሳይተረተር ረዘም ላሉ ጊዜያቶች መቆየት እንደሌ ለበት አስጠንቅቆኛል:: ምክንያቱም እንደ ተጠቀለለ ከቀረ ከዚያ በኋላ ለመተርተር አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን ጥቅል ሲባጎ ከልቤ አጠገብ ካኖርኩት በኋላ ጌታን እያመሰገንኩና ላገኘኋቸው በሙሉ ማንን እንደተገናኘሁና እነርሱም የሱስን የት ማግኘት እንደሚችሉ በደስታ እየተናገርኩ ጠባቡን ደረጃ ወረድኩ፡፡ ይህ ሐልም ተስፋ ሰጠኝ፡፡ አረንጓዴው ጥቅል ሲባጎ በአእምሮዬ ውስጥ ያለውን እምነት ይወክላል፡፡ ከዚህ በኋላ ውብና ውስብስብ ያልሆነው በእግዚአብሔር የመታመን ነገር በነፍሴ ውስጥ መስረጽ ጀመረ፡፡ EWAmh 59.5