ታላቁ ተጋድሎ

1/45

ታላቁ ተጋድሎ

የተርጓሚው ማስታወሻ

በታላቁ የማዳን እቅዱ ውስጥ ሠራተኛ ሆኜ አገለግለው ዘንድ ለእኔ ከሁሉም ለማንሰው ሰው መላእክት የሚመኙትን ሥራ እሰራ ዘንድ እድሉን ለሰጠኝ ለአምላኬ ክብር ምስጋና ይሁን። ከጥፋት የሚነጥቅ አምላክ ነውና፣ በምክሩ ግሩም, በምሪቱም አስደናቂ ነውና እንደ እርሱ ያለ የሌለ መሆኑን እመሰክርለታለሁ። GCAmh .0

በትርጉም ሥራ ገና ብላቴና ብሆንም በኔ ላይ እምነት ጥለው፣ በመጨረሻው ዘመን ማብቂያ ጠርዝ ላይ ለምንገኝ ለእኛ እጅግ ጠቃሚ ምሪት የሚሰጠውን ይህንን መጽሐፍ እንድተረጉም እድሉን ለሰጡኝ የቤተ ክርስቲያናችን የህትመት ክፍል መሪዎች ምስጋና አቀርባለሁ። GCAmh .0

ለውድዋ ባለቤቴ ሰብለ ደሴ ግሩም ለሆነው ድጋፍዋ እንዲሁም የተጋራችውን የኃላፊነት ሸክም በደስታ ተረክባ ላበረከተችው አብይ አስተዋፅዖ ላመሰግናት እወዳለሁ። GCAmh .0

ሙሉ የመጽሐፉን የጽሑፍ ሥራ በመሥራት ለረዱኝ ለአቶ ደመቀ አየልኝ፣ ለወ/ሮ ሜሮን ሹሜ እና ለአቶ ግርማ አበባው፣ የከበረ ምስጋና አቀርባለሁ። GCAmh .0

በአርትኦት ሥራው ለተሳተፉ ለአቶ ኤፍሬም ዳዊት፣ ለወንድም ገለቶ ገመቹ፣ ለወ/ሮ እንያት ሰንደቅ፣ ለአቶ ታምሬ ሻዕማሎና ሌሎችም፣ በተለይ ደግሞ ለአቶ ደመቀ አየልኝ ምስጋናየ ታላቅ ነው። GCAmh .0

በተለያዩ እልህ አስጨራሽ ግድድሮሾች ውስጥ ሳልፍ፣ በከባድ ፈተናዎችና ሐዘኖች ውስጥ ሥራመድ የፀሎት ክንዶቼ በመሆን ላሸነፉልኝ ወታደሮች ለእህቴ ለኤፍራታ አጋዤ፣ ለወ/ሮ ህይወት ካሳሁን፣ ለወ/ት ውባሉ ጥላሁን፣ ለአቶ ግርማ አበባው፣ ለአቶ ደመቀ አየልኝ፣ ለአቶ ኤፍሬም ዳዊትና ሌሎችም በርካታ ሰዎች አድናቆቴ ወደር የለውም። GCAmh .0

ራሱ ዲያብሎስ ካልሆነ በስተቀር ይህንን መጽሐፍ አንብቦ የማይባረክ፣ ባህርይውን ለማደስ ቁርጥ ውሳኔ የማያደርግና ለጌታ ለመሰብሰብ የማይፈልግ ሰው ይኖራል ብዬ አላምንም። GCAmh .0

ስለሆነም ወደ ሰማይ ለምናደርገው ጉዞ አይነተኛ እገዛ የሚያበረክተውን ይህንን መጽሐፍ ያነቡ ዘንድ ሁሉም በአክብሮት ተጋብዘዋል። GCAmh .0

* በዚህ መጽሐፍ የተካተቱ ጥቅሶች የተወሰዱት ከ1879 ዓ.ም. እና ከ1962 ዓ.ም. ትርጉም ነው። GCAmh .0

** አንዳንድ ሐሳቦች የበለጠ ግልጽ እንዲሆኑ የአሳታሚዎቹና የተርጓሚው ማብራሪያዎች በቅንፍ [ ] ውስጥ ተቀምጠዋል። GCAmh .0

***’Scriptures’ የሚለው ቃል እንደ አስፈላጊነቱ አንዳንድ ጊዜ ‘መጽሐፍ ቅዱሳት’፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ‘መጽሐፍ ቅዱስ’ ተብሎ ተተርጉሟል። GCAmh .0

**** የመጽሐፉ የዘመን አቆጣጠር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር (እ.አ.አ.) ነው። GCAmh .0