የአድቬንቲስት ቤት
ምዕራፍ ሃምሳ—ሰባት ለማያምን የትዳር አጋር የሚንፀባረቀው ጠባይ
ክርስቲያን ሚስት የማያምን ባልዋን ትተው?፦ በቤት ውስጥ ካሉባቸው ፈተናዎች የተነሳ ምክር ከሚጠይቁ እናቶች ደብዳቤዎችን ተቀብያለሁ። ከነዚህ ደብዳቤዎች ውስጥ የአንዱ ሁኔታ የብዙዎቹን የሚመለከት ነው። ባልና አባት አማኞች አይደለም፤ በመሆኑም ልጆችዋን በማሠልጠን ረገድ እናት ሁሉም ነገር ከባድ ሆኖባታል። ባልዋ የረከሰ ሰው ነው፤ ቋንቋውም ባለጌና የስድብ ነው፤ ልጆቹ ሥልጣንዋን እንዳያከብሩ ያስተምራቸዋል። ከልጆችዋ ጋር ለመፀለይ በምትሞክርበት ጊዜ ይመጣና ማንቧረቅ በሚችለው ከፍተኛ ጩኸት፣ እግዚአብሔርን በመርገም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መጥፎ ቅጽል ስሞችን ያዥጎደጉድበታል። ተስፋ ቆርጣለች፤ ሕይወት ሸክም ሆኖባታል፤ ምን ማድረግ ትችላለች? እንደዚህ ዓይነት ቤት ውስጥ መቆየትዋ ለልጆችዋ የሚያመጣው ጥቅም ምንድን ነው? በእግዚአብሔር የወይን ሥፍራ ጥቂት ሥራ የመሥራት ልባዊ ፍላጎት አላት፤ ልጆችዋ እንዲያዋርዷትና እንዲያምጹባት ሁልጊዜ ከሚያስተምራቸው ባልና አባት ጋር አብሮ ከመኖር መለየት እንደሚሻልም ታስባለች። AHAmh 251.1
ለእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ የእኔ ምክር፡- እናቶች ሆይ ሻካራና ፈላጭ ቆራጭ አስተሳሰብ ባለው ባልና አባት ምክንያት በነፍስ ቁስለትና ብልዘት እንዲሁም በድህነት ውስጥ ታልፉ ዘንድ ብትፈተኑ ልጆቻችሁን አትተዉ፤ ለአምላክ-የለሹ አባታቸው አትተዋቸው። ኃላፊነታችሁ በማያወላውል ሁኔታ በሰይጣን ቁጥጥር ሥር ካለው አባታቸው ተጽዕኖ እንድትከልሏቸዉ ነው። 1 AHAmh 251.2
ራስን በመግዛት ሕያው ምሣሌነትን ለግሱ፦ ፈተናዎች አሉባችሁ፤ አውቃለሁ፤ ሆኖም ከማቀራረብ ይልቅ የሚያራርቅ መንፈስ አለ። ራስን የመቆጣጠርና የታጋሽነት ሕያው ምሣሌነት ባለቤትሽ በእያንዳንዱ ቀን ሊያይ ይገባዋል። እርሱን ለማስደሰት የምትችይውን ሁሉ አድርጊ፤ ሆኖም አንዴ እንኳን ከእውነት መርህ ፈቀቅ ለማለት እንዳይዳዳሽ…. AHAmh 251.3
ክርስቶስ ሙሉ አካላችን ለአገልግሎቱ እንዲውል ይፈልጋል - ልብ፣ ነፍስ፣ አዕምሮና ጉልበት ለርሱ እንዲሆኑ ይፈልጋል። የሚጠይቅሽን ሁሉ ከሰጠሽው በባህርይ እርሱን ትወክያለሽ። መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ሲሠራ ባልሽ እንዲያይ አድርጊው። ጥንቁቅና አሳቢ፣ ታጋሽና ይቅር-ባይ ሁኚ። እውነትን እንዲቀበል አታስገድጅው። እንደ ሚስት የሚገባሽን ኃላፊነት ፈጽሚና ልቡ መነካት አለመነካቱን እይ። በሚቻልሽ መንገድ ሁሉ አስደስቺው፤ ኃይማኖታችሁ አያራርቃችሁ፤ ከግንዛቤ በመነጨ መታዘዝ እግዚአብሔርን ታዘዢው፤ በምትችይው አጋጣሚ ሁሉ ባልሽን አስደስችው። AHAmh 251.4
የሱስን እንደምትወጅውና እንደምታምኝው ሁሉም ይዩ። ባለቤትሽ የሚያምኑትና የማያምኑት ጓደኞችሽ ሁሉ የእውነትን ውበት እንዲያዩ እንደምትፈልጊ ማስረጃ ስጫቸው። ሁልጊዜ መልካም ሥራን የሚያበላሸውን ያንን የሚያሳምምና የሚያሳስብ ጭንቀት ግን አታሳዪ…. AHAmh 252.1
