ቀደምት ጽሑፎች
17—ለመጨረሻው ጊዜ ዝግጅት ማድረግ
የጌታ ሕዝቦች በጌታ ቀን ውጊያ ላይ መሰለፍ ከመቻላቸው አስቀድመው ታላቅ ሥራ ሊሠራ እንደሚገባ ጌታ በ ኦስዌጎ ኒው ዮርክ መስከረም 7 / 1850 ዓ.ም. ላይ በራእይ አሳይቶኝ ነበር፡፡ አድቬንቲስቶች ነን ብለው እራሳቸውን ወደሚጠሩ ነገር ግን ወቅታዊውን እውነት ወደሚቃወሙ እንድመለከት ተደረግኩ፡፡ በዚህ በመሰብሰቢያ ወቅት እነርሱን ይከፋፍልና ይበታትን ዘንድ የጌታ እጅ በላያቸው ስለ ነበር አየከሰሙ ሲሄዱ ይስተዋሉ ነበር፡፡ እነዚያ ቀደም ብለው ተታለው የነበሩ በመካከላቸው ያሉ የከበሩ ዕንቁ ዎች ዐይኖቻቸውን ከፍተው እነዚህ ሰዎች የሚገኙበትን እውነተኛ ሁናቴ እንዲመለከቱ ተደርገዋል፡፡ አሁን በጌታ መልእክትኞች አማካኝነት እውነት ሲሰጣቸው፤ የቀድሞዎቹን ባልደረቦዎቻቸውንና ስህተት የሆነውን በመተው፤ የከበረውን እውነት በመያዝ ከትክክለኛው ጎራ ለመሰለፍ፣ መልእክትኞቹን ለማድመጥ እንዲሁም የመልክቱን ውበትና በውስጡ ያለውን ውህደት ለመመልከት ተዘጋጅተዋል፡፡ EWAmh 50.1
የጌታን ሰንበት የሚቃወሙ መጽሐፍ ቅዱስ አንስተው የእኛን አቋም ስህተተኝነት ማመላከት ባለመቻላቸው የሚያምኑትንና እውነትን የሚያስተምሩትን ስም በማጥፋትና በእነርሱ ላይ በማሾፍ በባህሪዎቻቸው ላይ ጥቃት ይሰነዝሩ እንደነበር ተመልክቻለሁ፡፡ በአንድ ወቅት ጥንቁቅ፣ እግዚአብሔርንና ቃሉን ያፈቅሩ የነበሩ ብዙዎች የእውነትን ብርሃን በመቃወም ልባቸውን አደንድነው የእግዚአብሔርን ሰንበት የሚጠብቁትን እርጉም አድርገው ለማቅረብና በሐሰት ለመክሰስ የማያመነቱ ይሆናሉ ተቃዋሚዎች ያለ ፍርሃት እውነትን በይፋ የሚናገሩትን መጉዳት ይችሉ እንደሆነ በማሰብ ይህን አካሄድ ይከተላሉ ነገር 7ን እነዚህ ነገሮች የግዚአብሔርን ሥራ አያስተጓጉሉም፡፡ እንደውም እውነትን የሚጠሉ ሰዎች ሊገፉበት የመረጡት ይህ አካሄድ የአንዳንዶች 0ይኖች የሚከፈቱበትን ዕድል ይፈጥራሉ፡፡ ሕዝቡ ያንሰራራ ዘንድ የጌታ እጅ በእነርሱ ላይ በመሆኑ እያንዳንዱ የከበ ረ የእግዚአብሔር ልጅ ከያለበት ወጥቶ በአንድ ይሰባሰባል፡፡ እርሱ ሥራውን በክብር ወደ ክንውን ያመጣዋል EWAmh 50.2
እኛ እውነትን የምናምን የክፉው መጠቀሚያ መሣሪያ እንዳንሆን ኣብልጠን መጠንቀቅ ይገባናል፡፡ እያንዳንዱ አረማመዳችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ልናውቅ ይገባል፡፡: የእኛ ስህተትና ግድፈት በ1843 ላይ እንደተስተዋለው የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ለሚጠሉ ድል ይሆናቸዋል፡፡: EWAmh 51.1
