ቀደምት ጽሑፎች
16—ዕውሩ (መንፈሳዊ ዐይኖቹ የታወሩት) ዕውሩን ሲመራ
ሊመጣባቸው ስላለው ነገር በእጅጉ አነስተኛ ግንዛቤ የነበራቸው--- መንፈሳዊ ዐይኖቻቸው የታወሩ መሪዎች ያፈሯቸው የነበሩ ነፍሳትም እንዲሁ ማየት የተሳናቸው እንደነበሩ ተመልክቻለሁ፡፡ እነዚህ እራሳቸውን ከእውነት በተቃራኒ ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ሰዎች በእውነት ድል ሲሆኑ ከመምህራኑ ብርሃን በመፈለግ እንደ እግዚአብሔር ሰዎች አድርገው ሲመለከቷቸው የነበሩ ብዙዎች ችግር ውስጥ ይወድቃሉ፡፡ እነዚህን መሪዎች ከሰንበት ጋር ዝምድና ያላቸውን ነገሮች ሲጠይቋቸው የሚሰጧቸው ምላሽ ከአራተኛው ትእዛዝ ተጨባጭ ሁኔታ ያፈነገጠ ይሆናል፡፡ ከሰንበት ተቃራኒ የሆኑ አያሌ አቋሞች ሲያዙ ሳለ እውነተኛው ታማኝነት ከግምት ውስጥ እንዳልገባ ተመልቼአለሁ፡፡ የእነርሱ ዋንኛ አጀንዳ ከጌታ ሰንበት በማፈግፈግ በእግዚአብሔር ከተባረከውና ከተቀደሰው ዕለት ውጪ በሆነው ቀን ማረፍ ነው፡፡ አንደኛውን አቋማቸውን እንዲለቁ ሲደረጉ ተቀባይነት አጥቶ ቀደም ብሎ ተኮንኖ የነበረውን ሌላውን ተቃራኒ ይይዛሉ፡፡ EWAmh 49.1
የእግዚአብሔር ሕዝቦች ወደ እምነት አንድነት እየመጡ ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን አምላካዊ ሰንበት የሚጠብቁ ተመሳሳይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶችን በመጋራት በአንድነት ጸንተው ሲቆሙ ነገር ግን ከዳግም ምጽአቱ ተከታይ ሕዝቦች ጋር በመሆን ሰንበትን የሚቃወሙ እርስ በርሳቸው በመከፋፈል ይበታተናሉ፡፡ አንዱ ሰንበትን በመቃወም ወደፊት በመምጣት አንዲህ፣ እንዲያ መሆን አለበት ይልና በመደምደሚያው ሰንበት ተፈጽሞአል ሲል አቋሙን ይፋ ያደርጋል፡፡ ሆኖም ይህ የእርሱ ኣካሄድ የሰንበትን ጥያቄ ተረጋግቶ እንዲቀመጥ ስለማያደርው እንዲሁም ሥራው ወደፊት እየገፋ በመሄዱና የጌታ ልጆች አሁንም ሰንበትን አጥብቀው በመያዛቸው ሌላው--ከእውነት ተቃራኒ ይዞ ብቅ ያለውን የመጀመሪያውን አመለካከት ሉ ለሙሉ ውድቅ በማድረግና በማጣጣል ከእርሱም ሆነ ከእኛ ተቃራኒ ንድፈ ሃሳብ ይዞ ብቅ ይላል፡፡ በተመሳሳይ ሦስተኛውም ሆነ አራተኛው ሰው ብቅ ቢሉም ነገር ግን ያንዳቸውም አመለካከት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ «ሰባተኛው ቀን የእግዚአብሔር አምላክህ ሰንበት ነው» በሚል እንደቀረበው አይሆንም:፡፡ EWAmh 49.2
እነዚህ የተመለከትኳቸው ነገሮች ሥጋዊ አስተሳሰብ ያላቸው እንጂ የእግዚአብሔር ቅዱስ ሕግ አካል አልነበሩም፡፡ የማጠቃለያ ሃሳቦቻቸው እርስ በርሳቸው የሚጣረሱና በአምላካዊው ሕጎች ላይ ጥሰት የፈጸሙ፣ አራተኛውን ትእዛዝ ከመጠበቅ ይልቅ ለመለወጥ ወይም ለማስወገድ ማንኛውንም ነገር የሚያደርጉ ናቸው:: በእነዚህ አስተምሮዎቻቸው ዙሪያ መንጋው የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ጸጥ ለማሰኘት ይመኛሉ፡፡ አብዛኞቹ ተከታዮቻ ቸው መጽሐፍ ቅዱሶቻቸውን የሚመረምሩት በጣም በጥቂቱ በመሆኑ መሪ ዎቻቸው በቀላሉ ሐስቱን እውነት አስመስለው በማቅረብ ሊያስቷቸው ይችላሉ:፡፡ እነርሱም መሪዎቻቸው የሚሏቸውን ብቻ አግዝፈው በመመልከት ይቀበሏቸዋል፡፡ EWAmh 49.3