ባል አንድም የወቀሳ ወይም ጥፋቱን ነቅሶ የሚያወጣ ቃል አይስማ። አንዳንድ ጊዜ በአጣብቂኝ ቦታዎች ታልፊያለሽ፤ ስለነዚህ ችግሮች ግን አታውሪ። ዝምታ አንደበተ-ርቱዕነት ነው። ችኩል ንግግሮች የሚያመጡት ፋይዳ ቢኖር ደስታ-ቢስነሽን ማከል ነው። ደስተኛና ፍልቅልቅ ሁኚ። የምትችይውን ሁሉ የፀሐይ ብርሃን ወደ ቤትሽ በማምጣት ጥላዎቹን አባርሪያቸው። የጽድቅ ፀሐይ ብሩህ ጨረሮች በነፍስሽ መቅደስ ክፍሎች ላይ ያንፀባርቁ። ከዚያም የክርስቲያን ሕይወት ውብ መዓዛ ወደ ቤተሰብሽ ይመጣል። ልዩነት በሚፈጥሩ እውነት በሌለባቸው ነገሮች ላይ ብዙ ጊዜ መኖር ያበቃል። 2 AHAmh 252.2
ሸክም የበዛባት ግን ደስተኛነትዋን እንድትጠብቅ የምትመከር ሚስት፦ ባልሽ ፊቱን ከየሱስ ስለመለሰ አሁን እጥፍ ኃላፊነት አለብሽ…. AHAmh 252.3
ቃሉን በመተግበር ረገድ ብቻሽን በመቆምሽ ከፍተኛ ሐዘን እንደሚሰማሽ አውቃለሁ። ኦ ሚስት ሆይ ወጥነት ያለው የእምነትና የመታዘዝ ሕይወትሽ ባልሽን ወደ እውነት ሊመልሰው እንደሚችል አታውቂምን? ውድ ልጆችሽ ወደ ክርስቶስ ይምጡ። በቀላል ቋንቋ ስለ እውነት አስተምሪያቸው፤ የክርስቶስን ፍቅር የሚገልጹ አስደሳችና ማራኪ መዝሙሮችን ዘምሪላቸው። ሕፃናትን ይወዳልና ልጆችሽን ወደ የሱስ ይዘሻቸው ነይ። AHAmh 252.4
ሁሌም ደስተኛ ሁኚ፤ ክርስቶስን የወከለው የሚያጽናናው መንፈስ ቅዱስ ካንች ጋር እንዳለ አትርሺ፤ ፈጽሞ ብቸኛ አይደለሽም። አሁን የሚናገርሽን ድምጽ ብትሰሚ፤ የልብሽን በራፍ ለሚያንኳኳው ሳትዘገዪ ብትከፍቺ “ከአንተ ጋራ እራት እበላ ዘንድ አንተም ከኔ ጋራ ጌታ የሱስ ሆይ ወደ ቤቴ ግባ” ብትይው ሰማያዊው እንግዳ ይገባል። ፈጽሞ መለኮታዊ የሆነው ከአንቺ ጋር ሲኖር ሠላምና ዕረፍት አለ። 3 AHAmh 252.5
ክርስቲያናዊ መርሆዎችን ጠብቂ፦ እግዚአብሔር የማይመለክበት ቤተሰብ በባህር መሐል እንዳለች መሪ እንደሌላት መርከብ ነው። ከባድ ማዕበል ይመታታል፤ ይሰባብራትማል፤ በውስጥዋ ያሉትም ሁሉ የማለቅ አደጋ ይጋረጥባቸዋል። ለክርስቶስ ስትይ ለራስሽና ለልጆችሽ ሕይወት ከፍተኛ ዋጋ ስጪ፤ [በፍርድ ቀን] በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ልጆችሽንና ባልሽን መገናኘትሽ አይቀሬ ነውና። ጠንካራዎቹ የክርስቲያን መርሆዎችሽ እያደጉና እየጎለበቱ ይሂዱ እንጂ አይድከሙ። ምንም ያህል ባልሽ ቢበሳጭ እጅግም ቢቃወምሽ የማያወላውል ታማኝ ክርስቲያናዊ ጥንካሬ አንፀባርቂ። ከዚያም በአፉ ያሻውን ቢለፈልፍም እንኳ የሥጋ ልብ እስካለው ድረስ በልቦናውና በውሳኔው ውስጥ ሳያከብርሽ አይቀርም። 4 AHAmh 252.6
