ታላቁ ተጋድሎ
የአሳታሚዎቹ መቅድም
“መኖሪያቸውን የተውት” (ይሁዳ 6) የእነርሱ መሪ በሰማይ ከነበረው ቅዱስና የተከበረ ስፍራ ሲወድቅ በእግዚአብሔር ዓለም ላይ ከባድ ጥል (ውዝግብ) እንዲሰፍን አደረገ። GCAmh .0
ከጉዳዩ ባህርይ አንፃር በጽድቅና በኃጢአት መካከል ዘላለማዊ ቅራኔ ኖሮ መሆን አለበት። በንጽህናና በብክለት ምንም አይነት ህብረት ሊኖር አይችልም፤ የሁሉም ነገር ጠቅላይ ደራሲ የሆነው፣ ሁሉም ፍጽምና ከእርሱ የሚመነጨው እግዚአብሔር ለኃጢአትና ለሁሉም ፍሬዎቹ፣ ለአመጽ ደራሲና ለሁሉም ተከታዮቹ ድርድር የሌለው ጠላትነት አቋም ከመያዝ በቀር ሌላ ሊያደርግ አይቻለውም። GCAmh .0
ሌላ መደምደሚያውም ግልጽ ነው፦ እግዚአብሔር የሁሉም ክፋት ጠላት ሆኖ፣ በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ ምንም የማይሳነው ሆኖ፣ ከራሱ ባህርይ አብሮ በሚሄድ ሁኔታ፣ አመጽ ወደርሱ ግዛት እንዲገባና ለዘላለም እንዲኖር ሊፈቅድ አይቻለውም። ሰርጎ ገቡ ወደ ውጪ መጣል አለበት፤ የሰላም በጥባጩ መደምሰስ አለበት። ይህንን ተጋድሎ በተመለከተ በቅዱስ ፈጣሪና በአማጺ ፍጡር መካከል ስላለው ክርክር (ተጋድሎ) ጉዳይ ምንም ጥያቄ ሊኖር አይችልም። GCAmh .0
ኃጢአት ለሁሉም አለማት ፍጡራን ባህርይውንና ውጤቶቹን በሙላት ይገልጽ ዘንድ ይህ ተጋድሎ በተፀነሰበት ጊዜ እንዲቆም ሳይደረግ ቆይቷል። ኃጢአት በስተመጨረሻ በሚደመሰስበት ጊዜ፣ ያገኘው መከራ የተገባው እንዲሆን እያንዳንዱን አዕምሮ የሚያሳምን በቂ ማስረጃ ይለግሳል፤ የተገባውን ውድመትም ሁሉም በደስታ ይቀበሉታል። GCAmh .0
ደስ የሚያሰኘው ነገር፣ ከከኃዲ መላዕክት ውጪ፣ ከኛ (ምድር) በስተቀር ሌላ በዚህ የኃጢአት አመጽ ተጽዕኖ ስር የወደቀ ዓለም ስለመኖሩ መረጃ የለንም። መሳጭ የሆነ ጉዳይ ይሆን ዘንድ ግን ይህ በቂ ነው፤ ምክንያቱም ሰይጣንና መላዕክቱ ከሰማይ ተባረው ይህ ዓለም የእውነትና የሀሰት ትንቅንቅ ብቸኛ የቲአትር መድረክ ሆኗል። ሁሉም ሰዎች ተሳታፊ ሆነዋል። ከኃጢአት የመታደስ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የመታረቅና የተቀባይነት ደረጃ ላይ የመድረስ ችግር በእርሱና በድነት መካከል ተጋድሞአል። GCAmh .0
ታዲያ ካለፈበት ደረጃ፣ አሁን ካለው እርምጃና የወደፊቱ ክስተት አንጻር እንደዚህ ታላቅ ተጋድሎ በሚመስጥ ትኩረት ሊታይ የሚችል ሌላ ምን ርዕስ አለ? በምንና በእንዴት አይነት ሁኔታ ነው ተጋድሎው የሚያበቃው? ለረጅም ጊዜ ሲናፈቅ የነበረው መቋጫውስ እየቀረበ እንደሆነ ማስረጃ አለ? GCAmh .0
እነዚህን ታላላቅ ጉዳዮች አስመልክቶ የሚከተሉት ገጾች ተሰጥተዋል፤ ለእንደዚህ አይነቱ ሥራ ደግሞ ጸሐፊዋ የተለየ ብቃት እንደያዘች ተወዳዳሪ የሌለው ግልጽ ማረጋገጫ አለን። ገና ከልጅነቷ ጀምሮ ለእግዚአብሔር ቃል ስለነበራት ክብርና ፍቅር፣ ለአገልግሎቱም ስላላት ቅንዓትና መሰጠት ልብ የተባለች ናት። በቅዱስ መጻሕፍት ተስፋዎች ያላት መጠን የለሽ እምነት፣ በአዳኙ አጠገብ መኖር ትችል ዘንድ የሚገፋፋና መንገድ የከፈተ ሆኖላታል። የመንፈስ ቅዱስ በረከት በገፍ ተሰጥቷታል። የዚህ መንፈስ አንዱ ሥራም “የሚመጡትን ነገሮች” (ዮሐ 16÷13) ለክርስቶስ ተከታዮች ለማሳየት መሆኑ አስቀድሞ GCAmh .0