ግንቦት 14/1851 ላይ የየሱስን ውበትና አፍቃሪነት ተመልክቼ ነበር፡፡ ክብሩን ስመለከት ከፊቱ ፈጽሞ መለየት እንደሌለብኝ አሰብኩ፡፡ ከዚያም ኣብን ከከበበው ከክብሩ ብርሃን ሲወርድ አየሁ፡፡ ይኸው ብርሃን አጠገቤ ሲቃረብ ሰውነቴ እንደ ቅጠል ሲርገፈገፍ ተሰማኝ፡፡ ብርሃኑ እኔ ጋር ደርሶ ቢሆን ኖሮ ልጠፋ እችል ነበር-ሆኖም ብርሃኑ ልፎኝ ሄደ:፡፡ በዚህን ጊዜ ከዚህ ታላቅና አስፈሪ አምላክ ጋር ባለን ግንኙነት ማድረግ ያለብንን በጥቂቱም ቢሆን ለማስተዋል ቻልኩ፡፡ ከዚያም አንዳንዶች በእግዚአብሔር ቅድስና ዙሪያ ያላቸውን የደበዘዘ ገጽታና የእርሱን ቅዱስና አቻ የሌለውን ስም ምን ያህል በከንቱ እንደሚያነሱና ይህ የሚያናግሩት አምላክ ምን ያህል ታላቅና አስፈሪ እንደሆነ ሳይገነዘቡ እንደሆነ ተመለከትኩ፡፡ ብዙዎች ሲጸልዩ ግዴለሽና ተገቢ ያልሆኑ አገላለጾችን ይጠቀማሉ፡፡ ይህ ደግሞ አፍቃሪውን የጌታ መንፈስ በማሳዘን ልመናቸው ሰማይ ሳይደርስ እንዲቀር ያደረጋል፡፡ EWAmh 51.2
እንዲሁም በሰማያዊው መቅደስ የሚያማልደን ካኅን በሌለበት በመከራው ጊዜ በጌታ ዓይኖች ስር ለመኖር ምን መሆን እንዳለባቸው ብዙ ዎች እንደማይገነዘቡ ተመልቻለሁ፡፡ እነዚያ የሕያው እግዚአብሔርን ማኅተም የሚቀበሉና በመከራው ወቅት ከለላ የሚያገኙI ሙሉ ለሙሉ የየሱስን ገጽታ ማንጸባረቅ አለባቸው:፡፡ EWAmh 51.3
ብዙዎች በጌታ ቀን ገጣሚ ሆነው ለመገኘትና በዓይኖቹ ስር ለመኖር «መታደስን» እና «የኋለኛውን ዝናብ” ብቻ በመሻት በእጅጉ አስፈላጊ የሆነውን ዝግጅት የማድረጉን ነገር ቸል ብለውት እንደ ነበር ተመልክቻለሁ: በመከራው ወቅት ያለ ከለላ የቀሩ ስንቶችን አየሁ! እነዚህ ሰዎች ዝግጅት የማድረግን አስፈላጊነት ችላ በማለታቸው በተቀደሰው አምላክ ፊት ገጣሚ አድርጎ የሚያቆማቸውን መታደስ መቀበል አልቻሉም ነበር፡፡ በነቢያት ለመታነጽ የተቃወሙና መላውን እውነት በመታዘዝ ነፍሳቸውን ለማጥራት ያልቻሉ፧ እንዲሁም እነርሱ ከሚገኙበት ተጨባጭ ሁኔታ በእጅጉ የተሻለ እንደሆኑ አድርገው ለማመን ፈቃደኞች የሆኑ ሁሉ መቅሰፍቶቹ በሚወርዱ ጊዜ የግንቡ አካል ይሆኑ ዘንድ መታነጽና መጠረብ ያስፈልጋቸው እንደ ነበር ይመለከታሉ፡፡ ነገር ግን ይህን ለማድረግ ጊዜ የለም፤ ልመናቸውን ተቀብሎ ከአብ ዘንድ የሚማልድም አይኖርም:፡፡ ከዚህ ጊዜ አስቀድሞ «ዐመጸኛው በዐመጹ ይቀጥል፤ ርኩሱም ይርከስ፤ ጻድቁም ይጽደቅ፤ ቅዱሱም ይቀደስ» የሚል ባለ ግርማ አዋጅ ይፋ ይሆናል፡፡ በመታበይ፣ በራስ ወዳድነት፣ ዓለምን በመውደድና በማንኛውም ከአንደበት በሚወጡ አጓጉል ቃላትና ድርጊቶች ላይ ድል ያላገኘ ማንም ቢሆን የሚያድሰውን ቃል ማካፈል እንደማይችል ተመልክቻለሁ፡፡ በመሆኑም ይበልጥ ወደ ጌታ የቀረብን በመምጣት በጌታ ቀን ለውጊያው ሊያቆመን የሚችለውን ዝግጅት በጽናት መሻት ይኖርብናል፡፡ እግዚአብሔር ቅዱስ መሆኑንና ቅዱስ የሆኑ ብቻ በእርሱ ፊት ለዘላለም መኖር እንደሚችሉ ሁሉም ያስታውሱ፡፡ EWAmh 51.4