ለእግዚአብሔር መጠይቅ ቅድሚያ ይሰጠው *፦ ከዚያም የእንጀራ ልጁን አየሁ፤ በእግዚአብሔር የተወደደች ናት ግን በባርነት እሥራት የተያዘች፣ ፈሪ፣ የምትንቀጠቀጥ፣ ተጠራጣሪ፣ የተከዘችና በጣም ድንጉጥ ናት። ይህች እህት እምነት ለሌለው ከእርስዋ ያነሰ ዕድሜ ላለው ወጣት ፈቃዷን ማስገዛት እንዳለባት ሊሰማት አይገባትም። ጋብቻዋ ማንነትዋን ሊያጠፋው እንደማይገባ ታስታውስ። በላይዋ ያለው የእግዚአብሔር መጠይቅ ከማንኛውም ምድራዊ መጠይቅ የበለጠ ነው። ክርስቶስ በራሱ ደም ገዝቷታልና የራስዋ አይደለችም። በእግዚአብሔር ላይ ሙሉ እምነትዋን መጣል ተስኗት ሕሊናዋን ለፈላጭ ቆራጭና ጨካኝ ፍጡር አሳልፋ ሰጥታለች። ዲያቢሎስ ጌታው በርሱ በኩል በተሳካ ሁኔታ ይሠራ ዘንድ የምትርበደበደዋንና የምትሸማቀቀዋን ነፍስ የበለጠ ማስበርገግ ይቻለው ዘንድ በሰይጣን ለሚተኮስ ሰው ራስዋን አስገዝታለች። ብዙ ጊዜ በመንፈስ መናወጥ ውስጥ አልፋ የስሜት መረጃ ተቀባይ አካልዋ ብትንትኑ የወጣ እንክትክት ያለች ሆናለች። አገልግሎትዋ እንዲነፈገውና ይህች እህት በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንድትሆን የጌታ ፈቃድ ነው? አይደለም። ጋብቻዋ የዲያብሎስ የማጭበርበር ተግባር የተፈፀመበት ነበር። አሁን ግን አንዴ አግብታለች፤ መልካም የሆነውን ሁሉ ለማግኘት ትጣር፤ ባልዋን በለሆሳስ ታስተናግደው፤ ሕሊናዋን ሳትጥስ ደስ ይለው ዘንድ የሚቻላትን ታድርግ። በዚህ አመጹ ከቀጠለ ሊያገኘው የሚችለው ሰማይ ይህ ዓለም ብቻ ነው። ነገር ግን በአስፈሪው ዘንዶ መንፈስ የተያዘውን ጨቋኝ የሆነውን ባልዋን ለማስደሰት ስትል [መንፈሳዊ] ስብሰባዎችን የመካፈል እድልዋን ባትጠቀምበት ይህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም። 5 AHAmh 253.1
ሌላኛው አለ:- “አግብቻለሁ ስለዚህ መውጣት አልችልም” የዚህ ሰው ጥፋት ማግባቱ አይደለም፤ ከከፍተኛውና ከአስፈላጊው የሕይወት ጉዳይ ሕሊናዋን ካፋታች ሴት ጋር መጋባቱ እንጂ። አንድ ወንድ ሚስቱና ትዳሩ ሐሳቡን ከክርስቶስ እንዲያርቅ ወይም የወንጌሉን ወርቃማ ግብዣ እምቢ እንዲል ይመሩት ዘንድ ፈጽሞ መፍቀድ የለበትም። 6 AHAmh 253.2
ሁሉንም ከማጣት ግማሽ ማትረፍ ይሻላል፦ ወንድም ኬ(K) ብዙ ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች ገጥመውሃል፤ ሆኖም ለቤተሰብህ የሚገባውን ለማድረግ ቅን ጠንካራና የውሳኔ ሰው ሁን፤ ከተቻለም ከአንተ ጋር ውሰዳቸው። ወደ ሰማይ በምታደርገው ጉዞ አብረውህ ይሆኑ ዘንድ ምንም ዓይነት ጥረት አትቆጥብ። ነገር ግን ልጆችህና እናታቸው አብረውህ ሊጓዙ ፈቃደኛ ካልሆኑ እንዲያውም ከኃይማኖታዊ AHAmh 253.3
አባላት የተሰጡ ምስክርነቶች ናቸው፡፡ ይህ ለወንድም ቲ(T) ከተሰጠው መልእክት የቀጠለ ነው - አዘጋጆቹ፡፡ ኃላፊነቶችህና ግዴታዎችህ ሊያደናቅፉህ የሚጥሩ ከሆኑ ብቻህንም ቢሆን እንኳ ወደ ፊት መራመድህን ቀጥል። ኑሮህ ፈሪሃ-እግዚአብሔር ያለው ይሁን። ስብሰባዎችን በመካፈል ልታገኝ የምትችለውን ሁሉንም የመንፈሳዊ ኃይል የመሰብሰብ እድልህን ተጠቀምበት፤ ሊመጣ ላለው ቀን ያስፈልግሃልና። የሎጥ ሀብት ንብረት ሁሉ ወደመ፤ ማጣት ቢያጋጥምህ ተስፋ አትቁረጥ፤ የቤተሰብህን አንዱን ክፍል ማትረፍ ሁሉንም ከማጣት እጅግ የተሻለ ነው። 7 AHAmh 253.4