እንደተነገረ፣ እንደ አንድ የቤተ ክርስቲያን ሥጦታ እንዲደረግ በታዘዘው መንገድ አማካኝነት መሥራት የትንቢት መንፈስ ስጦታ ተብሎ ተገልጾአል (1ኛ ቆሮ 12÷9፣10፤ 14÷1)፤ ስለዚህም ወደ ትኩረትዋ የመጡትን ባለፉት ጊዜያት የተከናወኑ ነገሮች፣ ተመዝግቦ ከሚገኝ ከማንኛውም አውድ ይልቅ ልቅም ባለ ሁኔታ እንድትናገር፣ እንዲሁም ከሰው ችሎታ በላይ በሆነ እይታ የወደፊቱን እንድታነብ በመለኮት መገለጥ እንደተባረከች እናምናለን። ከሰማይ አባታችን ጋር ህብረት ማድረግ ምን እንደሆነ የሚያውቁ እነርሱ፣ እነዚህን ገጾች ሲያነቡ መሀሪ፣ ታላቅ ካህን ሆኖ ክርስቶስ ከተቀመጠበት፣ ወደ ክብር ለሚያመጣቸውም በርካታ ልጆቹ እርዳታ ለመላክ ሁልጊዜም ዝግጁ ከሆነበት የፀጋ ዙፋን ፀኃፊዋ እርዳታ እንደምትቀበል፣ ከሰማያዊ ምንጭም እንደምትቀዳ ማመን የሚገባቸው መሆኑን እንደሚሰማቸው እናስባለን [እብ 2÷10]። GCAmh .0
ከመንፈስ ከሆነው ታላቅ መጽሐፍ - ከመጽሐፍ ቅዱስ ቀጥሎ፣ አሁን እየተከናወነ ስላለው ታሪክ ስለሁሉም ነገሮች ፍጹም መታደስ በበለጠ ግሩምና መሳጭ በሆነ መልኩ የሚያቀርብ፣ ለህዝብ የተበረከተ ከዚህ የተሻለ መጽሐፍ የለም። የዚህ ዓለም መዝጊያ ታሪክ ክስተቶች እጅግ አስደማሚና አስፈላጊ ባህርይ ያላቸው በመሆኑ፣ እነዚህ ጉዳዮች በዚህ ሥራ በበለጠ፣ በስፋት ትኩረት አግኝተዋል። አንባቢው፣ በጌታችን የማቴዎስ 24 ታላቅ ትንቢት ጀምሮ ታሪኩን ቢከታተል፣ ቃል ወደተገባላት መቤዠት ስትራመድ በገጠማት ጦርነትና ስቃይ ለቤተ ክርስቲያንዋ ወደሚሰማው አዲስ የርኅራኄ ስሜት ሲገባ ራሱን ያገኘዋል፤ በእግዚአብሔር ህዝቦች የመጨረሻ ድል መንሳት ጥርት ያለ ገለፃ፣ የሰይጣንና የሁሉም ተከታዮቹ ውድመት፣ ፍጹምና ዘላለማዊ የሆነ የክፋት ሥራ ከዓለማት መወገድ፣ ተላቁ ተጋድሎም ሲጠናቀቅም የቅዱሳን የዘላለም ርስት ትሆን ዘንድ የምድር መታደስ፣ የእያንዳንዱን ነፍስ የሚያቃጣጥል ይሆናል። GCAmh .0
እዚህ የቀረቡት ርዕሰ ጉዳዮች የገዘፉ ምስሎችና ግሩም ጥልቀት የሚያካትቱ ቢሆኑም፣ ሐዋሪያውም እንደሚናገረው፣ መንፈስ ብቻ ሊመረምረው የሚቻለውን፣ “የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር” (1ኛ ቆሮ 2÷10) የያዙ ቢሆንም፣ ለመረዳት ቀላል በሆነ፣ ባልተወሳሰበ እና አስቸጋሪ ባልሆነ ቋንቋ የቀረቡ ናቸው። የዚህ ሥራ መነበብ፣ ለቅዱስ መጻሕፍት ያለውን መተማመንና ፍቅር፣ ለሰዎች መቤዤት በሰራው ድንቅ ሥራ ለክርስቶስ የበለጠ አዘኔታ፣ ሁሉንም የጥበብና የእውቀት መዛግብት ለያዘው ለሁሉም ፀጋ አምላክ ለሆነው እግዚአብሔር የበለጠ አክብሮት ወደ መስጠት እንደሚመራ በማወቃችን ሐሴት እናደርጋለን። GCAmh .0
የዚህ ሥራ የተለያዩ እትሞች እስካሁን [ተሰራጭተው] ስላለቁ፣ በተለያዩ ቋንቋዎች እንዲተላለፍ ምቹ ሆኖ፣ ተሻሽሎና መጠኑ ጨምሮ፣ ይህንን እትም ስንልክ የተለየ ደስታ ይሰማናል። መግለጫዎቹ ለሥራው ፍላጎትና ዋጋ ይጨምሩለታል። ለሚያነቡ ሁሉ በረከት፣ ለታላቁ አምላክ ክብር የሚጨምር ይሁን። GCAmh .0